የጤና እንክብካቤ ለጥገኝነት ጠያቂዎች

Hälso- och sjukvård för asylsökande – amhariska

እናንተ በስዊድን ጥገኝነት ጠያቂ የሆናችሁ አፋጣኝ የሆነና መቆየት የማይችል የጤናና የ ጥርስ ህክምና የማግኘት መብት አላችሁ፡፡

በስዊድን ውስጥ የቀጠና ግዛቶችና ክልሎች የጦና እንክብካቤ የመስጠት ሀላፊነት አለባቸው፡፡ ይሄ በሀገሪቱ ሁሉ የሚሰራ ነው፡፡ እያንዳንዱ የቀጠና ግዛትና ክልል በየሆስፒታሉ ውስጥና በጤና እንክብካቤ ጣቢያዎች ስላሉ መረጃዎች የሚገልጽ የራሱ ድህረ ገጽ አለው፡፡ እያንዳንዱን ቀጠናና ክልል የያዘም አንድ ድህረ ገጽ አለ፡ 1177 Vårdguiden (የጤና እንክብካቤ መመሪያዎች)፡፡

በ 1177 የጤና እንክብካቤ መመሪያዎች  ውስጥ የተለያዩ የጤና እንክብካቤ እና የጥርስ ክኒኮችን መገኛ መረጃና ስራ የሚጀምሩበትን ሰዓት ማግኘት ይችልሉ፡፡ በየትኛውም ሰዓት 1177 በመደወል የጤና እንክብካቤ መመሪያዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ስልክ ቁጥሩም 1177 ነው፡፡ ሲደውሉ የጤና ፍላጎትዎን ከምታመዛዝን፤ ምክር ከምትሰጥ እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ ወደ ትክክለኛው የጤና እንክብካቤ ክሊኒክ የምትመራዎት  ነርስ ጋር ያወራሉ፡፡

የበለጠ ለማንበብ www.1177.seexternal link, opens in new window

የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት

በስዊድን ጥገኝነት ጠያቂ ከሆናችሁ አፋጣኝ የሆነና መቆየት የማይችል የጤናና የ ጥርስ ህክምና የማግኘት መብት አላችሁ፡፡. የቀጠናው ግዛት/ክልል ምን አይነት የጤና እንክብካቤ ማግኘት እንዳለባችሁ ይወስናል፡፡ የማዋለድ እንክብካቤ፣ የማስወረድ እንብካቤ፣ የወሊድ ቁጥጥር ምክር፤ የአራስነት እንክብካቤ እንዲሁም ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል አስመልክቶ እንክብካቤ  የማግኘት መብት አሎት፡፡

ከ 18 አመት በታች ያሉ ጥገኝነት ጠያቂ ህጻናትና ወጣቶች ልክ እንደ ስዊድን ሀገር እንዳሉ ሌሎች ህጻናት ነጻ የጤና እና የ የጥርስ ህክምና የማኘት መብት አላቸው፡፡

የጤና ግምገማ

ሁሉም የጥገኝነት ጠያቂዎች የጤና ግምገማ ይደረግላቸዋል፡፡ ለጥገኝነት ካመለከቱ በኋላ በአፋጣኝ ነጻ የሆነ  የጤና ግምገማ እንዲደርጉ ይደረጋል፡፡  

የጤና ግምገማው ለጥገኝነት ያስገቡት ማመልከቻ ላይ ምንም ተጽእኖ አያመጣም፡፡ ቶሎ እርዳታ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ለመለየት ስለሆነ ግምማው ለእርስዎ ነው፡፡ በጤና ግምገማው ላይ ስለ ጤና በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ምክር ሲያገኙ እንዲሁም በስዊድን ውስጥ ስላለው የጤና እንክብካቤ መረጃ እንዲሁም የመለያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች ለ ስዊድን የስደተኞች ቦርድ አይሰሩም እንዲሁም ሚስጥር የመጠበቅ ቃለ መሃላ ገብተዋል፡፡

ስንኩልና ካለብህ

የጤንነት ምርመራ በምታደርግበት ወቅት የስንኩልና ችግር ካለህ ወይንም ቢሰማህ ቶሎ ብለህ ታመለክታለህ። የአካል ወይንም የዓምሮ ስንኩልካለብህ ።

በስንኩልነት ምክንያት የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ ችግር ካጋጠመህ ዕርዳታ ይደረግልሃል። በስነኩልና ምክንያት ፈቃድ እንዳይሰጥህ የሚወስን ሕግ የለም።

ስንኩልና ካለህ ና ፈቃድ ከተሰጠህ፤ አስፈላጊ ዕርዳታ እንዲሰጠህ መብት አለህ፤ እስዊድሹ ሕብረተ ሰብ እንድትሳተፍ እንዲቀልልህ ይረድሃል።

የጤና እንክብካቤ መቼ እንደሚያስፈልግዎ

ከታመሙ ወይም ራስዎን ካቆሰሉ መጀመሪያ ማድረግ ያለብዎት ነገር ወደ ጤና እንክብካቤ ማእከላት መሄድ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቀጠሮ አስይዘው ወደ እንክብካቤ ማእከላት ይመጣሉ፡፡ አካባቢዎት ያለ የጤና እንክብካቤ ማእከል ከፈለጉ 1177 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ በጣም ከታመሙና ምቡላንስ ከፈለጉ 112 መደወል ይችላሉ፡፡

ለአጣዳፊ የጥርስ ህመም ወደ ብሄራዊ የጥርስ አገልግሎት (Folktandvården) ወይም በቀጠና/ክልል ወደተመደቡት ዴንቲስቶች መሄድ ይችላሉ፡፡

በ 1177.se. ”Hitta vård“ን ለተጨማሪ መረጃ ይመልከቱ፡፡ እዚያ ያሉት መረጃዎች በተለየዩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡ ስዊድንኛ የማይናገሩ ከሆነ ሆስፒታል ሲሄዱ ወይም ወይም ጤና ጣቢያ በሚሄዱበት ጊዜ ወይም የጥርስ ክሊኒክ ሲሄዱ አስተርጓሚ ለማግኘት መብት አለዎት፡፡ አብዘኛውን ጊዜ ጠጤና ጣቢያው ሰራተኞች አስተርጓሚ ያዘጋጃል:: ቀጠሮ በሚያሲዙበት ጊዜ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ ይናገሩ፡፡

መድሀኒቶች

ፋርማሲ ውስጥ መድሁኒቶችን እና ሌሎች የጤና እንክብካቤ መጠበቂያዎችን መግዛት ይችላሉ፡፡ እዛ ሀኪም ያዘዘልዎትን መድሀኒትም መግዛትም ይችላሉ፡፡

የታካሚ ትራንስፖርት

በጤና ሁኔታዎ ምክንያት ወደ ጤና ጣቢያው በራስዎ መሄድ የማችሉ ከሆነ፣ የታካሚ ትራንስፖርት እንዲዘጋጅ ማድረግ  ይቻላል፡፡ ከሆስፒታል ዌም ከ ጤና ጣቢያ ለመመለስ እና ለመሄድ ያወጡት ወጪም ይወራረዳል፤ ይህም ከጠየና ጋር የተያያዘ ምክንያት ካለው ነው፡፡  ለ ታካሚ ትራንስፖርት መብት እንዳለዎ እና እነደሌለዎ የሚወስነው እንክብካቤ የሚያደርግልዎ ሰው ነው፡፡ ስለሚኖሩበት ወረዳ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 1177 ቫርድጉይደን መደወል ይችላሉ፡፡

በ www.1177.se/Regler-och-rattigheter/Sjukresor/ ተጨማሪ ማንበብ ይችላሉ፡፡ (በስዊድሽኛ ቋንቋ)external link, opens in new window

የ እል ኤም ኤ ካርዶን ህልጊዜ ይያዙ

መድሀኒት ሲገዙ ወይም ወሰ ጤና ጣቢያ በሚሄዱ በት ጊዜ የ እል ኤም ኤ ካርዶን ማሳየት አለብዎ፡፡ የ እል ኤም ኤ ካርድ ያተሰጠዎ ከሆነ ጥገኝነት የጠየቁበትን ደረሰኝ ማሳየት አለብዎ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ጤና ጣቢያ በሚሄዱበት ጊዜ የ እል ኤም ኤ ካርዶን ካሳዩ የሚጠየቁት የሂሳብ መጠን አነስተኛ ይሆናል፡፡ መድሀኒት መደብር ሲሄዱም ለአብዛኛዎቹ በሀኪም ለሚታዘዙ መድሀኒቶችም የሚጠየቁት ክፍያ አነስ ያለ ነው፡፡

ለጤና ክብካቤ የሚወጣ ወጪ

የ LMA ካርዳቸውን ለሚያሳዩ የጥገኝነት ፈላጊዎች እነኚህ ክፍያዎች ተገቢ ናቸው፡፡

የጤና ክብካቤ ማዕከልን ወይንም ሆስፒታልን ይጎብኙ
  
በጤና ክብካቤ ማዕከላት ውስጥ የዶክተሮች ቀጠሮ50 ክሮነር
ከሪፈራል* በኋላ የዶክተሮች ቀጠሮ50 ክሮነር
ከሪፈራል* በኋላ ከዶክተሩ ይልቅ ወደ ሌላ የጤና ክብካቤ ሰጪ (ለምሳሌ ነርስ፣ ፊዚዮቴራፒስት፣ አማካሪ)25 ክሮነር
የህጻናት እና ቅድመ ወሊድ ህክምና፣ የእርግዝና ክብካቤ እና የህጻናት ወሊድነጻ
ተላላፊ በሽታ ካለብህ የመከላል ህክምናነጻ

*ሪፈራል ማለት አንድ ህመምተኛ ልዩ የሆነ ምርመራ ወይም ህክምና ሲያስፈልገው ዶክተሩ ወደ ሌላ የጤና ክብካቤ ሰጪ ክሊኒክ የሚልከው የመግባቢያ ወረቀት ነው፡፡ የሪፈራል ወረቀቱ ስለሚታይብህ የህመም ምልክቶች፣ ስለ ስሜትህ እና የበፊት የህምም ታሪክህ እና ቁስል ካለህ በዝርዝር የሚይዝ ነው፡፡ የጤና ክብካቤ ሰጪው ክሊኒክ - የሪፈራል ወረቀቱን የሚቀበልህ - ለምርመራ ይጠራሃል፡፡

ከባድ የሆስፒታል ክብካቤ

ለከባድ ታማሚዎች የሚጠየቀው ክፍያ ከሀገር ሀገር ይለያያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ያለውን የክፍያ መጠን ከሀገሪቱ ምክር ቤት/ከክልሉ ድህረ ገጽ ላይ ወይም በ 1177 ቫርደጉይደን ማግኘት ትችላለህ፡፡

ከባድ የጥርስ ህክምና
  
ወደ ብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ወይንም ወደ ሌላ የጥርስ ህክምና ሰጪ የጥርስ ሃኪም የሚደረግ አጣዳፊ ህክምና50 ክሮነር
ከብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት እውቅና ውጪ ወደ ግል የጥርስ ሃኪም ለድንገተኛ ህክምና መሄድሃኪሙ የሚያስከፍለንን

መድሃኒቶች

ሃኪም ለሚያዝልህ መድሃኒቶች በአብዛኛው የምትከፍለው 50 ክሮነር ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚታዘዙልህ መድሃኒቶች ከ 50 ክሮነር በላይ ውድ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ለህፃናት የሚታዘዙ መድሃኒቶች ነጻ ናቸው፡፡

ለህመምተኛ የሚሆን ትራንስፖርት

ለህመምተኛው ትራንስፖርት ከ40 ክሮነር ያልበለጠ ትከፍላለህ፡፡

ከስደተኞች ቦርድ የሚደረግ ድጋፍ

ለጤና ክብካቤ ያወጣሃቸውን ወጪዎች እንዲሁም ለመድሃኒት ግዢ ያወጣሃቸውን ወጪዎች ከታዘዘበት ወረቀት ጋር ይዘህ ልዩ ድጋፍ እንዲደረግልህ የስደተኞች ቦርድን መጠየቅ ትችላለህ፡፡

ወጪዎችህ ከ 400 ክሮነር ከበለጡ

በ 6 ወራት ውስጥ ለዶክተሮች ቀጠሮ፣ ለህመምተኛ ትራንስፖርት፣ ለታዘዙ መድሃኒቶች እና ለሌላ የጤና ክብካቤዎች (እንደ ፊዚዮቴራፒ ላሉ) ያወጣኸው ወጪ ከ 400 ክሮነር ከበለጠ ልዩ ድጋፍ እንዲደረግልህ ማመልከት ትችላለህ፡፡ የስደተኞች ቦርድ ከ 400 ክሮነር ለሚበልጡ ወጪዎች ሽፋን ይሰጥሃል፡፡ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲደረግልህ ለአገልግሎቱ የከፈልክበትን ደረሰኝ (የክፍያ መጠን ሳይሆን) ለማረጋገጫ ማሳየት አለብህ፡፡ የመድሃኒቶቸን ደረሰኝ በተመለከተ በታዘዘልህ መሰረት ማቅረብ ይኖርብሃል - በደረሰኙ ላይ ስምህ ሊጠቀስ ይገባል፡፡

ከባድ የጤና ክብካቤ እና መድሃኒት

ለከባድ የጤና ክብካቤ የሚወጡ ወጪዎች ከላይ በተጠቀሰው የ400 ክሮነር ውስጥ የሚጠቃለሉ አይደለም - ነገር ግን ከ50 ክሮነር ለሚበልጥ ወጪ ልዩ ድጋፍ እዲደረግልህ መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ከባድ የጥርስ ህመም አጋጥሞህ የብሔራዊ የጥርስ ህክምና አገልግሎት ክፍት ያልነበረ ከሆነ ወይንም አንተ አጣዳፊ አገልግሎት ፈልገህ ጊዜ ያልነበራቸው ከሆነ በተመሳሳይ መልኩ የምትስተናገድ ይሆናል፡፡ ደረሰኙን ወደ ስደተኞች ቦርድ ይዘህ ሄደህ የልዩ ድጋፍ ማመልከቻህን ህክምናውን ከታከምክ በኋላ በፍጥነት አስገባ፡፡

Last updated: 14 December 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.