መኖርያ ቤትህ በስደተኞች ጽ/ቤት ስር ይሁን

Bo hos Migrationsverket – amhariska

መረጃው ላንተው ጥገኝነት የምትፈልግና የጥያቄህ ውሳኔ በመጠባበቅ እያለህ የስደተኞች ጽ/ቤት ንብረት በሆነው ቤት ለመኖር የምትሻ የተዘጋጀ ነው።

የሚሰጠውን ውሳኔ በሚጠብቁበት ጊዜ የስደተኞች ኤጀንስ ጊዜያዊ መጠለያ ይሰጥዎታል።

ገንዘብ ከሌለህ የመኖርያ ቤቱ ክፍያ የስደተኞች ጽ/ቤት ነው የሚፈጽመው፡ ነገር ግን ገቢ ወይም ሌላ የገንዘብ ምንጭ ካለህ የመኖርያ ቤቱ ክፍያ ራስህ ነው የምትከፍለው፡ መኖርያ ቤቱ ምግብ ጨምሮ የሚያስከፍል ከሆነ ደግሞ፡ ለምግቡ ትከፍላለህ። 

ቦታ በተገኘበት ኣካባቢ ነው የምትኖረው

የምትኖርበትን ቦታ ራስህ መምረጥ ኣትችልም፡ ነጻ መኖርያ ቤት በሚገኝበት ቦታ ነው መዛወር ያለብህ። ኣንዳንድ ግዜ የጥያቄህ ውሳኔ ብመጠባበቅ እያለህ ወደ ሌላ ቦታ እንድትጓዝ ትገደዳለህ፡ ይህን የሚሆንበት ምክንያት በብዛት ለሚመጡ ጥገኝነት ፈላጊዎች ቦታ ለመተው ነው።

ቤትን ተካፍሎ መኖር

በስደተኞች ጽ/ቤት ስር የሚተዳደሩ ቤቶች ለጥገኝነት ፈላጊዎች ብቻ ነው። በቤቱ ውስጥ ኣንድ ክፍል የተሰጠህ ሲሆን ክፍሉ ያንተ ነው። መኖርያ ቤቱ ኣፓርትማ ሆኖ ሌሎች ሰዎች ተካፍለው የሚኖሩበት ነው። ቤተሰብ ከሆኑ የግል ቤት ይሰጣቸዋል። ወንድላጤ ከሆነ ግን ክፍሉ ከሌሎች ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ሰዎች ተካፍሎ መኖር ይኖርበታል። 

ባንዳንድ ምክንያት ለየት ያለ ክፍል እንዲሰጥህ ከፈልግክ በመቀበያ ጽ/ቤት ካሉት ሰዎች ጋር ተነጋገር።

ልዩ የሆነ አስፈላጊነት ካለዎት

ለተለየ ችግር የተጋለጡበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፥ ለእርስዎ የሚስማማ የመኖሪያ ቦታ የማግኘት መብት ሊኖርዎት ይችላል። የመኖሪያ ሁኔታን በተመለከተ፥ አስቸኳይና ልዩ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ካሉ፥ በተቻለ ፍጥነት የማስተናገጃውን ጽ/ ቤት (mottagningsenhet) ያነጋግሩ። ለርስዎ የሚስማማና የተሻለ ሁኔታ የሚያመጣ መፍትኄ ለማግኘት የተቻለንን እናደርጋለን።

የተመላሽ ማቆያ ማዕከል

ከስዊድን የመባረር ወይም አገር ለቅቃችሁ እንድትወጡ የተወሰነባችሁ፣ ውሳኔው ከሚጸናበት ዕለት ጀምሮ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ባዘጋጀው የተመላሽ ማቆያ ማዕከል (återvändandecenter) ውስጥ ቦታ እንድታገኙ ግብዣ ይደረግላችኋል። ይህ ግብዣ ደረሳችሁ ማለት ከእንግዲህ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ሌላ የመኖሪያ ሥፍራ አያዘጋጅላችሁም ማለት እንደሆነ መረዳት ይኖርባችኋል። ”የተመላሽ ማቆያ ማዕከል” የሚባለው ሥፍራ በዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያዎች አጠገብ የሚገኝ ማረፊያ ቦታ ነው።

ጥገኝነት ጠያቂዎች ስዊድንን ለቅቃችሁ እስክትወጡ ወይም የኢኮኖሚ ድጋፍና መኖሪያ ሥፍራ የማግኘት መብታችሁ እስኪነሳ በተመላሽ ማቆያ ማዕከል ውስጥ ታርፋላችሁ። በተመላሽ ማቆያ ማዕከል ውስጥ በሚያርፉበት ወቅት፥ ወደ ትውልድ አገራችሁ የመመለስ ዝግጅታችሁን የሚመለከት ምክርና ድጋፍ ይሰጣችኋል።

ለሌሎች ነዋሪዎች አክብሮት መስጠት

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት፡ ሁሉም ነዋሪዎች ደኅንነት እንዲሰማቸው ይሻል። ስለሆነም ጽ/ቤቱ በሚያስተዳድራቸው መኖሪያዎች ሁሉ፡ ማንኛውም ዓይነት አልኮልና ናርኮቲክ የተከለከሉ ናቸው። ሁሉም ነዋሪዎች፥ ሃይማኖት፥ ባህል፥ ወሲባዊ ዝንባሌ ሆነ ጾታ ሳይለያቸው እርስ በርስ መከባበርና መተሳሰብ ይኖርባቸዋል።

ማንኛውም ዓይነት የሃይል አመጻ የተከለከለ ሲሆን፥ በስዊድን ሕግ መሰረት ቅጣት ያስከትላል። ስለሆነም የሃይል አመጻ ከተከሰተ ለፖሊስ እናመለክታለን። ይህ ከውጭ ያሉትን ብቻ ሳይሆን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉትንም ይመለከታል። ልጅን ለማረም ሆነ ሌላ የቤተሰብ አባልን ለመገሰጽ ዱላ መጠቀም የተከለከለ ነው።

ለሆነ ዛቻ፥ ዱላ ወይም ለሌላ የመብት መደፈር ተጋልጠው ከሆነ ከመኖሪያ አስተዳደሩ ሰራተኞች ጋር ወይም የማስተናጋጃው ጽ/ቤት ጋር ይነጋገሩ። በአካባቢዎ ከሚገኙ ነጻ ድርጅቶችም (frivilligorganisationer) ጋር መነጋገር ይችላሉ። ወንጀል የሚያመለክቱ ከሆነ በቴሌፎን ቁጥር 114 14 ይደውሉ። አስቸኳይ አደጋገኛ ከሆነ ደግሞ 112 ይደውሉ።

የሴቶች ከለላ መስመር (Kvinnofridslinjen) ዛቻ፡ አካላዊ፡ ሰነልቦናዊ ወይም ወሲባዊ ጥቃት ለደረሳባችሁ ምክርና ድጋፍ ይሰጣል። ይህን ቁጥር 020‑50 50 50 ይደውሉ። የበለጠ ለማንበብ kvinnofridslinjen.se ይጎብኙ።

የድጋፍ ስልክ መስመር ለወንዶች፡- አካላዊ፣ አዕምሯዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባችው ወንዶች፥ ምክርና ድጋፍ የሚያገኙበትን ዕድል አዘጋጅቷል፣ በዚህ ስልክ ቁጥር፣ 020‑80 80 80 ደውሉ። የበለጠ ለማንበብ stodlinjenforman.se ይጎብኙ።

የድጋፍ ስልክ መስመር ለትራንሶች፡- አካላዊ፣ አዕምሯዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባችው ትራንሶች ምክርና ድጋፍ የሚያገኙበትን ዕድል አዘጋጅቷል፣ በዚህ ስልክ ቁጥር፣ 020‑55 00 00 ይደውሉ።

የቤት ዕቃና ቁሳቁስ

መኖሪያ ቤቱ፡ የቤት ዕቃዎችና አስፈላጊ ቁሳቁሶች አሉት። ቤቱ፡ የቤት ዕቃውና ቁሳቁሶቹ የስደተኞች ጽ/ቤት ንብረት ናቸው። ስለዚህ በነዚህ ንብረቶች ላይ ጉዳት ማድረስ ሊያስከስስ ይችላል። በሚኖሩበት ቤት ውስጥ የተሰበረ ነገር ወይም የማይሰራ ነገር ካለ በቶሎ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞችን መገናኘትና መንገር ያስፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች መኖሪያ ቤቱ ድረስ መጥተው በመጎብኘት መታደስ የሚገባቸው ነገሮችን ይመለክታሉ።

የግልዎ ንብረቶች

በህንፃው ውስጥ ያሉት መጋዘኖችም ሆኑ ክፍት ቦታዎች፥ ከሚኖሩበት ቤት ጋር የተካተቱ አይደሉም። ዕቃዎችዎን የሚያስቀምጡበት ሳጥን ከነመቆለፊያው ይኖርዋታል፥ ይሁን እንጅ፡ ለዕቃዎችዎ ደህንነት ሃላፊነት የሚወስዱት እርስዎ ብቻ ነዎት። በቤቱ ውስጥ ነዋሪ እስከሆኑ ድረስ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች ሳጥንዎን አይከፍቱም።

የጋራ ቦታ

ሁሉም እንዲመቸውና ለሁሉም እንዲስማማ፥ የጋራ የሆኑ ቦታዎችን እንዴት እንደምትጠቀሙባቸው የሚያስረዱ ደንቦች አሉ። ወደ መኖሪያው ቦታ ሲመጡ፥ መከተል የሚገባዎትን ደንብ በተመለከተ የበለጠ መረጃዎች ያገኛሉ።

በሁሉም መኖሪያ ቦታዎች የሚከተሉት ደንቦች ይከበራሉ:-

  • ንጽህና መጠበቅና ማጽዳት
  • በህንፃው ውስጥ አለማጨስ
  • ለቤት ዕቃዎችና ቁሳቁሶች ጥንቃቄ ማድረግ
  • የቤት እንሰሳ አለማስከተል የሚሉ ናቸው።

የደህንነት ጥንቃቄ

ማስተዋል ያለብዎት፥

  • በራስዎ የኤሌክትሪክ ጥገና ለማድረግ ወይም የኤሌክትሪክ ማውጫውን ለመቀየር መሞከር በሕይወት ላይ አደጋ የሚያስከትል ስለሆነ ክልክል ነው።
  • የሆነ ነገር ሲበላሽ ለመኖሪያ ቤቱ ሰራተኞች ይንገሩ
  • የውጩን በር መተላለፊያ ወይም የአደጋ ጊዜ መውጫው፥ በእሳት አደጋ ወቅት ቶሎ ለማምለጥ እንዲቻል መዘጋት የለባቸውም፥
  • ዲሽ መትከል ሁሌ የሚፈቀድ ስላልሆነ፥ የእርስዎን ቤት በተመለከተ እንዴት እንደሆነ ለማዋቅ ሁሌ ሰራተኞችን ይጠይቁ።

ስለ አካባቢዎ ያስቡ

ከእርስዎ ጋር በመሆን፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ለአካባቢው ድሕንነትና መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽዖ ማድረግ ይሻል። ስለዚህ የሚከተሉትን ጉዳዩች ያስተውሉ፥

  • ውሃ፡ ኤሌክትሪክና ሙቀት መስጫውን ሳያባክኑ በአግባቡ ይጠቀሙበት።
  • ውጩ ቀዘቃዛ በሚሆንበት ጊዜ፥ መስኮቱን ለረጅም ጊዜ ክፍቱን አይተውት። (ብዙ ኤሌክትሪክና ሙቀት ያባክናልና)
  • የሚጥሉትን ተረፍና አሮጌ ነገሮች በስነ ሥርዓት ያደላድሉ። ተረፍና አሮጌ ነገሮች በተዘጋጀላቸው ልዩ ማጠራቀሚያ ነው የሚጣሉት። በሚኖሩበት ህንፃ ያለውን የቁሻሻ አጣጣል ተጨማሪ መረጃ መኖሪያውን ከሚያስተዳድሩት የጽ/ቤታችን ሰራተኞች ወይም ከባለ ንብረቱ ያገኛሉ።

ቤቱን ለቀው ሲወጡ ወይም ወደ ሌላ ቦታ ሲቀይሩ

ከእርሶ ቀጥሎ ለሚገባው ሰው ሁሉም ነገር በቦታው መኖሩንና በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱን ለማረጋገጥ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች መጥተው ቤቱንና የቤቱን ዕቃዎች እንዲሁም ቁሳቁሶቹን ይቆጣጠራሉ።

ስለዚህ የሚከተሉትን ማድረግ አይዘንጉ:-

  • የሚለቁትን ክፍል ያጽዱ
  • የግልዎ የሆኑትን ዕቃዎች ይዘው ይሂዱ። አንዴ ከወጡ በኋላ ወይም ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት መዝገብ ውስጥ ከወጡ በኋላ፥ ትተውት የሚሄዱትን ዕቃ ተመልሰው የማግኘት ዕድል ላይኖር ይችላል። ትተውት የሄዱት፥ ወይም ረስተውት የሄዱት ዕቃ ሊጣል፥ ወይም ሊለገስ ወይም ወድቆ እንደተገኘ ዕቃ ተቆጥሮ ለፖሊስ ሊሰጥ ይችላል።
  • ቁልፎችን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞች ያስረክቡ።
  • መኖሪያ ቦታ የሚቀይሩ ከሆነ፡ የሚጓጓዙት በአውቶቡስ ወይም በባቡር ነው የሚሆነው። ስለሆነም የጓዝ መጠን የተወሰነ ነው። ከጽ/ቤታችን መኖሪያ ወደ ሌላ በሚቀይሩበት ወቅት፥ የሚሸክፉት ጓዝ መጠንን በተመለከተ ስላለው ሁኔታ ለማወቅ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሰራተኞችን ያነጋግሩ። ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የመኖሪያ ቦታ የሚያዘጋጅሎት ጥገኝነት ጠያቂ እስከሆኑ ድረስ ብቻ ነው። የመኖሪያ ፈቃድዎን በሚመለከት አንድ ውሳኔ ሲሰጥዎ፥ በመኖሪያው የመቆየት መብትዎ የሚያበቃበት ሁኔታን ያስከትላል።

በመኖሪያው የመቆየት መብትዎ ሊያበቃ ይችላል

የጥገኝነት ጥያቄዎን ውጤት በሚጠብቁበት ወቅት የስድተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ባዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራ እንዲቆዩ ይጋብዛል። የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄዎ አንድ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ግን፥ በዚያ መኖሪያ ሥፍራ የመቆየት መብትዎ ያበቃል፣ ወይም ወደ ተመላሽ ማቆያ ማዕከል መሄድ ይኖርብዎታል።

የጥገኝነት ጥያቄዎ ውድቅ ሲሆን በመካያው ምን እንደሚከተል ለማወቅ የበለጠ ያንብቡ! (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመኖሪያ ፈቃድ ሲያገኙ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ ቤት በሚያዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራ ስትቀመጡ የነበራችሁ፥ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጣችሁ፥ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” አዲስ የመኖሪያ ቦታ እንዲኖራችሁ የበኩሉን ድጋፍ ያደርግላችኋል። አዲስ የመኖሪያ ቦያ እስክናገኝላችሁ ድረስም፥ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” ባዘጋጀላችሁ የመኖሪያ ቦታ መቆየት ትችላላችሁ። አዲስ ቤት አግኝተንላችሁ፥ ያንን ቤት አንፈልግም የምትሉ ከሆነ ግን፥ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” ባዘጋጀው መኖሪያ ቦታ በቀጣይነት የመቀመጥ መብት አይኖራችሁም።

ግዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ በምታገኝበት ግዜ ስለሚሆነው ለማወቅ ተጨማሪ እዚህ አንብቡ።

Last updated: