መጠለያ

Boende – amhariska

የጥገኝነት ጥያቄዎችን አቅርበው ለውሳኔ እየጠበቁ ነገር ግን መኖሪያ ቤት ከሌልዎት የስደተኞች ኤጄንሲ (የስደተኞች ጉዳይ) ሊረዳዎት ይችላል። የራስዎትን መጠለያ በራስዎት ለማዘጋጀት ከመረጡ ለምሳሌ ከዘመዶች ወይም ከጓደⶉች ጋር በመኖር ይችላሉ። የራስዎትን መጠለያ በራስዎ ለማዘጋጀት ከፈለጉ፣ የስተደኞች ኤጄንሲ ሊያገኝዎት ይችል ዘንድ አድራሻዎትን መስጠት አለብዎት።

በስደተኞች ኤጄንሲ የሚሰጥ ቤት

የስደተኞች ኤጄንሲ ለውሳኔ በሚጠብቁበት ጊዜያት ጊዜያዊ የሆነ መኖሪያ ቤት ይስጥዎታል። ምንም ዓይነት ገንዘብ ከሌልዎት የስደተኞች ኤጄንሲ ለመኖሪያ ቤቱ ኪራይ ይክፈላል።

ቦታው በተገኘበት ሁሉ መኖር ይኖርብዎታል

ቤት እንዲያገኝልዎት የስደተኞች ኤጄንሲን እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ፣ በራስዎት የት መኖር እንዳለብዎት መምረጥ አይችሉም፤ ነገር ግን ቤት ወደተገኘበት ቦታ ለመንቀሳቀስ መዘጋጀት አለብዎት። ለውሳኔ በሚጠባበቁበት ጊዜ፣ ለብዙ አመልካቾች ቦታ ለመስጠት ወደ አዲስ ቤት መጓዝም ሊኖርብዎት ይችላል።

የመኖሪያ ክፍልንም ሊጋሩ ይችላል

የስደተኞች ኤጄንሲ ቤቶች ለጥገኝነት ፈላጊዎች ብቻ ይውላሉ። በቤት ውስጥ ቦታ የተሰጥዎት ከሆነ፣ ይህ ቦታ ለእርስዎ ብቻ የታሰበ ነው። ብዙውን ጊዜ ቤቱ ሌሎች ብዙ ሰዎች የሚኖሩበት አንድ ፎቅ ይይዛል። ብዙውን ጊዜ ቤተሰብ ለራሳቸው ክፍል ያገኛሉ። ያላገቡም ተመሳሳይ ጾታ ካላቸው ከሌሎች ሰዎች ጋር ክፍል ሊጋሩ ይችላሉ።

በምንም ምክንያት፣ የተለየ የመቆያ መኖሪያ ቤት ከፈለጉ፣ እባክዎትን ለእንግዳ ተቀባይዎ ማዕከል ይንገሩ። የስደተኞች ኤጄንሲ ማንኛውም በቤቱ ውስጥ የሚኖር ሰው በራሳቸው ቤት አከባቢ እንደሚኖሩ እንዲሰማቸው ያረጋግጣል። እያንዳንዱ በቤቱ ውስጥ የሚኖር ሰው እርስ በርሳቸው እንዲከባበሩ እና ያለምንም የሃይማኖት፣ የባሕል ወይም የጾታ ሁኔታ ልዩነት ለእርስ በርሳቸው መቀባበልን ማሳየት በጣም አስፈላጊ ነው።

LGBT ከሆኑ እና ስለመጠለያዎ የተለየ ፍላጎቶች ካልዎት በተቻለ ፍጥነት ለእንግዳ ተቀባይ ሠራተኛ ጋር ይነጋገሩ። ደኅነቱ የተረጋገጠ እና ለእርስዎ ትክክለኛ የሚሆነውን ቤት ለማግኘት ማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።

ቤቱ ውስጥ ለመኖር ያለዎት መብት የሚያበቃበት

ወደ አገርዎ የመላክ ወይም በግዳጅ ወደ አገርዎ የመወሰድ ውስኔ ከተወሰነብዎት እና ውሳኔው ተግባራዊ መደረግ ካለበት፣ ወይም በፈቃደኝነት ለቀው የሚሄዱበት የጊዜ ገደብ ከደረሰ ቤቱን ባዶ ማድረግ ይጠብቅብዎታል። ይህም የእነርሱን እንክባካቤ የሚፈልጉ ዕድሜአቸው ከ18 በታች ያሉት ልጆች ለሌላቸው አዋቂዎች ተግባራዊ ይደረጋል።

የራስዎት ቤት

የስደተኞች ኤጄንሲ በሚያቀርበው ቤት ውስጥ ለመኖር ካልፈለጉ፣ የራስዎትን መጠለያ ማግኘት ይችላሉ። አብዛኛው ሰው የጥገኝነት ማመልከቻቸው ምላሽ ለማግኘት በሚጠብቁበት ጊዜ ከጓደኞች ወይም ከዘመዶች ጋር መኖርን ይመርጣሉ። የራስዎትን መጠለያ በራስዎ ማመቻቸው ከፈለጉ፣ የዚህን ውጪዎች በራስዎት መክፈል አለብዎት።

በምንም ምክንያት ይሁን፣ እርስዎ በራስዎ ባመቻቹት መጠለያ ውስጥ በቀጣይነት መኖር የማይችሉ ከሆነ፣ ስፍራ በተገኘበት ቦታ ላይ፣ የስደተኞች ኤጄንሲ በሚሰጠው ቤት ውስጥ መዛወር ይችላሉ። እባክዎትን ለበለጠ መረጃ እርስዎ በተመዘገቡበት የእንግዳ መቀበያ ማዕከልን ይጎብኙ።

የስደተኞች ኤጄንሲ በሚሰጠው ቤት ውስጥ አሊያም እርስዎ በራስዎት ባመቻቹት ቤት ውስጥ ቢኖሩም፤ የስደተኞች ኤጄንሲ እርስዎን ለማግኘት የሚችልበት ቦታ ላይ መኖር አለብዎት። በሚጠባበቁበት ጊዜ መኖሪያዎትን ቀይረው ከሆነ ስለ አዲሱ አድራሻዎ ለእንግዳ መቀበያ ማዕከል መንገርዎን ያስታውሱ።

ለመኖር ከተፈቀደልዎት

በስደተኞች ኤጄንሲ በተሰጥዎት ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ባገኙበት ጊዜ አዲስ ቤት ለማግኘት ከስደተኞች ኤጄንሲ እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ። የስደተኞች ኤጄንሲ አዲስ ቤት እስከሚያገኝልዎት ድረስ በስደተኞች ኤጄንሲ በተሰጥዎት ቤት ውስጥ መኖር መቀጠል ይችላሉ። በራስዎት መጠለያ ውስጥ እየኖሩ ከሆነ ወይም ሥራ መስራት በሚችሉበት ደረጃ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ፣ በራስዎት አዲሱን የመኖሪያ ቤት ማመቻቸት አለብዎት።

በቋሚነት የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ ምን ሊሆን እንደሚችል በይበልጥ ያንብቡ።

ለተወሰነ ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ ምን እንደሚሆን በይበልጥ ያንብቡ።

Last updated: 24 August 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.