የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ

Familjeåterförening – amhariska

ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን መጥቶ ከእርስዎ ጋር ለመኖር ያለው ዕድል በተሰጥዎት የመኖሪያ ፈቃድና የጥገኝነት ዓይነት ላይ የሚመሰረት ነው። ከቤተሰብዎ ጋር የመሰባሰብ መብት ከተሰጦት፥ (försörjningkrav) 'መተዳደሪህን መቻል' የሚባለው ደንብ ሊመለከቶት ይችላል።

የመኖሪያ ፈቃድ መያዝዎ ብቻ ቤተሰብዎ በእርግጠኛነት ወደ ስዊድን ሊመጡልዎት ዕድል አላቸው ማለት አይደለም። ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም እንደ ስደተኛ የመጠጊያ ፍቃድ ከተሰጥዎት፥ ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ማስገባት ይችላል። የተሰጥዎት የጥገኝነት ፈቃድ እንደ 'ተለዋጭ ጥገኝነት የሚሻ' ዓይነት ከሆነ ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ለመምጣት ያለው ዕድል በጣም አነስተኛ ነው።

ማን የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ መብት አለው?

የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ መብት፤ በተሰጠዎት የጥገኘት ፈቃድ ዓይነት ላይና፤ እንዳንዴም ጥገኝነት የጠየቁበት ጊዜ ላይ የሚመሰረት ነው።

የሚከተሉትን ነጥቦች ያሟሉ ከሆነ ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል።

 • ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያሎት ከሆነ
 • የተሰጥዎት ጥገኝነት ደረጃ በስደተኛነት ከሆነ
 • የጥገኝነት ደረጃው (alternativt skyddsbehövande) ተለዋጭ ጥገኝነት የሚሻ ዓይነት ሆኖ ቢያንስ ከ24 ህዳር (ኖቬምበር) 2015 በፊት ጥገኝነት ጠይቀው ከሆነ፥

የተሰጥዎት ጥገኝነት ደረጃ ተለዋጭ ጥገኝነት የሚሻ ዓይነትና ቢያንስ ከ24 ህዳር (ኖቬምበር) 2015 በፊት ጥገኝነት የጠየቁ ከሆነ የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ መብት የሚኖርዎት አንድልዩ ሁኔታ ካለ ብቻ ነው ።

የቅርብ ቤተሰብ ብቻ ነው መምጣት የሚችል

እንደ ቤተሰብ ተብሎ የሚታሰበው፥ ባል፥ ሚስት፥ በሕግ የተመዘገበ/ች የኑሮ ጓደኛ እና ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ልጆችዎ ናቸው። ሌላው ዘመድ አዝማድ ወይም ከ18 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ፥ እርስዎ በጊዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድ ሲያገኙ፥ ወደ ርስዎ ወደ ስዊድን አገር ሊመጡ አይችሉም። ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ከሆንክ/ሽ ወላጆችህ/ሽ እንደ ቅርብ ዘመድ ይቆጠራሉ።

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥትዎት ከሆነ ሊያገቧት ወይም አብሮ ሊኖሩ የሚፈልጓት (የሚፈልጉት) እንኳን ወደ ስዊድን ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ።

የጊዜ ገደብ ያለው የመኖሪያ ፍቃድ ከተሰጠዎት፥ የኑሮ ጓደኛዎ የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ የሚችለው/የምትችለው እርሶና ጓደኛዎ፥ ሁለታችሁም ቢያንስ 21 ዓመት ዕድሜ የሞላችሁ ስትሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ወደ ስዊድን ከመምጣታችሁ በፊትህ አብራችሁ ትኖሩ የነበራችሁ መሆን አለበት። የሁለታችሁም የሆነ ልጅ ካላችሁ ግን የዕድሜ መሙላት ግዴታ ሊነሳላችሁ ይችላል።

ለቤተሰብዎ የሚሰጠው የመኖሪያ ፈቃድ የእርሶ መኖሪያ ፈቃድ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ብቻ ነው።

መተዳደሪያህን የመቻል ግዴታ

የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ መብትዎ ከተከበረ መተዳደሪያዎን የመቻል ግዴታ (forsörjningkrav) በሚባለው ደንብ ሊመለከቶት ይችላል። ይህም ማለት ራሶንና ቤተሰቦን የማስተዳደር ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊኖሮት ይገባል ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሰብዎ ስዊድን ሲመጣ የሚገባበት ደረጃውን የጠበቀና የቤተሰቡን ብዛት የሚመጥን የመኖሪያ ቤት ሊኖርዎት ይገባል።

የእርሶ መተዳደሪያ

ራስዎንና የመኖሪያ ፈቃድ የሚጠይቀውን ቤተሰብ አባላትን የሚያስተዳድሩበት በቅጥር መልክ የሚያገኙት ቋሚ ገቢ ያልዎት መሆኑን ማሳየት ይጠበቅቦታል። በቅጥር መልክ የሚገኝ ገቢ የሚባሉት የሚከተሉት የገቢ ምንጮች ናቸው።

 • ከሥራ የሚገኝ ደሞዝ
 • ለሥራ አጥነት የሚሰጥ ድጎማ
 • ለሕመምተኛ የሚከፈል ገንዘብ
 • በስራ የተገኘ የጡረተኛ ደሞዝ

እርስዎና የመኖሪያ ፈቃድ የሚጠይቁት የቤተሰብዎ አባላት ሊተዳደሩበት የሚያስችል ትሩፋት ያለው ከፍተኛ ሃብትና ንብረት ካለዎት፥ አንድ ማሟላት ያለብዎትን ግዴታ ተወጡ ማለት ይቻላል።

የእርሶ ገቢ

መተዳደሪያህን የመቻል ግዴታን ለመወጣት ገቢዎ ምን ያህል መሆን እንዳለበት የሚወሰነው በቤተሰቡ አባላት ብዛትና ለሚኖሩበት መኖሪያ ቤት በሚከፍሉት ወጪ ነው። ከገቢዎ ላይ የመኖሪያ ቤቱ ወጪ ከተነሳለት በኋላ (ኖርማልቤሎፕ) በቂ ገንዝብ እንዲቀርዎት ያስፈልጋል። ይህም ማለት በየወሩ የመኖሪያ ቤት ወጪ ከከፈሉ በኋላ ቀሪው ገንዘብዎ ለቀለብ፥ ለአልባሳት፥ ለንጽሕና፥ ለቴሌፎን፥ ለኤሌክትሪክ፥ ለመድህንና ለሌሎች ጥቃቅን ጊዜያዊ ወጪዎች የሚበቃ መሆን ይኖርበታል ማለት ነው።

የ2019ቱ በቂ ገንዝብ (ኖርማል ቤሎፕ)

 • 4 923 ክሮነር ለአንድ ብቸኛ ዐዋቂ ሰው
 • 8 133 ክሮነር በአንድ ቤት ለሚኖሩ ባልና ሚስት ወይም አብሮ-ነዋሪዎች
 • 2 612 ክሮነር ለልጅ፥ 6 ዓመት እስኪሞላው ድረስ
 • 3 007 ክሮነር ለልጅ፥ 7 ዓመት ወይም ከዛ በላይ ለሆነ

የመኖሪያ ቤትዎ

የቤተሰብዎን አባላት ብዛት የሚመጥንና ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት እንዲኖርዎት ያስፈልጋል። ልጅ የሌላቸው ሁለት ዐዋቂውች፥ ቢያንስ አንድ ክፍል ከኩችና ወይም የማብሰያ ቦታ ያለው ከሆነ በቂ ቤት ሊባል ይችላል። ልጆች ካሉ ግን ክፍሎቹ በዛ ማለት አለባቸው። ሁለት ልጆች አንድ መኝታ ቤት ሊጋሩ ይችላሉ።

ቤትን ከተከራይ መከራየት ችግር የለውም፥ ይሁን እንጂ የኪራይ ውሉ የአከራዩን፥ የባለቤቶች ማኅበርን ወይም የኪራይ ጉዳይ ጽ/ቤትን ዕውቅና ይሁንታ ያገኘ መሆን ይኖርበታል።

ቤቱ የቤተሰብዎ አባላት ስዊድን ውስጥ ከገቡበት ዕለት ጀምሮ ሊኖሩበት የሚችል መሆን አለበት።

ከ'መተዳደሪያህን መቻል' ግዴታ ነፃ ስለመሆን

መተዳደሪያዎን የመቻልና መኖሪያቤትን የማዝጋጀት ግዴታ ከዚህ በታች የተጠቀሰኑትን ሰዎች አይመለከትም፥

 • ከ18 ዓመት በታች ከሆንክ
 • ”የፖለቲካ ጥገኛ” ወይም ”የአማራጭ ከለላ የሚያስፈልግዎ ስደተኛ” ሆነው ፈቃድ ባገኙ ሶስት ወሮች ውስጥ የመኖሪያ ፋቃድ የሚጠይቁ የቤተሰብ አባላት ካልዎት። ይህም ተቀባይነት የሚኖረው ግን የቤተሰብ አባላቱ ባል፥ ሚስት፥ በሕግ የተመዘገበ/ች የኑሮ ጓደኛ እና ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ልጆችዎ ከሆኑ ብቻ ሲሆንና፤ በተጨማሪም ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ ባሉ አገሮች የመልሶ መገናኘት ዕድል ከሌለ ነው። በእርስዎና በጓደኛዎ ኑሮ መሃል ያለው ትዳርም በደንብ የተደላደለ መሆን ይኖርበታል። ግንኙነታችሁ ከአገሪቱ ውጭ ከተጀመረና ከተጋባችሁ ወይም አብራችሁ ለመኖር ቃል ካሰራችሁ ትዳራችሁ የተደላደለ ነው ማለት ይቻላል። ማመልከቻው በአገር ውስጥ የሚቀርብ ከሆነ፥ ግንኙነታችሁን የመሠረታችሁት ስዊድን ውስጥ በሕጋዊ መንገድ እየኖራችሁ መሆን ይኖርበታል
 • ከሐምሌ 20፡ 2016 ወይም ከዚያ ቀደም ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ያስገባ
 • የመኖሪያ ፈቃዱን የሚያራዝም የቤተሰበ አባል ካለ፥

የኑሮ ጓደኛ (samboförhållande) የሚባለው ሁለት ሰዎች ሳይጋቡ በትዳር መልክ አብረው ሲኖሩ ነው።

የቤተሰብ አባላት መሐል ስላለው ዝምድና ሰለ'መተዳደሪያህን መቻል' ግዴታ የሚሞላው ቅፅ

የቤተሰቦችዎ አባላት ስዊድን መጥተው ከእርሶ ጋር ለመኖር የመኖሪያ ፋቃድ ማመልከቻ ሲያስገቡ በቤተሰብ አባላት መሐል ስላለው ዝምድና የሚገልጹበት አንድ ቅፅ ወይም ፎርም ይደርሶታል። የ'መተዳደሪያህን መቻል' ግዴታ የሚመለከቶትከሆነ ደግሞ ራስዎንና የመኖሪያ ፈቃድ የጠየቁትን የቤተሰብ አባላትን ማስተዳደር የሚችል ገቢ እንዳልዎትና የሚመጡትን የቤተሰብ አባላት ማኖር የሚችል ብቃት ያለው ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ማዝጋጀታትዎን ማሳየት ይኖርቦታል። በቅፅ ላይ የሚሞሉት መልስ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት (ሚግራሽንቫርኬት) በቤተስብዎችዎማመልከቻ ላይ ለሚኖረው ግምት ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ በተሰጥዎት የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅፁን ሞልተው መላክም አስፈላጊ ነው።

መተዳደሪያ የመቻልና የመኖሪያ ቤት የማዝጋጀት ግዴታን የማያሟሉ ከሆነ ቤተሰቦችዎ ያስገቡት የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ ውድቅ ይሆናል።

ቋሚ ሥራና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የመኖሪያ ቤት ኮንትራትከሌልዎት፥ የቤተሰቦችዎን ጥያቄ በምንመለከትበት ወቅት የ'መተዳደሪያህን መቻል' ግዴታ ማሟላትዎን እንዲያሳዩን እንደገና ልንጠይቅዎት እንችላለን።

ማመልከቻን በጊዜ ማስገባት አስፈላጊ ነው

ቤተሰቦችዎ፥ እርስዎ ፈቃድ ካገኙበት ጊዜ በሶስት ወራት ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ ካስገቡ የ'መታዳደሪያህን መቻል' ግዴታ ማሟላት አይመለከቶትም። ስለዚህ ማመልከቻውን በማለፊያ ጊዜ ውስጥ ጠቃሚ ነው።

ማመልከቻው በፍጥነት መድረሱን ዕርግጠኛ ለመሆን የበለጠው መንገድ እርስዎ ራሱዎ የቤተሰቦችዎን ማመልከቻ በኢንተርኔት ድረገፅ ቢያስገቡ ነው። በቤተሰቦችዎ ፈንታ እርስዎ ማመልከቻውን የሚያስገቡ ከሆነ የውክልና ሥልጣን እንዲኖሮት ያስፈልጋል። የስደተኞች ጽ/ቤት፥ ማመልከቻውን ከመዘገበው በኋላ ቤተሰቦችዎ የስዊድንን ኤምበሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ለመጎብኘት ቀጠሮ እንዲይዙ ይጠየቃሉ።

የቤተሰቦችዎን ማመልከቻ በኢንተርኔት ድረገፅ ለመላክ በዚህ ይሂዱ

በቤተሰቦችዎ ፈንታ ማመልከቻ ስለማስገባት ተጨማሪማብራሪያ ያንብቡ

የውክልና ሥልጣን ምንድን ነው?

የውክልና ሥልጣን፥ አንድ አመልካች ሌላን ሰው በእሱ/ሷ ፈንታ እንደ እሱ/ሷ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲፈጽምለት በጽሁፍ መብት የሰጠበትና በፊርማው ያረጋገጠው ሰነድ ነው። አንድ የውክልና ሥልጣን፥ ለምሳሌ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ማመልከቻ እንዲያስገባለት፥ ለውሳኔ ምክንያት የሆኑትን ነጥቦች እንዲወስድ ወይም ውሳኔውን ይግባኝ እንዲልለት መብት የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። የውክልና ሥልጣን በውክልና ሰጪው የተጻፈ መሆን ይኖረታል፥ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በጠየቀ ጊዜ ዋናውን ቅጂ ማቅረብ መቻል ያስፈልጋል።

የውክልና ሥልጣን ለሌላ ሰው ሲሰጡ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አንድ ደብዳቤ ይጽፋሉ

 • የውክልና ሥልጣን መሆኑ
 • የውክልና ሰጪው ሥም፥ ዕድሜና አድራሻ
 • ውክልና ተቀባዩ እንዲያከናውን የተሰጠው መብት
 • የውክልና ተቀባዩ ሥም፥ ዕድሜና አድራሻ
 • የውክልና ሰጪው ፊርማ
 • ደብዳቤው ውስጥ የውክልና ሥልጣኑ መቼ፥ የትና ለማን እንደተሰጠ የሚያሳይ ፊርማ የሰፈረበት መሆን አለበት።

ማመልከቻውን ተከታተል

ቤተሰብዎ ማመልከቻ ካስገቡ በኋላ የዶሴ ቁጥር ወይም የጉዳይ ቁጥር (ärendenummer) ይሰጣቸዋል። በዚህ ቁጥር አማካይነት፥ ማመልከቻው በስደተኞች ጽ/ቤት መመዝገቡንና ውሳኔም ተሰጥቶት እንድሆን በድረገፅ መከታተል ይቻላል።

ማመልከቻውን ተከታተል

Last updated: 30 January 2019

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.