በመጠባበቅ ላይ እያለህ
Medan du väntar – amhariska
መረጃው፡ በስዊድን ኣገር ጥገኝነት ጠይቀው ሲያበቁ ገና መልስ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ሰዎች ይመለከታል
- العربية (arabiska)
- Azərbaycanca (azerbajdzjanska)
- ب ه سۆرانی (sorani)
- English (engelska)
- Español (spanska)
- پارسی (persiska)
- Français (franska)
- Bosanski, hrvatski, srpski (kroatiska)
- Հայերեն (armeniska)
- Kurmancî (kurmandji)
- Монгол хэл (mongoliska)
- يه دری (dari)
- پښتو (pashto)
- Arlijan (romani arli)
- Русский (ryska)
- Af soomaali (somaliska)
- Shqip (albanska)
- Swedish (svenska)
- ትግርኛ (tigrinska)
- Oʻzbek (uzbekiska)
እዚህ፡ የጥገኝነት ጥያቄ ካቀረብክ በህዋላ ምን እንደሚካሄድና እንደ ስደተኛ መጠን በስራ ላይ፡ በትምህርት፡ በመኖርያ ቤት፡ በጤናና እንክብካቤ፡ በገንዘብ እርዳታ የሚኖርህን መብቶች በሚመለከት ማንበብ ትችላለህ።
የጥገኝነት ጥያቄ ምርመራ እስኪጀመር ያለው ጥበቃ
የጥገኝነት ጥቃቄዎን በተመለከተ ለምርመራ እስኪቀርቡ ድረስ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ሲቀርቡ ግን ለምን ስዊድን አገር ጥገኝነት መጠየቅ እንደፈለጉ፥ ምን እንደደረሰብዎት፥ ወደ አገርዎ ቢመለሱ ምን ሊደርስብዎት እንደሚችል መግለጽ ይኖርብዎታል።
ውሳኔ እስኪያገኙ ብዙ ጊዜ ለጥያቄ ሊጠሩ ይችላሉ። የስደተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤቱ (Migationsverket) በቀጠርዎት ቀንና ሰዓት ይምጡ። የጊዜ እጥረት ስላለብን፥ አዲስ የቀጠሮ ቀን መያዝ ጉዳይዎ ውሳኔ የሚያገኝበትን ጊዜ ሊያራዝምብዎት ይችላል።
አድራሻዎን ያሳውቁ
አድራሻዎን ከቀየሩ፥ ለጥያቄ ስንፈልግዎት ሆነ ለሌላ ጉዳይ እንድናገኝዎት አዲሱን አድራሻ ለስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migationsverket) ያሳውቁ። ከስደተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት የሚላክ መረጃ እንዳያመልጥዎ የሚመጣልዎትን ደብዳቤ ሁሉ እየተከታተሉ ያንብቡ።
ኣንተን፡ እንደ ጥገኝነት ፈላጊ ሊረዱህ የሚችሉ ተቋሞች
ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል Amnesty International
የሰደተኞች የጥገኝነት ኮሚቴ ምክርቤት Flyktinggruppernas och asylkommittéernas riksråd
የጥገኝነት ፈላጊዎችና የስደተኞች ምክር ሰጪ ጽ/ቤት Rådgivningsbyrån för asylsökande och flyktingar
ስዊደናዊት ቤትክርስትያን Svenska kyrkan
ስለስዊድን ማህበረሰብ መረጃዎች በተለያዩ ቋንቋዎች በእነዚህ ውስጥ ይገኛል Information om Sverige