The Swedish Migration Agency logotype

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት/ፍረምሊንግፓስ

Främlingspass – amhariska

ኣንተ: ፓስፖርት የሌለህ: ሊኖርህም የማይችለው ባንዳንድ ምክንያት ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ወይም ሚግራኹንቬርከት ፓስፖርት ሊሰጥህ ይችላል።

ይሀንን ለምሳሌ ኣንተን ማለት ካገርህ መንግስት ሸሽተህ መጠግያ የምትፈልግ በዚህ ምክንያት ደግሞ ያገርህን መንግስት ፓስፖርት ልትጠይቀ የማትችል እንዲሁም በስዊድን ኣገር ለመኖር የመኖርያ ፈቃድ የተሰጠህን ይመለከታል።  ካገርህ መንግስት ግንኙነት በለሌበት የመጠግያ ምክንያት የመኖርያ ፈቃድ ተሰጥቶህ እንደሆነ: ለምሳሌ የሰብኣዊ ክብር ችግር: የተፈጥሮ ኣደጋ ወይም ኣጠቃላይ ያገርህ ሁኔታ: እንዲህ ከሆነ ካገርህ መንግስት ግንኙነት በማድረግ ፓስፖርት ልትጠይቅ ትችላለህ።  

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በግምገማው ለጥገኝነት ውሳኔ የተሰጠውን ምክንያት ነው እንደ መሰረት ኣድርጎ የሚወስደው: ስለሆነም በያንዳንዱ ጉዳይ ልዩ ምርመራ ያካሄዳል። ያገርህ ፓስፖርት ለማግኘት በጣም ከባድና ኣስቸጋሪ ወይም ውድ በመሆኑ ብቻ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለማግኘት በቂ ምክንያት ኣይደለም።

እንደ ፓስፖርት የሚያገለግልና ለጉዞ የሚያገለግል ሌላ ሰነድ ካለህ: ከስደተኞት ጉዳይ ጽ/ቤት የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ኣይሰጥህም። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣገሩ ውስጥ ላለው ሰው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ኣይሰጥም።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ስለ መጠየቅ  

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የምትጠይቀው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ቍ. 190011 በሞምላትና ይዘሀው ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የፈቃድ ኣሃዱ ጋ በመሄድ ነው። ይሁንና ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ ያዝ። ለያንዳንዱ ሰው ነው ቀጠሮ የሚያዝለት። እያንዳንዱ ደግሞ የራሱ ፎርም ይሞላል።  

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 190011 (በሽወደን ቋንቋ)PDF

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 191011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ)PDF

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በሚመለከት እንዴት እንደሚሞላ በተጨማሪ ኣንብብ።

ማመልከቻህን ለማቅረብ በሚቀጥለው የኢንተርነት ኣድራሻ ቀጠሮ ያዝ፤ www.migrationsverket.se/book-appointment

ከ 18 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው ህጻናት

ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በራሳቸው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ ኣይችሉም። ወላጆቻቸው ወይም ኣሳዳጊዎቻቸው ነው በኣካል ወደ ጽ/ቤት ሂደው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የሚጠይቁላቸው።  

ሁለት ኣሳዳጊዎች ቢኖሩ ሁለታቸው ለ18 ዓመት በታች ለሆኑትን  ህጻናት የሚመለከት የፈቃድ ፎርም ቍ. 246011 በሞምላት ከህጻኑ ማመልከቻ ጋር ባንድ ላይ እንዲቀርብ የሚያደርጉ።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ  ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 246011 (በሽወደን ቋንቋ)PDF

 የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ  ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 247011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ)PDF

ክፍያ

ኣብዛኞቹ ለሚያቀርቡት የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ማመልከቻ ይከፍላሉ። ማመልከቻው ስታቀርበው በካርድ ኣድርገህ ክፈል ወይም የመክፈያ ካርድ ትወስድና ቆይተህ ትከፍላለህ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ክፍያውን እስክታጠናቅቅ ግዜ ጉዳይህን መመርመር ኣይጀምርም።  

 የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ክፍያ  

ጉዳዩ ለማከናወን የሚፈዽበት ግዜ

ባሁኑ ግዜ ጉዳዩ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ ለማወቅ የስደተኞች ጽ/ቤት የኢንተርነት መረጃ ኣንብብ። ጉዳዩን የሚከታተል ሰው ተጨማሪ መረጃ የሚጠይቅህ ከሆነ በዚያ ኣኳያ ግዜው ሊራዘም ይችላል።  

የስደተኞች ጉዳይ  ጽ/ቤት ጉዳይህን ከጨረስው በኋላ: ውሳኔውን በፖስታ ኣድርገን እንልክልሃለን።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በሚመለከት ለማከናወኑ የሚወስደው ግዜ በተጨማሪ ኣንብብ።   

የእንግዳ ፓስፖርት ይውሰዱ

የእንግዳ ፓስፖርትዎን ከሌላ ቦታ እንዲያወጡ ካልተነገርዎት በስተቀር፥ የሚያወጡት ከዚያው መጀመሪያ ማመልከቻ ካስገቡበት ፈቃድ ሰጪ ጽ/ቤት ወይም አገልግሎት ማዕከል ነው። የእንግዳ ፓስፖርትዎን ከሌላ ክ/ሀገር ወይም አካባቢ ማውጣት የሚፈልጉ ከሆነ፥ ይኽንኑ ፍላጎትዎን ማመልከቻ ሲያስገቡ ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች ይንገሩ።
 
የእንግዳ ፓስፖርትዎን ለመውሰድ ሲመጡ ጊዜው የጸና መታወቂያ እንዲይዙ ያስፈልጋል።

የጉዞ ሰነድዎን ለመውሰድ የጊዜ ቀጠሮ መያዝ አይርሱ። (የቀጠሮ አገልግሎት የሚሰጠው በእንግሊዝኛና በስዊድንኛ ብቻ ነው።)

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በመጠቀም የሚደረግ ጉዞ

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የኤውሮጳ ሕብረት ፍላጎት የሚያሟላ በመሆኑ ወደ ፈልግከው ኣገር መሄድ ትችላለህ። ነገር ግን ኣንዳንድ ኣገሮች ቪዛ ይጠይቃሉ። ስለሆነም ጉዞህ ከመጀመርህ በፊት ያገሪቱን ኤምባሲ መጠየቅ ይኖርብሃል።

የተሰጠህን የመኖርያ ፈቃድ በጥገንኘት ምክንያት ከሆነ በውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ላይ ወደ ኣገርህ ወይም ወደ የተባረርክበት ኣገር ለመሄድ እንደማትችል የሚገልጽ ጽሑፍ ኣለ።

ማንነትህን ለማጠናከር ካልቻልክ: በውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ማንነትህ እንዳልተረጋገጠ ተጽፍዋል። ስለሆነም ወደ ኣንዳንድ ኣገሮች በምትጓዝበት ግዜ ችግር ሊያጋጥምህ ይችላል።  

ፓስፖርትህ  የሚያገለግልበት ግዜ

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት እንደ ተለመደው ለኣምስት ዓመት ያህል ያገለግላል፡ ሊራዘም ግን ኣይችልም። የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ከወደቀ በኋላ ሌላ የምትፈልግ ከሆነ: እንደገና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርብሃል።

ኣዲስ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ስትጠይቅ እንደገና ፎቶ መነሳትና የጣት ኣሻራ መስጠት ይኖርብሃል። ምክንያቱም ፎቶህና የጣት ኣሻራህ በኮምፕዩተር ውስጥና በፓስፖርትህ በሚገኘው የኮምፕዩተር ቺፕስ ካልሆነ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውስጥ ስላልተከማቸ ነው።

ፓስፖርትዎን ከጣሉ ወይም ከጠፋብዎት

የእንግድነት ፓስፖርትዎ (främlingspass) ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቁ፥ መጀመሪያ የሚወስዱት እርምጃ፥ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሄደው፡ ማመልከት ነው። ሌላ አዲስ የእንግድነት ፓስፖርት የሚያስፈልግዎት ከሆነ፥ አንድ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል። አዲስ የእንግድነት ፓስፖርት ፈልገው ማመልከቻ ለማስገባት ሲመጡ፥ ከፖሊስ ጣቢያው የተሰጥዎትን ወይም እቤትዎ ድረስ በፖስታ የሚላክልዎትን የፖሊስ ማመልከቻ ግልባጭ ይዘው ይምጡ።

የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ

ማመልከቻህ ውድቅ ሲሆን 

የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህና የመኖርያ ፈቃድህ የሚመለከተው ማመልከቻህ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውድቅ ሲሆን የይግባኝ ኣቤቱታ ማቅረብ ትችላለህ።

በይግባኝ ኣቤቱታው የትኛው ውሳነ እንዲቀየርልህ እንደምትፈልግና ውሳኔው ልክ ኣይደለም የምትልበት ምክንያት ደብዳበ በመጻፍ ግለጠው። በደብዳቤው ውስጥ የግል መረጃና የጉዳዩ ቍጥር መጻፍ ይኖርብሃል። ደብዳቤውን ራስህ ፈርምበት።

የመጣል ውሳኔ ከተቀበልክ ቢረዝም ከሶስት ሳምንት በኋላ የይግባኝ ኣቤቱታህ  ለስደተኞች ጽ/ቤት እንዲደርሳቸው ኣድርግ።

ሌላ ሰው ይግባኝ እንዲልልህ ከፈለግክ ለሰውየው ብቁ የጽሑፍ የውክልና ስልጣን እንድትሰጠው ይገባል።

Last updated: 22 May 2019

Was the information on this page helpful to you?