የቀን አበል መጠየቂያ ቅጽ አሞላል መመሪያ

Instruk­tioner till ansökan om dager­sätt­ning – amhariska

የቀን አበል ለመጠየቅ (Mot23) የሚባለውን የማመልከቻ ቅፅ ሲሞሉ የሚከተሉት መመሪያ። ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑና የቀን አበል መጠየቅ ሲሹ ይህን ቅፅ ይጠቀሙ።

1. የማንነት መረጃ

በማመልከቻው ቅጽ ላይ ማንነትዎን እና የሚገኙበትን አድራሻ የሚገልጽ መረጃ ያስፍሩ። በዚህ ማመልከቻ ላይ ስም ከነአባት፣ አድራሻዎን፥ የተወለዱበትን ዕለት፥ ፆታዎን፥ ዜግነትዎንና ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የተሰጥዎትን የዶሴ ቁጥር ያስፍሩ።

2. ሃብትና ንብረት ማሳወቅ

ገቢ፡- ከቅጥር የሚያገኙት ደሞዝ ካለ እንዲሁም ከተለያዩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች የሚሰጥዎት፣ ለምሳሌ ከፎሸክኒግካሳ (Försäkringskassan) የሚሰጥ እንደ የታማሚ ድጎማ፥ የወላጅ ድጎማ፥ የልጅ ድጎማ የመሳሰሉትን ይወስዱ እንድሆን ይግለጹ።

ጥሬ ገንዝብ፡- ጥሬ ገንዘብ ካለዎት ይግለጹ። መጠኑንም በቅጹ ያስፍሩ።

ሃብትና ንብረት፡- ሃብትና ንብረት ያለዎት ከሆነ ይግለጹ፣ ለምሳሌ መኪና፥ ስዊድን ውስጥ ወይም በውጭ አገር ባንክ ያስቀመጡት ገንዘብና ንብረት፥ የግል ድርጅት፥ አክሲዮን ወይም በውጭ አገር የሚገኝ፥ ተሽጦ ጥሬ ገንዘብ የሚያስገኝ ንብረት ካለዎት ይግለጹ።

3. ማመልከቻው ላይ ይፈርሙ።

ማመልከቻው ላይ ፊርማዎን በማኖርዎ የሚከተሉትን ነጥቦች ያረጋግጣሉ፡-

  • በማመልከቻው ላይ ያሰፈሩት ሁሉ ለሰብዐዊ ክብርዎና ለህሊናዎ ሲሉ ትክክለኛና ዕውነት መሆኑን፥
  • በማመልከቻው ላይ ያሰፈሩት መረጃዎችና የሚሰጥዎትን የኢኮኖሚ ድጎማ የሚለውጡ ሌሎች ሁኔታዎች በሚከሰቱበት ወቅት ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የማሳወቅ ግዴታ ያለብዎት መሆኑን፣ እንደተገነዘቡና የአድራሻ ለውጥ ሲያደርጉ ማሳወቅ አንዳለብዎት፣
  • የተሳሳተ መረጃ መስጠት ድጎማ የማጭበርበ ወንጀል (bidragsbrott) መሆኑና ወደ ፖሊስ የሚያስከስሶት መሆኑን እንደተገነዘቡ፥
  • የፈረሙበትን የማመልከቻ ሰነድ በሚገባ የተረዱት መሆኑን ነው ያረጋገጡት።

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ተጨማሪ መረጃ ሳያስፈልገው፥ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ማመልከቻውን ከወዲሁ በተሟላ መልኩ መሙላት አስፈላጊ ነው። የሰጡት መረጃ ያልተሟላ ከሆነ፥ የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማመልከቻውን እንዲያሟሉ ይጠይቅዎታል፥ ይህ በተራው ውሳኔ ሊሰጠበት የሚችልበትን ግዜ ያራዝመዋል ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት፣ ማመለከቻው ውሳኔ ሊሰጥበት የሚያስችል አይደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ጉዳዩን ሊሰርዘውም ይችላል።

ማመልከቻውን የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት (mottagningsenhet) ድረስ ሄደው መስጠት ወይም በፖስታ መላክ ይችላሉ።

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ባለጉዳይ ማስተናገጃዎች አድራሻ (በስዊድሽኛ ቋንቋ)

Last updated: