የመኖሪያ ፈቃድን ማራዘም

Förlänga uppehållstillstånd – amhariska

በጊዜ ገደብ የተወሰነ የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎትና ፈቅድዎም ከወደቀ በኋላ፥ ስዊድን ውስጥ መቆየት የሚፈልጉ ከሆነ፥ ፈቃድ የማራዘሚያ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርቦታል።

የመኖሪያ ፍቃድዎን ለማራዘም የሚያድርጉት ነገር፥ በተሰጠዎት የፈቃድ ዓይነት ላይ የተመሰረተ ነው። ይሁን እንጂ ሁሌም የያዙት ፈቃድ ጊዜ ገደቡ ከማለፉ በፊት፥ ኣስቀድመው አዲስ ፈቃድ እንዲሰጥዎት መጠየቅ ይኖርቦታል።

ስለዚህ ጉዳይ የሚያብራሩ ገጾችን ያንብቡ። (አንዳንድ ገጾች በሁሉም ቋንቋ አይገኙም።)

ጥገኝነት ጠይቀው ከነበረና፥ በጊዜ ገደብ የተወሰነ የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት

በጊዜ ገደብ የተወሰነው የመኖሪያ ፈቃድዎ በሚወድቅበት ጊዜ፥ እንዲራዘምሎት መጠየቅ ይችላሉ። አሁን ባሉበት ሁኔታም፥ ከለላ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎ ይራዘማል። አንዳንዴም እንደ ሁኔታው፥ ስዊድን ውስጥ ለመቆየት የሚያስችል ሌላ ምክንያት ካለዎትም፥ ፈቃድዎ ሊራዘም ይችላል።

ጥገኝነት ጠይቀው የመኖሪያ ፈቃድዎ ስለ ማራዘም፥ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ስዊድን ውስጥ ከሚቀመጡ ጋር አብረው ለመኖር የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ከሆነ

አብሮ በመኖር ምክንያት ፈቃድ ስለማራዝም፥ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙት በሥራ ምክንያት ከሆነ

የመኖሪያ ፈቃድዎ ጊዜ ካለፈ በኋላ፥ ሥራ መሥራት የሚፈልጉ ከሆነ ፈቃድዎ እንዲራዘም ማመልከት ይኖርብዎታል። ለስድስት ወርና ከዚያም በላይ ለሚያህል ጊዜ ተቀጥረው ይሰሩ ከነበረና፥ ፈቃድዎ ከመውደቁ በፊት የማራዘሚያ ማመልከቻ ካስገቡ፥ የፈቃድ ውሳኔ እስኪሰጥ እየጠበቁ፥ ሥራዎን መቀጠል ይችላሉ።

ፈቃድ ስለማሳደስ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙት ድርጅት በመክፈትዎ ምክንያት ከሆነ

ድርጅት በመክፈትዎ ምክንያት ፈቃድ ስለማራዝም፥ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙት በመማር ምክንያት ከሆነ

በኮለጅ ወይም በዩኒቨርሲቲ በመማር ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ስለማራዘም፥ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የቱሪስት ቪዛ ወይም ለጉብኝት ፈቃድ የተሰጥተዎት ከሆነ

በጉብኝት ምክንያት ፈቃድ ስለማራዝም፥ የበለጠ ማብራሪያ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: