“ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛና” የመሥራት መብት
Frågor och svar om AT-UND och rätten att arbeta – amhariska
አዎ፡ አገሪቱን ለቀው ለመውጣት ከስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር እስከተባበሩ ድረስ ውሳኔው ከተሰጥዎ በኋላም ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) ሊይዙ ይችላሉ።
አዎ፥ ማንነትዎን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሌላ ዓይነት መንገድ እንዲያረጋግጥ ከተባበሩ ይቻላል።
ከ16 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ብቻቸውን የመጡ ልጆች ስዊድን ውስጥ እንዲሠሩ ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) ሊኖራቸው ይገባል። 16 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች በልምምድና አነስተኛ ሥራዎች እንዲሁም አንድ ቁንጽል ሥራ ለመሥራት ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) አያስፈልጋቸውም። ይሁን እንጂ የአሳዳጊው ወይም ሞግዚቱ ፈቃድ መሆኑን ማሳወቅ ያስፈልጋል። በደሞዝ ሆነ በድጎማ መልክ የሚሰጥ ጥቅም ሁላ፥ ለምሳሌ እንደ ስጦታ ካርድ፥ በLMA ደንብ መሠረት ያገኙትን የመታገዝ መብት ሊነካ እንደሚችል ያስተውሉ።
አዎ፡ 16 ዓመት ከሞላህ/ሽ ወይም በላይ ከሆንክ/ሽ። ከ16 ዓመት በታች የሆኑ የአሳዳጊው ወይም ሞግዚቱ ፈቃድ መሆኑን ማሳወቅ ያስፈልጋል።
አይ፡ አይኖርበትም።