የጥገኝነት ውሳኔ ካገኘህ በኋላ

Efter beslut om din ansökan om asyl – amhariska

የስደተኞች ጽ/ቤት የጥገኝነት ጥያቄህን መልስ ከሰጠበት በኋላ በመቀበያው ኣሃዱ ልትጠራ ነው። እዛውም ውሳኔውን በሚመለከት መረጃ ይሰጠሃል እንዲሁም ውሳኔው ላንተ ምን ማለት መሆኑን መግለጫ ይሰጠሃል።

የጥገኝነት ጥያቄህን በሚመለከት ኣዎንታዊ መልስ የተቀበልክ ስትሆን ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ይሰጠሃል፡ በስዊደን ኣገር ለመኖርም መብት ታገኛለህ።

ብስዊድን ኣገር ስትኖር ምኑ እንደሚመለከትህ በተጨማሪ ኣንብብ

የጥገኝነት ጥያቄህን በሚመለከት ኣሉታዊ መልስ የተቀበልክ ስትሆን ጥያቄህ ውድቅ ሁኗል ማለት ነው። እንዲህ ሲባል ደግሞ የስደተኞች ጽ/ቤት በስዊደን ኣገር ለመኖር በቂ ምክንያት እንድሌለህ ያምናል ማለት ነው። ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን ሁለት ኣማራጮች ይኖሩሃል ፤ ውሳኔውን ተቀብለህ ወደ ኣገርህ መመለስ፡ ወይም የይግባኝ/ኣቤቱታ ጥያቄ ማቅረብ።

የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን ምን እንደሚመለከትህ በተጨማሪ ኣንብብ

Last updated: