የጥገ ኝነት ጉዳይህን እስኪጣራ ለመስራት

Arbeta under tiden som asylsökande – amhariska

የጥገኝነት ጥያቄህ በሂደት ላይ እያለ ራስህን መቻል ይገባሃል። ለዚህም ባጠራቀምከው ገንዘብ ወይም በስራ ብምታገኘው ገቢ ሊሆን ይችላል።

ውሳኔው እስክታገኝ ድረስ የመስራት መብት እንዲኖርህ የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከሚያስፍልግ ግዴታ ነጻ መሆንህን የሚያረጋግጥ ምስክር (AT-UND) መኖር ኣለብህ።

እንደ ጥገኝነት ፈላጊ የስራ መብት ለማግኘት ማሟላት ያለብህ

የሚከተሉንትን ካሟላህ መብቱን ለማግኘት ናጻ ነህ፤

  • ብቁ መታወቅያ ወረቀት ስታቀርብ ወይም ማንነትህን ለመግለጽ ስትተባበር
  • ጉዳይህን በስዊደን ኣገር የሚታይ ከሆነ
  • ጥያቄህ መሰረት ያለው ከሆነ። ከዚህ ኣገር እንድትወጣ ከተወሰነብህ AT-UND ለማግኘት መብት የለህም ቶሎም ካገሪቱ ትባረራለህ።

የትኛው ኣገር ጉዳይህን ለማየት ስልጣን እንዳለው የሚወስን የዱብሊን መምርያ ነው። (በእንግሊዝኛ)

መረጃ ላንተ ካገሪቱ እንድትወጣ የተወሰነብህ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የተፈለገውን ነገር ያሟላህ ከሆንክ LMA-ካርድ ታገኛለህ፡ እዛው ላይ AT-UND እንዳለህ ተጽፍዋል። ካርዱ ማግኘቱ ራሱ የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከሚጠየቀው ግዴታ ነጻ ነህ ማለት ነው። AT-UND የመኖርያ ፈቃድ እስክታገኝ ወይም ኣገሪቱን ለቀህ እስክትወጣ ድረስ ያገለግላል። ጉዳዩን በሚመለክት ማለት AT-UND መኖርህ በእርግጥ ለማወቅ ከፈለግክ በመቀበያው ክፍል ያሉትን ሰዎች ኣነጋግራቸው።

ስለ LMA-ካርድ በተጨማሪ ኣንብብ

የሥራ ፈቃድ ከመኖር ግዴታ ነጻ እንዲሆኑ ከተወሰንልዎት (AT-UND)፥ ወደ ሠራተኛና አሠሪ ማገናኛ ማዕከል (Arbetsförmedlingen) ሄደው ሥራ መፈለግ ይችላሉ።

በኣርበትስፎርመድሊንገን ወብሳይት ክፍት የስራ ቦታን በሚመለከትና ሌላ ጠቃሚ መረጃ ልታገኝ ትችላለህ (በእንግሊዝኛ)external link, opens in new window

ጥገኝነት እየጠየቅክ እያለህ ስራ ብታገኝስ

ጥገኝነት እየጠየቅክ እያለህ ስራ ካገኘህ የስራ ፈቃድ ለማግኘት ከሚያስፍልግ ግዴታ ነጻ መሆንህን የሚያረጋግጥ ምስክር (AT-UND) ለስራ ሰጪው ማሳየት ይኖርብሃል። ምስክሩ በ LMA ካርድህ ብቍጥር 7 ይገኛል።

ስራ ሰጪው ስራ ስለ ማግኘትህ በተመዘገብክበት ቦታ ለሚገኘው የመቀበያ ክፍል (ሞታግኒንግስኤንሄት) ማመልከት ኣለበት። ስራ ሰጪው ስራው መቼ እንደሚያበቃም ለመቀበያ ክፍሉ ማሳወቅ ኣለበት። ስራ ማግኘትህ የሚገልጽ መልእክት በልዩ ፎርም ይሞላል፡ ቍ. 152011

Notification of employment or termination of employment of an asylum seeker, form number 152011 (በስዊድሽኛ ቋንቋ)PDF

የቀን ኣበል የምታገኝ ከሆንክ ገቢህን ሁሌ ለሚግራኹንቨርከት መላክ ይኖርብሃል። የሳምኦርድኒንግ ቍጥር ለማግኘት ደግሞ ስካተቨርከትን (የቀረጥ ጽ/ቤት) ማነጋገር ይገባሃል። የሳምኦርድኒንግ ቍጥር ፐርሾንኑመር ለሌላቸው ሰዎች የሚሰጥ ነው፡ ስራ ስትሰራና ቀረጥ መክፈል ሲያስፈልግህ የሳምኦርድኒንግ ቍጥር ያስፈልጋል። ስትታመምና ለጊዜው ወደ ስራ መሄድ ስታቋርጥ፡ ገንዘብ (ሹክፐኒንግ) ለማግኘት  የሳምኦርድኒንግ ቍጥር ያስፈልገሃል።

ለተጨማሪ መረጃ ስካተቨርከትን ኣነጋግር (ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window

የባንክ ሂሳብ መክፈት ከፈለጉ

ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚያገኙት የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገንዝብ የሚያስቀምጠው፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ብቻ ነው። አስሪዎ የሚከፍሎትን ወርሃዊ ደሞዝ የሚያስቀምጡበት የባንክ ሂሳብ መክፈት ከፈለጉ፥ ባንክ ቤት ሄደው መነጋገር ይኖርብዎታል። የባንክ ሂሳብ ለመክፈት የሚጠየቀውን መስፈርት ሟሟላትዎን የሚያጣራውና የሚወስነው እያንዳንዱ ባንክ ቤት ራሱ ነው።

ሁሉም ባንክ ቤቶች ማንነትዎን ማወቅ ስለሚፈልጉ የርስዎን ማንነት የሚገልጽ አንድ ህጋዊ የመታወቂያ ሰነድ ይጠይቃሉ። ምን ዓይነት የመታወቂያ ሰነድ እንደሚቀበሉ የሚወስኑት ራሳቸው ባንክ ቤቶቹ ናቸው። አንዳንድ ባንክ ቤቶች የጥገኝነት ጠያቂዎች መታወቂያ ሰነድ ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር እንዳለ እያወቁ፥ የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ የሚፈቅዱበት ግዜ አለ። ይሁን እንጂ የአገልግሎት ግዜው የጸና የስደተኞች ጉዳይ ካርድ (LMA-kort) እና የኦሪጅናሉ መታወቂያዎ ትክክለኛ ቅጅ መሆኑ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ማህተም የተረጋገጠ የመታወቂያ ሰነድም አብሮ ማሳየት ያስፈልጋል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤቱ የሚመሰክረው መታወቂያው ሃቀኛ መሆኑን ሳይሆን፥ ቅጅው በእጁ ካሉት የመታወቂያ ሰነዶች ጋር አንድ መሆኑን ብቻ ነው። ለእኛ የሰጡት የመታወቂያ ሰነዶች ራሳቸው ቅጅዎች ከሆኑ ግን እንዲህ ዓይነት ምስክርነት መስጠት አንችልም።

የሆነ ሆኖ ባንኮቹ የመታወቂያ ሰነዶቹን ካዩ በኋላ፥ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትን ይገናኙና እርስዎ ያቀረቧቸው መረጃዎች ትክክለኞች መሆናቸውን ያጣራሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ለባንኮቹ ማረጋገጫ የሚሰጠው፥ እርስዎ መረጃ ለሌላ የማስተላለፍ ፈቃድ ሰጥተውት ከሆነ ብቻ ነው፣ ማለትም እርስዎ ቀደም ብሎ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከባንኮች ጋር እንዲነጋገርና መረጃ እንዲሰጥ በፊርማዎ አረጋግጠው ከሆነ ነው። እንዲህ ዓይነት ፈቃድ እስከ አሁን ያልሰጡ ከሆነ በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የስደተኞች ጉዳይ እንግዳ መቀበያ ቢሮ ዘንድ ሄደው፥ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ፈቃድ መስጠት የሚፈልጉ መሆንዎን ይግለጹ።

የባንክ ሂሳብ መክፈት በሚፈልጉበት ግዜ አንዳንድ ባንክ ቤቶች የሥራ ቅጥር ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሊጠይቅዎት ይችላሉ። ያን ዓይነቱን የቅጥር ማስረጃ ከአስሪዎ ማግኘት ይችላሉ።

ከ18 ዓመት በታች ከሆንክ/ሽ

16 ዓመት ወይም በላይ ከሆንክ ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) ያስፈልግሃል። ከቤተሰብ ጋር ወይም ብቻህን የመጣህ ብትሆንም ይህ ይመለከትሃል።

16 ዓመት ያልሞላችሁ በልምምድና አነስተኛ ሥራዎች እንዲሁም አንድ ቁንጽል ሥራ ለመሥራት ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) አያስፈልጋችሁም። የስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤትም ቅጥሩን ማጽደቅ አይኖርበትም። ይሁን እንጂ የአሳዳጊው ወይም ሞግዚቱ ፈቃድ መሆኑን ማሳወቅ ያስፈልጋል።

በደሞዝ ሆነ በድጎማ መልክ የሚሰጥ ጥቅም ሁላ፥ ለምሳሌ እንደ ስጦታ ካርድ፥ በLMA ደንብ መሠረት ያገኙትን የመታገዝ መብት ሊነካ እንደሚችል ያስተውሉ።

ካገሪቱ ውጣ የሚል ውሳኔ የተሰጠህ ከሆነ

አገሪቱን ለቀው ለመውጣት ከስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር እስከተባበሩ ድረስ ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) ሊይዙ ይችላሉ። ካልተባበሩ ግን የያዙት ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛ (AT-UND) አያገለግልም።

የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን

ውሳኔ እየጠበቅክ እያለህ የሰራህ ከሆንክ እና የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን የስራ ፈቃድ ለማግኘት ልትጠይቅ ትችላለህ።

የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሆኖ ሲያበቃ የስራ ፈቃድ ለማግኘት ምን እንደሚያስፈልግህ በተጨማሪ ኣንብብ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ጥገኝነት ለጠየቁ ሥራንና ከሥራ ፈቃድ ግዴታ መዳኛን (AT-UND) የሚመለከቱ የተለመዱ ጥያቄና መልሶች፥

Last updated: 16 October 2019

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.