ለጥገኝነት ፈላጊዎች የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ

Ekonomiskt stöd för asylsökande – amhariska

ራስን መደገፍ መቻል አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሰራ ሰርተህ ገንዘብ እያገኘ ካሆነ ወይም ሌላ ምንም ዓይነት ምንጭ ከሌለህ ለስደተኞች ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግልህ ማመልከት ትችላለህ፡፡ የገንዘብ ድጋፉ ብዙ ክፍሎች አሉት፡- የዕለት ወጪ ድጎማ፣ የቆይታ ወጪ እና ልዩ አበል፡፡

ጥገኝነት ስትፈልግ ለስደተኞች ቦርድ ምን ያህል ገንዘብ ወይም ሌላ ሀብት እንዳለህ መናገር ይኖርብሃል፡፡ የራስህ የሆነ ምንም ዓይነት ሀብት ከሌለህ የዕለት ወጪዎችህን ለመሸፈኛ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግልሃል፡፡ በጋብቻ ተሳስረው አንድ ላይ የሚኖሩና ሳይጋቡ አንድ ላይ የሚኖሩ ሰዎች የቤተሰቡን ኢኮኖሚ በተመለከተ የጋራ ሃላፊነት አላችው። ይህ ማለት፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእርስዎን የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብት በሚያጣራበት ወቅት የኑሮ ጓደኛዎን ገቢ ከግምት ያስገባል ማለት ነው።

የነበርዎት የኢኮኖሚ መጠን ሲቀየር፣ ለምሳሌ እርስዎ ወይም የኑሮ ጓደኛዎ ሥራ ከያዙና ገቢ ማግኘት ከጀመሩ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማሳቅውቅ ይኖርብዎታል። እርስዎ ወይም የኑሮ ጓደኛዎ የቀን አበል እያገኛችሁ እያለ በደሞዝ መልክ ገቢ ማግኘታችሁን አለማሳወቅ ወንጀል ነው። የመኖሪያ ቤት በሚቀይሩበት ግዜ የቀን አበል የማግኘት መብትዎ ላይ ለውጥ ሊደረግ ይችላል። ስለዚህ ሁሌ ወደ አዲስ አድራሻ ሲቀይሩ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያሳውቁ።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለህ ስራ ብታገኝ ማድረግ የሚገባህን ለማወቅ የበለጠ አንብብ፡፡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የቀን አበል

የቀን አበል መጠን እንደየ ሚኖሩበት ሁኔታ የተለያየ ነው፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በሚያዘጋጀው፥ የምግብ ወጪ በሚታሰብበትና የምግብ ወጪ በማይታሰብበት ቦታ ሲኖሩ መጠኑ ይለያያል ማለት ነው። ከትዳር ጓደኛ ወይም ከኑሮ ጓደኛ ጋር አብሮ መኖር የቀን አበልዎ መጠን ላይ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል።

መኖሪያ ከምግብ ጋር የሚሰጥበት የዕለት ወጪ ድጋፍ፡-

  • 24 ክሮ/ለብቻቸው ለሚኖሩ ጎልማሶች
  • ከኑሮ ጓደኛ ጋር ለሚኖር አንድ አዋቂ ሰው በቀን 19 ክሮኖር
  • ከወላጆቹ ጋር ለሚኖር 18 – 19 ዕድሜ ያለ ወጣት በቀን 19 ክሮኖር
  • 12 ክሮ/17 እና ከዚያ በታች ዕድሜ ላላቸው ህጻናት

ምግብ አብሮ ከመኖሪያ ጋር የማይሰጥበት የዕለት ወጪ

  • 71 ክሮ/ለብቻቸው ለሚኖሩ ጎልማሶች
  • ከኑሮ ጓደኛ ጋር ለሚኖር አንድ አዋቂ ሰው በቀን 61 ክሮኖር
  • ከወላጆቹ ጋር ለሚኖር 18 – 19 ዕድሜ ያለ ወጣት በቀን 61 ክሮኖር
  • 37 ክሮ/ከ 0–3 ዓመት ለሆኑ ህጻናት
  • 43 ክሮ/ከ 4–10 ዓመት ለሆኑ ህጻናት
  • 50 ክሮ/ከ 11–17 ዓመት ለሆኑ ህጻናት

ከሁለት ልጆች በላይ ያላቸው ቤተሰቦች ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ልጆች የየዕለቱን የወጪ ድጋፍ የሚያገኙ ሲሆን ለተቀሩት ልጆች ደግሞ የየዕለቱን የወጪ ሽፋን ግማሹን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

ከምግብ ውጪ የዕለት ወጪው ድጋፍ ለልብስ፣ ለጫማ፣ ለጤና ክብካቤ እና መድሃኒት፣ የጥርስ ክብካቤ፣ የመጸዳጃ ቤት ግብዓቶች፣ ሌላ ሸቀጣ ሸቀቶች እና ለመዝናኛ የሚሆኑ ወጪዎችን የሚሸፍን መቻል አለበት፡፡

የዕለት ወጪው የሚከተሉትን ከሆናችሁ ሊቀነስ ይችላል

  • ማንነተህን ለመግለጽ ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ
  • ራስን በመሰወር ለጥገኝነት የሚደረገውን ምርመራ የምታጓትት ከሆነ
  • ማመልከቻህ ተቀባይነት ካላገኘ ወይንም ወደ ሀገርህ እንድትመለስ ተወስኖ አንተን ለመመለስ በሚደረገው ስራ ላይ የማትተባበር ከሆነ

የመኖሪያ ሰፈርዎን፥ የማህበረ ኤኮኖሚ ተግዳሮት አለባቸው ወደ ሚባሉ አካባቢዎች የሚቀይሩ ከሆነ፥ የቀን አበል የማግኘት መብትዎን ሊነፈጉ ይችላሉ። የቀን አበል እና ልዩ ድጎማ የማግኘት መብትዎን ሊያሳጣዎት የሚችለው ሌላ ምክንያት ደግሞ የሚኖሩበትን ትክክለኛ አድራሻ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያላሳወቁ ከሆነ ነው። ለምሳሌ የፖስታ ሳጥን ቁጥር አድራሻ መስጠት።

በግልዎ በሚያዘጋጁት መኖሪያ ስለመቀመጥ እና ቤት የሚቀዩሩበት ሰፈር አድራሻ የቀን አበል የሚነካ መሆኑንና አለመሆኑን እዚህ ይፈትሹ

የቀን አበል መጠየቂያ ቅጽ (Mot23) (በስዊድሽኛ ቋንቋ) Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

የአበል ቅጹን በሚከተለው መልክ መሙላት ይችላሉ፣

የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስገኘው መብት ይነሳል

የመኖሪያ ፈቃድዎን በሚያገኙበት ወቅት የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስገኝልዎትን መብት ያጣሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በሚያዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራ እያሉ አንድ ኮምዩን ሲቀበልዎት፤ እንደ ደንቡ ከሆነ ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ሲሰጥዎት የነበረውን ድጎማ አያገኙም። በግልዎ ባዘጋጁት መኖሪያ ቦታ የሚቀመጡ ከሆነ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎን ካገኙ ከአንድ ወር በኋላ ድጎማ የማግኘት መብትዎ ይነሳል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ ሊነሳ የሚችለው፣ ማመልከቻዎ ውድቅ ሆኖ አገር ለቅቀው እንዲሄዱ ተወስኖ ወይም ከአገር እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላልፎ፥ ውሳኔው የሚጸናበት ግዜ ሲጀምር ወይም በራስዎ ፈቃድ ከአገር እንዲወጡ ታዝዘው የተሰጥዎት የግዜ ገደብ ሲያበቃ ነው። ይህ ደንብ የሚመለከተው ከ18 ዓመት በታች የሆነ፥ በአሳዳጊነት ወይም በሞግዚትነት አብሮ የሚኖር ልጅ የሌላቸውን አዋቂዎች ነው። የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ አገሪቱን ለቅቀው ሲወጡም ይነሳል።

ልጆች ያሉት ቤተ-ሰብ ስዊድንን ለቀው እስኪ ወጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከመስተንግዶ ክፍላችን መዝገብ እስኪሰረዙ ድረስ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ባዘጋጀላቸው የመኖሪያ ሰፈር ኑሯቸውን መቀጠል ይችላሉ።

ልዩ አበል

በዕለት ወጪ ድጋፍ ሊሸፈን ያልቻለ ከፍተኛ ፍላጎት ካለህ ልዩ አበል እንዲሰጥህ ማመልከት ትችላለህ፡፡  ስለፈለከው ዕቃ ወይንም የአገልግሎት ዓይነት ያደረብህን ፍላጎት ማረጋገጥ የሚኖርብህ ሲሆን መክፈል አለመቻልህንም ማስረዳት አለብህ፡፡ ለምሳሌ መነጽር፣ ህጻን ማቀፊያ ወይን የሚሞቅ የክረምት ጫማ፡፡ የስደተኞች ቦርድ ለፍላጎትህ የግል ምዘና ያደርጋል፡፡

ፍላጎትህን ለማሟላት ከሚሆንህ ዕቃ ውስጥ ልታገኘው የምትችለው በዋጋው ርካሽ የሆነውን ብቻ ነው፡፡

ልዩ ድጎማ የማግኘት መብትዎ የሚነካበት አንዱ አጋጣሚ፥ በግልዎ ፈልገው የሚቀይሩበት መኖሪያ ቤት የማህበር ኢኮኖሚ ተግዳሮት እንዳለባቸው ያመለከቱ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ነው።

ወደ ስደተኞች ቦርድ እንድትመጣ ስትፈለግ ለምሳሌ - ስለ ጥገኝነት ጥያቄህ ለማጣራት፣ ከተቀበለህ የአስተዳደር ሰራተኛ ጋር ለመገናኘት ወይንም በቡድን በሚካሄዱ ኩነቶች ላይ እንድትሳተፍ ሲፈለግ የጉዞ አበል የምታገኝ ይሆናል፡፡ ከምታገኘውን የአስተዳደር ሰራተኛ  ጋር ስለዚህ ጉዳይ ተነጋገር፡፡

ለጎልማሶች የሚሆን የማመልከቻ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር  Mot78 Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

ጎልማሶች ለልዩ አበል ቅጽ የሚሞሉት እንደዚህ ነው (በእንግሊዝኛ)

ከጎናቸው ማም ለሌለ ህጻናት እና ወጣቶች የሚሆን የማመልከቻ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር Mot72 Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

የመኖሪያ ቤት ወጪ ድጋፍ

ስራ ካገኘህ ወይንም ስራ የሚሰጥህ ሰው ካገኘህ ለመኖሪያ ቤት ወጪ ማመልከት ትችላለህ፡፡ ይህ ማለት ያገኘኸው ስራ ከሶስት ወር የቅጥር ጊዜ የሚበልጥ ከሆነ እና የምትሄድበት ቦታ ላይ የስደተኞች ቦርድ ሊሰጥህ የሚችለው መኖሪያ ቤት ከሌለ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ወጪ ድጋፍ -

  • 850 ክሮ/ለቤተሰዎች በወር
  • 350 ክሮ/ለአንድ ሰው በወር

ስለ ገንዘብ ድጋፍ ያለ ውሳኔ

የስደተኞች ቦርድ ስለ ገንዘብ ድጋፍ ውሳኔ ሲሰጥ ስለ ውሳኔው እናሳውቅሃለን፡፡

  • በተቀበለህ የአስተዳደር ሰራተኛ በኩል
  • በተለምዶ ቀላል ማሳወቂያ በሚባለው በኩል

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን በደብዳቤ የማሳወቅ መላ በመጠቀም፣ ወሳኔውን እርስዎ ቀድም ብለው በሰጡን የመኖሪያ አድራሻዎ በኩል በፖስታ እንዲደርስዎት ያደርጋል። በሚቀጥለው የሥራ ቀን ደግሞ፣ የውስኔው ሰነድ እርስዎ ጋር መድረሱን ለማጣራት፣ ሌላ አዲስ መቆጣጠሪያ መልዕክት እንልካለን። በዚህ መቆጣጠሪያ መልዕክት ላይ ውሳኔው የተላለፈበት ዕለት በውል ሰፍሮ ይገኛል። ውሳኔው ወደ እርሶ ከተላከ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔው ደርስዎታል ብሎ ይደመድማል። ከዚያ በኃለ ይግባኝ ለማለት ሶስት ሳምንት አለዎት፡፡

የሰጡንን አድራሻ ልንጠቀምበት ካልቻልን እና ስዊድን ውስጥ የተመዘገቡ ከሆነ የውሳኔውን ደብደቤ እና የቁጥጥር ደብዳቤውን መጀመሪያ ተመዝግበው ወደነበረበት አድራሻ እንልካለን፡፡

በተጨማሪም የፖስታ ሳጥኖን ሁል ጊዜ ማየቱን አይርሱ፡፡

የባንክ ካርድ

ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የቀን አበል እንዲያገኙ ከተፈቀደልዎት፥ ገንዘቡ ከሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ ጋር የተገናኘ አንድ የባንክ ካርድ ይሰጥዎታል።

ለራስዎ የ”ቀን-ድጎማ” (dagersättning) ለመጠቀም፥ የራስዎ የሆነ “የባንክ-ካርድ” (bankkort) እንዲኖሮት መብት ኣልዎት፥ በቤተሰባችሁ ውስጥ ብዙ ኣዋቂዎች የምትኖሩ ቢሆንም።

ስለ ጥገኝነት-ጠያቂዎች የባንክ-ካርድ እዚህ በይበልጥ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ይግባኝ መጠየቅ ከፈለግህ

ያንተን የወጪ ድጋፍ በተመለከተ የስደተኞች ቦርድ ስህተት ሰርቷል ብለህ ካሰብክ ውሳኔውን አስመልክቶ ይግባኝ መጠየቅ ትችላለህ፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉዳይ ሲገጥምህ የይግባኝ ጥያቄህን ውሳኔውን ከሰማህ (ካሳወቁህ) በኋላ ባሉ የሶስት ሳምንት ጊዜያት ውስጥ ወደ ስደተኞች ቦርድ ይዘህ መቅረብ ይኖርብሃል፡፡ የስደተኞች ቦርድ የይግባኝ ጥያቄህን ተመልክቶ ውሳኔውን ካልቀየረ የይግባኝ ጥያቄህ ጉዳይህን በድጋሚ ሊመለከት ወደሚችል የህግ የፍርድ ቤት አስተዳደር ያስተላልፈዋል፡፡ የህግ የፍርድ ቤት አስተዳደር የይግባኝ ጥያቄህን ውድቅ ካደረገው ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት (kammarrätten) ማመልከት ትችላለህ፡፡

የይግባኝ ጥያቄ የምታቀርብ ከሆነ ማድረግ ስላለብህ ነገሮች በደንብ አንብብ

ስለ ዕለት ወጪህ ድጋፍ ወይም ሌሎች አበሎችን በተመለከተ ጥያቄ ካለህ

ለጥገኝነት ፈላጊዎች የሚደረገውን የገንዘብ ድጋፍ በተመለከተ አጠቃላይ ጥያቄ ካለህ ወደ ስደተኞች ቦርድ መደወል ትችላለህ፡፡ ጥያቄህ ግን የራስህን የወጪ ድጋፍ በተመለከተ ከሆነ ወደ ተቋሙ መምጣት ይኖርብሃል፡፡ የስደተኞች ቦርድ ሰራተኞች ስለ ህጎቹ ሚስጥራዊነት ሲባል ይሄንን በስልክ ማውራት አይችሉም፡፡ ወደ ተቋሙ ስትሄድ የ LMA ካርድህን ይዘህ ሂድ፡፡

Last updated: