እርስዎ ጥገኝነት ጠያቂ እንደ መሆንዎ የስዊድነኛ ቋንቋ ለማወቅ ይፈልጋሉ​

Lära sig svenska – amhariska

እስዊድን ኣገር የመኖር ፈቃድ ከተሰጠህና የግብረ ጽ/ቤት ከተመዘገብክ የስዊድሽኛ ቋንቋ ለውጭ ኣገር ሰዎች (ኤስ ኤፍ ኢ) ለመማር መብት አለህ። ግን ፈቃድህን ከማግኘትህ በፊት ለመማር ከፈለግክ ወደ ዕርዳታየሚሰጡ ወይንም ማሕበራውያን ትምሕርት ቤቶች ትምሕርተ ስለሚሰጡ ከነሱ ጋር ተገናኝ።

የስዊድነኛ ቋንቋ ትምህርት ክበቦች

ለጥገኝነት ጠያቂዎች የስዊድን እና የማህበረሰብ መረጃ ወርክሾፖችን የሚያቀርቡ በርካታ የትምህርት ድርጅቶች አሉ። በአንድ የጥናት ቡድን ተገናኝተው፤ ስዊድንኛ ለመማርና ቡድኑ በጋራ ተሳታፊዎች በሚፈልጉት መንገድ ጥናቱ ማዘጋጀት ይችላሉ። ሁሉም የሚሳተፉት የመኖሪያ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እየጠበቁ ያሉትና እና የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ግን አሁንም በአጋጣሚ በተቋሙ መኖሪያዎች ውስጥ የሚኖሩ እዛ የመሳተፍ ዕድል ኣላቸው። እዚህ ላይ ለመሳተፍ ምንም አይነት ክፍያ ኣይከፍሉም እንዲሁም አስፈላጊ ሆነ ከተገኘ  የስዊድን ስደተኛ ቦርድ ኣጠቃላይ የእርስዎን የትምህርቶዎን የጉዞ ወጪ ይከፍላል። እርስዎ የጥገኝነት ጥያቄዎን ሌላ የአውሮፓ አገር ውስጥ ኣመልክተው ከሆነ ፣ በስዊድን ውስጥም የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ከስዊድን ልቀቁ ከተባሉ፤ ይህም በግልጽ ኣኳሃን ስዊድን ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት መብት የሌልዎት ከሆነ እና፤ እርስዎም በሚሰጠው ትምህርቱ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ከሆነ የጉዞ ወጪዎን መክፈል አለብዎት።

የስዊድንኛ ጥናት ውስጥ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ከሆነ  እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ካሉት የትምህርት ድርጅቶች ግንኙነት ማድረግ አለቦዎት። እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ የስዊድን  ትምህርት ወርክሾፖች ያለው የትኛውንም ማኅበር ለማወቅ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የመቀበያ ክፍል ያነጋግሩ።

ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር የስዊድነኛን ቋንቋ ይለማመዱ

በርካታ የበጎ አድራጊ ድርጅቶች ለጥገኝነት ጠያቂዎች የስዊድነኛን ቋንቋ ትምህርት ወይም የቋንቋ ካፌዎች በተለያዩ አይነቶች ያደራጃሉ። የትኞቹ ድርጅቶች የስዊድነኛን ቋንቋ ለማሰልጠን ሊረዱዎት እንድሚችሉ ለማወቅ የምትፈልጉ ከሆነ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የመቀበያ ክፍል ያነጋግሩ።

በግልዎ የስዊድነኛን ቋንቋ አጥኑ

በኢንተርኔት ላይ በግልዎ ስዊድነኛ ቋንቋን ለመማር ብዙ ፕሮግራሞች አሉ እንደ www.informationsverige.se። ያሉ ድህረ ገጾች ላይ የተለያዩ ስዊድንኛ ቋንቋ ለማወቅ የሚረዱ አገናኝ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ። አብዛኞቹ ፕሮግራሞች የኢንተርኔት ግንኙነት ይጠይቃሉ። ሁሉም ግን ከክፍያ ነጻ ናቸው።

በሚቀጥለው ድህረ ገጹ ላይ የስዊድንኛ ቋንቋን ለመማር ሁሉንም አገናኞች ያገኛሉ (www.informationsverige.se – ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window

Last updated: 24 August 2017

Was the information on this page helpful to you?