ለጥገኝነት ጥያቄ እንዴት ማመልከት ይቻላል

Så här ansöker du om asyl – amhariska

በስዊድን የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ከፈለጉ ማመልከቻዎትን ለማስገባት ወደ ስደተኞች ኤጄንሲ መሄድ ይኖርብዎታል። ወደ ስዊድን ሳይመጡ በፊት ጥገኝነት መጠየቅ አይቻልም።

ወደ ስዊድን በሚገቡበት ጊዜ ድንበር ለሚጠብቅ ፖሊስ ለጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚፈልጉ ሊነግሩት ይገባል። ለምሳሌ ያህል የዓለም አቀፍ በረራ በሚደረግባቸው የአውሮፒላን ማረፊያዎች በፓስፖርት መቆጣጠሪያው ላይ፣ በመርከብ ማቆሚያዎች እና ባቡሮች እና አውቶብሶች ወደ ስዊድን በሚገቡበት መግቢያ ላይ  የድንበር ጠባቂ ፖሊስ አለ። የድንበር ጠባቂ ፖሊስ አንዳንድ ጥያቄዎችን ይጠይቅዎት እና የጥገኝነት ማመልከቻዎትን ወደ ሚያቀርቡበት የስደተኞች ኤጄንሲ ይልክዎታል።

ስዊድን አገር ድሮ ገብተው እንደሆነ፥ ራስዎ ከሚግራሾንስቨርከት ጋር ግንኙነት ማድረግ ይኖርብዎታል። ጥገኝነት የመጠየቂያ ማመልከቻዎ፥ ከሚቀጥሉት የሚግራሾንስቨርከት የማመልከቻ መቀበያ ቦታዎች አንዱ፥ ቡደን፡ ፍሌን፡ ዮተቦርይ ወይም ስቶክሆልም፡ ማቅረብ ይችላሉ። ያለ አሳዳጊ ብቻቸው የመጡ ልጆች፥ በኖርሾፒንግ ማመልከቻ መቀበያ ቦታ፥ ማመልከቻ ማግባት ይችላሉ።

ለጥገኝነት ማመልከቻ የስደተኞች ኤጄንሲ ክፍሎችን የት ማግኘት እንደሚችሉ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የስደተኞች ኤጄንሲ የእርስዎን ማመልከቻ ይመዘግባል

ለጥገኝነት በሚያመለክቱበት ጊዜ ማን እንደሆኑ፣ ለምን ለጥገኝነት ማመልከት እንደፈለጉ እና ወደ ስዊድን እንዴት ተጉዘው እንደመጡ መግለጽ አለብዎት።

ማንነትዎን መግለጽ አለብዎት

ፓስፖርት ወይም ማንኛውም ሌላ የመታወቂያ ሰነድ ካለዎት ማንነትዎን፤ ስምዎ ማን እንደሆነ፣ መቼ እንደተወለዱ እና የየት አገር ዜጋ እንደሆኑ ለማሳወቅ ማቅረብ አለብዎት። የስደተኞች ኤጄንሲ ትክክለኛውን ውሳኔ ማሳለፍ እንዲችል የእርስዎን ማንነት ማሳየት አስፈላጊ ነው።

ማንነትዎን ማሳየት የሚችል ማንኛውም አይነት ሰነዶችን ማቅረብ ካልቻሉ በሌላ መንገድ እርስዎ ማንነትዎንለማረጋገጥ መሞክር አለብዎት። ለምሳሌ ማድረግ የሚችሉት የልደትዎን ሰርቴፊኬት፣ የቤተሰብ ወይም የውትድርና ምዝገባ ሰነዶችን ወይም የጋብቻ ሰርቴፊኬት ማቅረብ ይችላሉ። እንደዚያ ዓይነት ዶክመንቶች በግላቸው የራስዎትን ማንነት ማረጋገጥ አይችሉም፤  ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በርካታ ዶክመንቶች በአንድነት ማንነትዎን ለማረጋገጥ ተቀባይነት ይገኛሉ።

ለምን ማንነትዎን መግለጽ እንዳለብዎት ለመረዳት የበለጠ ያንብቡ፥

የስደተኞች እጄንሲ ስም እና የእርስዎን ማንነት እንዲያሳዩ የቀረቡትን ሰነዶች ላይ ያሉትን መረጃዎች  በመጠቀም እንደ ጥገኝነት ፈላጊ ይመዘግብዎታል። ይህም ማለት፣ ለምሳሌ፣ ጾታ ያስቀየሩ ሰዎች በተወለዱበት ጊዜ የነበራቸውን ስም እና ጾታ ይዘው  ይመዘገባሉ ማለት ነው። እንደ አጋጣሚ ሆኖ፣ የስዊድን ሕግ በማንኛውም በሌላ ስም እርስዎን ለመመዝገብ አይፈቅድልንም፤ ነገር ግን ሌላ የመጠሪያ ስም ወይም ሊነግሩን የሚፈልጉት የግል ቅፅል ስም  መጠቀም ከፈለጉ፣  በማስታወሻ እንይዘዋለን። ተርጓሚ፣ በጾታ የተወሰነ አማካሪ ወይም መርማሪ የሚፈልጉበት የተለየ ምክንያት ካለ፣ እና ከሌሎች የጥገኝነት ፈላጊዎች በተለይም ከተወሰነ ጾታ ጋር በአንድ ክፍል መኖር የማይፈልጉ ከሆነ በዚህ ደረጃ ላይ እያሉ ቢነግሩን መልካም ይሆናል።

ፎቶ ይነሳሉ እንዲሁም የጣትዎን አሻራ ይሰጣሉ

ለጥገኝነት በሚያመለክቱበት ጊዜ ፎቶ ይነሳሉ እንዲሁም የጣት አሻራዎ ይወሰዳል። የእርስዎ ፎቶ በስደተኞች ኤጄንሲ መዝገብ ላይ የሚጨመር ሲሆን የጥገኝነት ፈላጊ መሆንዎትን እንዲገልጽ ለሚሰጥዎት የጥገኝነት ፈላጊ ካርድ (LMA-card) ላይ በጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ከስድስት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ልጆች የጣት አሻራቸው አይወሰድም።

የጣት አሻራው በሌላ በየትኛውም የሸንገን አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብዎትን እና አለማቅረብዎትን እና በማንኛውም የሸንገን አገሮች ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳለዎት ወይም እንደተከለከሉ ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ ይውላል። የጣት አሻራው ምርመራ ወደ ስዊድን ሲመጡ በሌላ አገር እንደተመዘገቡ የሚያሳይ ከሆነ፣ ወይም በሌላ አገር የጥገኝነት ጥያቄ እንዳቀረቡ የሚያሳይ  ከሆነ፣ የስደተኞች ኤጄንሲ የትኛው አገር የእርስዎን ጥገኝነት መመርመር እንዳለበት ይወስናል። ይህን በመወሰን፣ አውሮፓ ህብረት/ EU ዱብሊን ሕግ ተግባራዊ ይደረጋል።

ከ14 ዓመት በታች ላሉት ልጆች የጣት አሻራ ምርመራ አይደረግላቸውም።

ስለ ዱብሊን ሕግ የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የማመልከቻ ቃለ መጠይቅ

አንድ ጊዜ ፎቶ ከተነሱ እና የጣት አሻራ ከሰጡ በኋላ ከመርማሪው ጋር ይገናኛሉ። በተርጓሚ እገዛ ማን እንደሆኑ፣ ለምን አገርዎንት ለቀው እንደመጡ እና እንዴት ወደ ስዊድን እንደተጓዙ ይገልጻሉ። ስለ ቤተሰብዎ እና ስለ ጤናዎም ይጠየቃሉ።

ሥራ ለመስራት የማያስችል የአካል ጉዳት ካለብዎት፣ ማለትም በአካላዊ፣ በአእምሮ ወይም በእውቀት ተግባርን ለማከናወን አቅምዎት አንሶ ከሆነ፣ ለስደተኞች ኤጄንስ ይህንን መናገር አለብዎት። ሥራ ለመስራት የማያስችል የአካል ጉዳትዎ ለጥገኝነት በሚያመለክቱበት ጊዜ ከስደተኞች ኤጄንሲ ጋር ለመገናኘት አስቸጋሪ ካደረገብዎት፣ እርዳታ የማግኘት መብት አለዎት። ለፍላጎትዎ የሚስማማ የማግኘትም መብት አለዎት።

ስለ ጥገኝነት ጥያቄ ሂደት- ቀጥሎ ያለው ምን እንደሆነ እና ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ይሰጥዎታል ። ተግባራዊ ስለሚሆኑ ጉዳዮች ማለትም መጠለያ፣ የገንዘብ ድጋፍ፣ የጤና እንክብካቤ እና ለልጆች ትምህርት የማግኘት መብትዎትን ስለሚመለከት መረጃ ያገኛሉ።

ለውሳኔ በሚጠባበቁበት ጊዜ በዋናነት በገንዘብ ራስዎትን ለመርዳት መሞከር አለብዎት። ምንም ዓይነት ገንዘብ የማይከፍልዎት ከሆነ እና ሌሎች ቋሚ ንብረት ከሌለዎት፣ ከስደተኞች ኤጄንሲ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።

ግልጽ ምክንያት የሌለው ማመልከቻ

ጥገኝነትን ለእርስዎ ለመስጠት በግልጽ የሚታይ ምንም ዓይነት ምክንያት ከሌለ፣ መርማሪው የስደተኞች ኤጄንሲ እርስዎ በጥገኝነት ለመቀበል ምንም ዓይነት ምክንያት እንደሌለው ይገልጽና በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ውሳኔው ይተላለፋል። ላቀረቡት የጥገኝነት ጥያቄ ምንም ዓይነት አግባብነት ያለው ምክንያቶች ከሌለዎት ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረግ ወደ አገር ውስጥ መግባትን የሚከለክል ውሳኔ ይሰጥዎታል።

ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረግ ወደ አገር ውስጥ መግባትን ስለሚከለክል ውሳኔ መቀበል ማለት ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ያንብቡ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ማመልከቻዎትን ካስገቡ በኋላ

መርማሪው ሁሉንም ሰነዶች፣ ለስደተኞች ኤጄንሲ የሰጡትን ቃል እና የጣት አሻራዎ ምርመራ ያሳየውን ሁሉ ይመለከታል። መርማሪው እርስዎ የሰጡትን መረጃ መሰረት በማድረግ፣ በእርስዎ ጉዳይ ላይ ምን ያህል ምርመራ እንደሚያስፈልግ ይወስናል። ሁሉም ማመልከቻዎች የተለያዩ ሲሆኑ የተለያዩ የምርመራ መጠንም ይፈልጋሉ።

መርማሪው የእርስዎን ማመልከቻ ቀጣይነት ላለው ምርመራ ያዘጋጃል። ይህም ከሌሎች መንግሥታዊ ከሆኑት ኤጄንሲዎች መረጃዎችን መውሰድን ሊያጠቃልል ይችላል። በማመልከቻዎት ላይ የሚጨመሩ ነገሮችን ማከል ከፈለጉ፣ መርማሪው ያነጋግርዎታል። ለምሳሌ ከማመከክቻዎ ጋር እርስዎን ሊገልጹ የሚችሉ ሰነዶችን ካላቀረቡ፣እንደዚህ ዓይነት ጭማሪዎች፣ ይፈለጋሉ።

የጥገኝነት ምርመራ እስኪጀመር ያለው ጥበቃ

የጥግኝነት ጥያቄዎ ስዊድን ውስጥ የሚወሰን ከሆነ፥ የስደተኛ ጽ/ቤት Migationsverket) የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት መብት ያልዎት መሆንዎን እስኪያጣራ እዚሁ መቆየት ይኖርብዎታል።

የጥገኝነት ጥቃቄዎን በተመለከተ ለምርመራ እስኪቀርቡ ድረስ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ለጥያቄ ሲቀርቡ ግን ለምን ስዊድን አገር ጥገኝነት መጠየቅ እንደፈለጉ፥ ምን እንደደረሰብዎት፥ ወደ አገርዎ ቢመለሱ ምን ሊደርስብዎት እንደሚችል መግለጽ ይኖርብዎታል። የጥበቃ ጊዜው እንድየ ሰዉ የተለያየ ሊሆን ይችላል።

ውሳኔ እስኪያገኙ ብዙ ጊዜ ለጥያቄ ሊጠሩ ይችላሉ። የስደተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤቱ (Migationsverket) በቀጠርዎት ቀንና ሰዓት ይምጡ። የጊዜ እጥረት ስላለብን፥ አዲስ የቀጠሮ ቀን መያዝ ውሳኔ የሚያገኙበትን ጊዜ ሊያራዝምብዎት ይችላል።

አድራሻዎን ያሳውቁ

አድራሻዎን ከቀየሩ፥ ለጥያቄ ስንፈልግዎት ሆነ ለሌላ ጉዳይ እንድናገኝዎት አዲሱን አድራሻ ለስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migationsverket) ያሳውቁ። ከስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚላክ መረጃ እንዳያመልጥዎ የሚመጣልዎትን ደብዳቤ ሁሉ እየተከታተሉ ያንብቡ።

ፈቃድ ስለ ማራዘም

የጊዜ ገደብ ያለበት ፈቃድ ካልዎትና ስዊድን ውስጥ መቆየት የሚፈልጉ ከሆነ ፈቃድዎ ሳይወድቅ የማራዝሚያ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል። አሁን ባሉበት ሁኔታም ከለላ የሚያስፈልግዎት ከሆነ የመኖሪያ ፈቃድዎ ይራዘማል። ስዊድን ውስጥ ለመቆየት የሚያስችል ሌላ ምክንያት ካልዎትም ፈቃድዎ ሊራዘም ይችላል።

የመኖሪያ ፈቃድ ለማራዘም ምን እንዲያደርጉ የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: