LMA-ካርድ ለጥገኝነት ፈላጊዎች

LMA-kort för asylsökande – amhariska

ኤል.ኤም.ኤ LMA የጥገኝነት ፈላዊዎች መቀበል የሚመለከት ነው። LMA-ካርድ የፕልስቲክ ካርድ ሆኖ የጥገኝነት ፈላጊ መሆንህን የሚያረጋግጥ ፎቶ ኣለው።

Bild av LMA-kort

በስዊደን ኣገር ጥገኝነት ስትፈልግ ፎቶ ትነሳልህ። በኋላ LMA-ካርድ የሚባል ካርድ ትሰጣለህ። ካርዱ የመታወቅያ ወረቀት (ኣይዲ ካርድ) ኣይደለም።  ጥገኝነት ፈላጊና ውሳኔ እስኪሰጥህ ድረስ በስዊድን ኣገር መኖር የምትችል መሆንህ ነው የሚያረጋግጠው። ካርዱ የግልህ ሆኖ ጥገኝነት ስትጠይቅ ደረስኙን በመተካት የተሰጠህ ነው።

LMA-ካርድሁሌ ካንተ ጋ ያዘው

ከባለስልጣን ጽ/ቤት ስትገናኝ LMA-ካርድ  ማሳየት ይኖርብሃል። ኣንዳንድ ግዜ LMA-ካርዱ ከውጭ ኣገር ፖስታ ሲላክልህ ወይም ከሚግረሽን የሚላከው ራኮማንዴ የሆነ ፖስታ ስትቀበል ልትጠቀምበት ትችላለህ።

ኣንዳድ ግዜ ሓኪም ቤት ስትሄድ LMA-ካርድ በማሳየት ዝቅተኛ ዋጋ ትከፍላለህ። የሓኪም ወረቀት በማሳየት መድሃኒት በምትገዛበት ግዜም በ LMA-ካርድ ዝቅተኛ ዋጋ ትከፍላለህ።

ለጥገኝነት ፈላጊዎች ስለሚመለከት ህክምና በተጨማሪ ኣንብብ

ከሚግረሽን ሰራተኞት ጋር ስትነጋገር በLMA-ካርድ ፎቶ ስር ያለውን ቍጥር ተጠቀምበት። ቍጥሩን በመጠቀም ሰነዶችህን ቶሎ ሊያገኙት ይችላሉ።

LMA-ካርድሲጠፋብህ

LMA-ካርድ ሲሰረቅብህ ወይም ሲጠፋብህ ቶሎ ብለህ ለፖሊስ ኣሳውቅ።  ከፖሊስ የምታገኘውን ሪፖርት ይዘህ ወደ መቀበያ ትሄዳለህ፡ ከዛም ኣዲስ LMA-ካርድ ትጠይቃለህ። 

LMA-ካርድየሚያገለግልበት ግዜ

የመጀመርያው  LMA-ካርድህ ለኣራት ወራት ነው የሚያገለግለው። ከዛ ቀጥሎ ለስድስት ወራት የሚቆይ ኣዲስ LMA-ካርድ የሰጥሃል። ኣሮጌው ካርድ ሲወድቅ ኣዲስ ካርድ ማዘዝ ኣያስፈልግም። ኣዲሱ ካርድ ወደ መቀበያው ጽ/ቤት ኣውቶማቲክ ነው የሚላከው፡ ኣንተም እዛው ሂደህ ትወስደዋለህ። ባብዛኞቹ የስደተኞች መቀበያ ጣብያዎች፥ ”የኤል.ኤም.አ መታወቅያ” (LMA-kort) መጥተህ ለመውሰድ፥ ቆጠሮ መያዝ ግዴታ ያስፈልጋል።

ጥያቄህ ውድቅ ሆኖ ካገር የሚያስወጣህ ውሳኔ ካገኘህና ውሳኔው በተግባር ላይ መዋል ከጀመረ ወይም በራስህ ፈቃድ ማድረግ የሚገባህ ወደ ኣገርህ የመመለስ  ግዜ ካለፈ፡ የገንዘብ እርዳታ መብትህ ያቆማል። ይህ ከ18 ዓመት በታች የሆኑት ልጆች ጋር በሞግዚነት ለማይኖሩትን ጎልማሶች ይመለከታል።

ከሚግራሾንስቨርከት በሚወጥቡተ ጊዜ፥ ካርድዎን ኣስረክበው መሄድ ይኖርብዎታል። ይህም ማድረግ ያለብዎ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎ በማግኘትዎ ምክንያት፥ ወይም በሌላ ምክንያት እርዳታ የማግኘትዎ መብት ቢቋረጥም ወይም ስዊድን አገር ለቀው መውጣትዎ ቢሆንም፥ ካርድዎን ያስረክባሉ።

የመቀበያው ክፍልህን ፈልግ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ልትጎበኘን ከመምጣትህ በፊት ቀጠሮ ትይዛለህ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: 2021-03-08