የስደተኛ ፈቃድ ለተሰጣቸው ሰዎች የመኖሪያ ፈቃድ ስለመስጠት
Uppehållstillstånd för dig som har fått status som flykting – amhariska
የስደተኛ ፈቃድ ከተሰጣችሁ ለሦስት ዓመት የመኖሪያ ፈቃድም ይሰጣችኋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ራሳችሁን ማስተዳደር ከቻላችሁ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
- Google+
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃዳችሁ በስዊድን ሀገር ውስጥ ለሦስት ዓመታት ለመኖር እና ለመሥራት የሚያስችል መብት ይሰጣችኋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ እንደ ማንኛውም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንደተሰጠው ሰው ሕክምና የማግኘት ተመሳሳይ መብት አላችሁ፡፡
የመኖሪያ ፈቃድ እንዳላችሁ የሚያሳይ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጣችኋል፡፡ ይህ ካር መታወቂያ ወረቅት ወይም የጉዞ ዶክመንት አይደለም፡፡ የመኖሪያ ፈቃዳችሁ ቀነ ገደብ እስካላለፈ ድረስ ከሀገር መውጣትም መግባትም ትችላላችሁ ነገር ግን ከስዊድን ውጪ ጉዞ የሚያደርጉ ከሆነ ወደ ስዊድን እንደገና ለመግባት ሕጋዊ የሆነ ፓስፖርት እና የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ እንዲኖራችሁ ግድ ይላል፡፡
በሕዝብ ምዝገባ ዶሴ ላይ መመዝገብ
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ በስዊድን ግብር ኤጄንስ ውስጥ በሚገኘው የሕዝብ መመዝገቢያ ዶሴ (ስካተቨርከት) ላይ በተቻለ ፍጥነት መመዝገብ አለብዎ፡፡ ስዊድንኛ ለስደተኞች (ኤስ ሴፍ አይ) የሚለውን ትምህርት ከመማራችሁ በፊት መመዝገብ ይርባችኋል እንዲሁም ስትመዘገቡ የስዊድን ማህበራዊ ጥበቃ ሲስተም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ መሆን አለብዎ፡፡ አንድ ጊዜ በሕዝብ መመዝገቢያ ዶሴ ላይ ከተመዘገባችሁ በኋላ የሰዊድን የመታወቂያ ዶክመንት ታገኛላችሁ፤ ይህም አስፈላጊ ነው ለምሳሌ የባንክ አካውን ለመክፈት፡፡
በስዊድን የሕዝብ መመዝገቢያ ዶሴ ላይ ለመመዝገብ ወደ ስዊድን ግብር ኤጀንሲ በመሄድ መመዝገብ ይኖርባችኋል፣ ኤጀንሲውም አድራሻዎትን፣ የትዳር ሁኔታችሁ (ያገቡ ወይም ያላገቡ እንደሆነ)፣ ዜግነታችሁን እና የትውልድ ቦታ ይመዘገባል፡፡ ወደ ግብር ኤጀንስ ሲሄዱ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዶን እና ሕጋዊ የሆነ መታወቂያ ማምጣት ይኖርባችኋል፡፡ መታወቂያዎ በስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ የተያዘ እንደሆነ ቅጂ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ቅጂው ከዋናው ጋር አንድ እደሆነ ቅጂውን በሚሰጠው ሰው መፈረም አለበት፡፡ የሚያረጋግጠውም ሰው ስሙን በትክክለኛው ፊደል (ካፒታል ሌተር) መጻፍ እና ስልክ ቁጥሩን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
በሕዝብ ምዝገባ ላይ የስዊድን ታክስ ኤጄንስ መረጃ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)
የመቋቋሚያ ድጋፍ እርምጃዎች
በቅርቡ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያገኛችሁ፥ እዚህ ሥራ ለመስራት መብት ኣላችሁ፤ ወደ ሥራው ዓለም ለመግባት ደረጃ የሚያስችል መቋቋሚያ ድጋፍ የማግኘት መብትም አላችሁ። የመቋቋሚያ ድጋፍ፥ ከሚሰጠው ዕርዳታ ውስጥ የስዊድንኛ ቋንቋ መማርን፥ ወደ ሥራው ዓለም ወደ መግባት ደረጃ የሚያደርሱና ራስን መቻልን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ይገኙበታል። የመቋቋሚያ ድጋፍን የመስጠትና ሥራ የማፈላለጉ ኃላፊነት ያለው ባለ ስልጣን፤ የስዊድን የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ተቋም (Arbetsförmedlingen) ነው።
ተጨማሪ መረጃ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ተቋም (Arbetsförmedlingen) ድረገጽ ላይ ያገኛሉ። መረጃው በተለያዩ ቋንቋዎች ቀርቧል። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)
“የስራ ማፈላለጊያ ቢሮ” (Arbetsförmedlingen)፥ ዕድሜዎ 65 ዓመት እስኪሞላ ድረስ፣ ስራ በማፈላለግ ሊረዳዎት ይችላል። ይህ ዕድሜ፡ በስዊድን የተለመደ የጡረታ ዕድሜ ነው። ዕድሜያቸው ከገፋ በኋላ ወደ ስዊድን የሚመጡ ሰዎች የሚያገኙት የጡረታ ደሞዝ አብዛኛውን ግዜ አነስተኛ ወይም ምንም ይሆናል። እርስዎ፣ ለመተዳደሪያዎ የሚበቃ የጡረታ ደሞዝ የማያገኙ ከሆነ ወደ “ጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን” (Pensionsmyndigheten) በማቅናት፥ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች የመተዳደሪያ ድጋፍ” የሚጠይቁበት (äldreförsörjningsstöd) የተሰኘውን” ማመልክቻ ሞልተው ያስገባሉ።
ስለ “በዕድሜ የገፉ ሰዎች መተዳደሪያ ድጋፍ”፡ በጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን፡ በስዊድንኛ የበለጠ ያንብቡ።
በስዊድን ሀገር ውስጥ ሥራ ስለ መሥራት
በሶስት ዓመት የጊዜ ገደብ የተወሰነ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጣችሁ፥ ስዊድን ውስጥ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ። የመኖሪያ ፈቃዳችሁ የጊዜ ገደብ በሚያበቃበት ወቅት ራሳችሁን ማስተዳደር የምትችሉበት ሥራ ካላችሁ፥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የመጠየቅ ዕድል አላችሁ።
ለስራ በሚያመለክቱበት ወቅት በስዊድን ሀገር ውስጥ ለመኖር እና ለመሥራት ፈቃድ እንደተሰጣችሁ የሚያሳዩ መረጃዎቻችሁን ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዳችሁን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡ ቀጣሪዎቻችሁ በስዊድን ሀገር ውስጥ ለምን ያኽል ጊዜ መስራት እንደተፈቀደላቸሁ ማወቅ ይፈልጋሉ እንዲሁም በስዊድን ውስት ለመስራት የተሰጥዎ ፈቃድ ምን ክከላ እንዳለበት ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡
የቤተሰብ ቅልቅል
የስደተኛ ፈቃድ ከተሰጥዎ ቤተሰቦችዎ በስዊድን ውስጥ ከእርሶ ጋር ለመኖር ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት ይችላሉ፡፡ ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት የሚችሉት ባል፣ ሚስት ወይም የተመዘገበ አጋር ወይም ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች ብቻ ናቸው ፡፡ እርሶ እና አጋርዎ ሁለታችሁም ዕድሜያችሁ ቢያንስ ከ21 ዓመት በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ወደ ስዊድን ከመምጣታችሁ በፊት አብራችሁ የኖራችሁ ልትሆኑ ይገባል፡፡ ልጆች አንድ ላይ የወለዳችሁ ከሆነ የእድሜ እገዳው ሊነሳ ይችላል፡፡ ቤተሰቦ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣቸው የሚችለው የእርሶ ፈቃድ ጊዜው ያላለቀበት እስከሆነ ድረስ ነው፡፡
ከቤተሰብ ጋር መቀላቀል የሚያስችል መረጃ ካላችሁ ማሟላት የሚገቧችሁ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ይህ ማለት ራሶን እና ቤተሰቦን በተገቢው መንገድ ማስተዳደር መቻል አለቦ ማለት ነው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቤተሰቦ ወደ ስዊድን ሲመጡ እነርሱን ጨምሮ መያዝ የሚችል በቂ ክፍሎች ያሉት እና ትክክለኛ ጥራት ያለው መኖሪያ ቤት ያስፈልጋል፡፡
ከቤተሰብ ጋር ስለመገናኘት እና ለዚህ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ተጨማሪ አንብብ፡፡
የመኖሪያ ፈቃድ ሊነጠቅ ይችላል
ለመኖሪያ ፈቃድ ሲያመለክቱ የውሸት ማስረጃ ከሰጡ፣ አውቀው ከዋሹ ወይም ለመኖሪያ ፈቃድ አስፈላጊ የሆነ ማስረጃን ሆን ብለው ከደበቁ የመኖርያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡ ወንጀል ሠርተው ተፈርዶቦት ከሆነ ፍርድ ቤት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ሊወስን ይችላል፡፡ ከዚያም የስደተኞች ኤጀንሲው የመኖሪያ ፈቃድዎን ይሰርዘዋል፡፡ ምንም እንኳ ለብዙ ዓመታት የመኖርያ ፈቃዱ የተሰጦት ቢሆንም የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ስለማራዘም
በጊዜ ገደብ የተወሰነው የመኖሪያ ፈቃድዎ በሚወድቅበት ጊዜ፥ እንደገና ማራዛም የሚችሉበት ዕድል አለዎት። አሁን ባሉበት ሁኔታም፥ ከለላ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎ ይራዘማል። ስዊድን ውስጥ ለመቆየት የሚያስችል ሌላ ምክንያት ካልዎትም፥ የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊራዘም ይችላል።
የመኖሪያ ፈቃድ ለማራዘም ምን እንዲያደርጉ የበለጠ ያንብቡ፥ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)
ይግባኝ ስለመጠየቅ
ለጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔ ይግባኝ መጠየቅ አይቻልም
የመኖሪያ ፈቃድ ይዛችሁ ወደ ስዊድን የመጣችሁ አዲስ እንግዶች የሚያስፈልጋችሁ መረጃ
የመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔ የተሰጠበትን ሰነድ በደንብ ያስቀምጡት። የመንግሥት ባለሥልጣናትና አንዳንድ ተቋማት ጋር ሲገናኙ ያሰነድ ይጠቀሙበታል።
እንደ ነዋሪ በሃገር አስተዳደር የሕዝብ መዝገብ (folkbokföring) ውስጥ እንዲመዘገቡና የስዊድን መለያ ልዩ ቁጥር (personnummer) እንዲያገኙ የቀረጥ ጽ/ ቤትን Skatteverket ሄደው ማነጋገር ያስፈልጋል።
በማኅበራዊ የመድን ስርዓት ውስጥ ለመመዝገብ ”ፎርሸክሪንግስካሳ” Försäkringskassan የሚባለውን መንግሥታዊ ተቋም ይጎብኙ።
አንዳንድ ኮሙዩኖች የሚከራዩ ቤቶችን የሚያፈላልጉ መስሪያ ቤቶች (bostadsförmedling) አሏቸው። የሚከራይ ቤት ለማግኘት ከነዚህ መስሪያ ቤቶች ዘንድ ሄደው መመዝገብ ይችላሉ። በተጨማሪ ኮሙዩኖች በአካባቢያቸው ስላሉ የግል ቤት አከራዮች መረጃ ሊሰጥዎች ይችላሉ።
የሚኖሩበት ኮሙዩን የሕፃናት እንክብካቤ ማዕከልና የልጆች ትምህርት ቤት ስላለው ለልጅዎ ያዘጋጅልዎታል።
ወደ ስዊድን የመጡት እንደ ስደተኛ ከሆነ ለመኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ቁሳቁስ መግዣ የሚሆን ገንዘብ መበደር የሚችሉበት ዕድል አለ። www.csn.se/hemutrustningslan
ጤናና ሕክምናን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት የሚኖሩበትን አውራጃ ጽ/ቤት ያነጋግሩ። በመላው አገር የጤና ጥበቃ መረጃ እዚህ ያግኙ 1177 Vårdguiden.
ስዊድንኛ ለመጤዎች (SFI) ስለሚባለውን ትምህርት ጥያቄ ካለዎት የሚኖሩበትን ኮሙዩን ጽ/ቤት ያነጋግሩ። ለተጨማሪ መረጃ ይህን ድረገጽ ይጎብኙ። Sveriges kommuner och landsting.
ሥራ በሚፈልጉበት ግዜ ሥራ ማፈላለጊያ ተቋም Arbetsförmedlingen ድረስ ሄደው ይመዝገቡ።
ዕድሜያችሁ ከገፋ በኋላ ወደ ስዊድን ለመጣችሁና በመካያው የጡረታ ደሞዛችሁ አነስተኛ ወይም ምንም ለሆነባችሁ፣ ጡረታ ጉዳይ ባለስልጣን Pensionsmyndigheten በዕድሜ የገፉ ሰዎች የመተዳደሪያ ድጋፍ (äldreförsörjningsstöd) የሚጠይቁበት፥ በስዊድንኛ ተጨማሪ ማብራሪያ አለው።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና በዩኒቨርሲቲዎች ስለሚሰጡ ትምህርቶች መረጃ ለማግኘት ወደነዚህ Antagning.se ወይም studera.nu
ድረገጻት ጎራ ይበሉ።
በትምህርት ላይ በሚቆዩበት ግዜ ስለሚሰጥ የመተዳደሪያ ገንዘብ (studiemedel) ጥያቄ ካለዎት CSN, Centrala studiestödsnämnden ይጎብኙ።
መንጃ ፈቃድን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት የትራንስፖርት ጉዳይ ጽ/ ቤትን Transportstyrelsen ማነጋገር ይችላሉ።
በፖለቲካ ጉዳይ የመምረጥና መመረጥ መብትዎን በተመለከተ የሚጠይቁት ጉዳይ ካለ Valmyndigheten ከሚባለው ባለ ሥልጣን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በስዊድን ስላለው ትምህርት ነክ ጉዳይን በተመለከተ፥ ከትምህርት ቤቶች ባለሥልጣን (Skolverket) Om svenska skolan መረጃ ይውሰዱ።
ስለ ስዊድንን ማህበራዊ ጉዳይ አጠቃላይ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች በ Information om Sverige ማግኘት ይችላሉ።
ስለ ስዊድንን ማህበራዊ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ደግሞ ይህን Svenska institutet ይህን ደረገጽ ይጎብኙ።
Hej hej Sverige! ስዊድን እንዴት እንደምትንቀሳቀሰ የሚያሳይ ቀላልና ቀሰቃሽ በሆነ መንገድ የተሰራ ፊልም መመልከት የሚችሉበት ድረገጽ ነው።
Lära svenska በ www.informationsverige.se የተባለው ድረገጽ ውስጥ ስዊድንኛ በግልዎ ሊማሩ የሚያስችሎት የተለያዩ ፕሮግራሞች ያገኛሉ።
Konsumentverkets upplysningstjänst የግዢና ሽያጭ ውልን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት መረጃ ያገኙበታል።