በመጠባበቅ ላይ እያለህ

Medan du väntar – amhariska

መረጃው፡ በስዊድን ኣገር ጥገኝነት ጠይቀው ሲያበቁ ገና መልስ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ሰዎች ይመለከታል

እዚህ፡ የጥገኝነት ጥያቄ ካቀረብክ በህዋላ ምን እንደሚካሄድና እንደ ስደተኛ መጠን በስራ ላይ፡ በትምህርት፡ በመኖርያ ቤት፡ በጤናና እንክብካቤ፡ በገንዘብ እርዳታ የሚኖርህን መብቶች በሚመለከት ማንበብ ትችላለህ።

የጥገኝነት ጥያቄ ምርመራ እስኪጀመር ያለው ጥበቃ

የጥገኝነት ጥቃቄዎን በተመለከተ ለምርመራ እስኪቀርቡ ድረስ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ሲቀርቡ ግን ለምን ስዊድን አገር ጥገኝነት መጠየቅ እንደፈለጉ፥ ምን እንደደረሰብዎት፥ ወደ አገርዎ ቢመለሱ ምን ሊደርስብዎት እንደሚችል መግለጽ ይኖርብዎታል።

ውሳኔ እስኪያገኙ ብዙ ጊዜ ለጥያቄ ሊጠሩ ይችላሉ። የስደተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤቱ (Migationsverket) በቀጠርዎት ቀንና ሰዓት ይምጡ። የጊዜ እጥረት ስላለብን፥ አዲስ የቀጠሮ ቀን መያዝ ጉዳይዎ ውሳኔ የሚያገኝበትን ጊዜ ሊያራዝምብዎት ይችላል።

አድራሻዎን ያሳውቁ

አድራሻዎን ከቀየሩ፥ ለጥያቄ ስንፈልግዎት ሆነ ለሌላ ጉዳይ እንድናገኝዎት አዲሱን አድራሻ ለስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migationsverket) ያሳውቁ። ከስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚላክ መረጃ እንዳያመልጥዎ የሚመጣልዎትን ደብዳቤ ሁሉ እየተከታተሉ ያንብቡ።

ኣንተን፡ እንደ ጥገኝነት ፈላጊ ሊረዱህ የሚችሉ ተቋሞች

ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል Amnesty International External link, opens in new window.

ካሪታስ ስቨርየ Caritas Sverige External link, opens in new window.

የሰደተኞች የጥገኝነት ኮሚቴ ምክርቤት Flyktinggruppernas och asylkommittéernas riksråd External link, opens in new window.

የጥገኝነት ፈላጊዎችና የስደተኞች ምክር ሰጪ ጽ/ቤት Asylrättscentrum External link, opens in new window.

ህጻናትን ኣድን Rädda barnen External link, opens in new window.

ቀይ መስቀል Röda korset External link, opens in new window.

የስዊድን ቀይ መስቀልና የጦርነት ቁስለኞችና የተገፉት የመንከባከብ ማእከል Svenska Röda Korsets behandlingscenter för krigsskadade och torterade External link, opens in new window.

ማሕበራዊ ሚስዮን Sociala missionen External link, opens in new window.

ስዊደናዊት ቤትክርስትያን Svenska kyrkan External link, opens in new window.

RFSL-Newcomers External link, opens in new window.

ስለስዊድን ማህበረሰብ መረጃዎች በተለያዩ ቋንቋዎች በእነዚህ ውስጥ ይገኛል Information om Sverige External link, opens in new window.

Last updated: