The Swedish Migration Agency logotype

የጉዞ ፓስፖርት

Resedokument – amhariska

የጉዞ ፓስፖርት ለማግኘት በ 1951 የጀነቫ ውል እንደ ስደተኛ መታወቅ ወይም ኣገር የሌለህና የ1954 የኒውዮርክ ውል ያሟላህ እንድትሆን ያስፈልጋል።    

የጉዞ ፓስፕርት የሚመለከት ማመልከቻ

የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ: መጠየቅያ በሚለው ፎርም ቍ 108021 ሞምላትና በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው የፍቃድ ኣሃዱ ማቅረብ ይኖርብሃል። ማመልከቻህን ለማቅረብ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ቀጠሮ ያዝ። ለያንዳንዱ ማመልከቻ ለማቅረብ የሚፈልግ ሰው ቀጠሮ ያዝለት።  እያንዳንዱ ሰውም የራሱ ፎርም ሞምላት ይኖርበታል።   

የጉዞ ፓስፖርት መጠየቅያ ቍ. 108021 (በሽወደንኛ ቋንቋ)PDF

የጉዞ ፓስፖርት መጠየቅያ ቍ. 109021 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ)PDF

የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ ምን ማደረግ እንደሚገባህ በተጨማሪ ኣንብብ።

ማመልከቻህን ለማቅረብ የሚቀጥለውን የኢንተርነት ኣድራሻ ተጠቅመህ ቀጠሮ ያዝ፤ www.migrationsverket.se/book-appointment

ከ 18 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው ህጻናት

ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በራሳቸው የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ ኣይችሉም። ወላጆቻቸው ወይም ኣሳዳጊዎቻቸው ናቸው በኣካል ወደ ጽ/ቤት ሂደው የጉዞ ፓስፖርት የሚጠይቁላቸው። 

ህጻኑ ሁለት ኣሳዳጊዎች ቢኖሩት ሁለታቸው መጠየቕያው ፎርም ላይ በመፈረም ስምምነታቸው መግለጽ ይኖርባቸዋል። ከኣሳዳጊዎቹ ኣንዱን ብቻ ልጁን ይዞ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ቢሄድና ማመልከቻውን ቢያቀርብ ሌላው ኣስቀድሞ በማመልከቻው ፎርም መፈረም ይገባዋል። ፊርማው በሶስተኛ ምስክር መታየት ይኖርበታል።

የህጻኑ ወላጆች በስዊድን ውስጥ የማይኖሩ ከሆነ: ማመልከቻ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚያቀርብበት ግዜ ኣሳዳጊው ወይም ሞግዚት ከርሱ ጋር መሆን ኣለበት።

ክፍያ

የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ ኣይከፈልበትም: ነገር ግን የጉዞው ፓስፖርት ስትወስደው ትከፍላለህ። የጉዞ ፓስፖርትህን ለመውሰድ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ስትመጣ በካርድ ነው የምትከፍለው። 

የጉዞ ፓስፖርት ክፍያ

ጉዳዩ ለማከናወን የሚፈዽበት ግዜ

ባሁኑ ግዜ ጉዳዩ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ ለማወቅ የስደተኞች ጽ/ቤት የኢንተርነት መረጃ ኣንብብ። ጉዳዩን የሚከታተል ሰው ተጨማሪ መረጃ የሚጠይቅህ ከሆነ በዚያ ኣኳያ ግዜው ሊራዘም ይችላል። 

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጉዳይህን ከጨረስው በኋላ: ውሳኔውን በፖስታ ኣድርገን እንልክልሃለን።

የጉዞ ፓስፖርት ለማከናወን የሚወስደው ግዜ በሚመለከት በተጨማሪ ኣንብብ።  

የጉዞ ፓስፖርት በመጠቀም የሚደረግ ጉዞ

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የኤውሮጳ ሕብረት ፍላጎት የሚያሟላ በመሆኑ ወደ ፈልግከው ኣገር መሄድ ትችላለህ። ነገር ግን በ1951 የጀነቫ ውል መሰረት ጥግተኛ ከሆንክ በፓስፖርትህ ላይ ወደ ኣገርህ ወይም ወደ የተባረርክበት ኣገር ለመሄድ እንደማትችል የሚገልጽ ጽሑፍ ኣለ።

ማንነትህን ለማጠናከር ካልቻልክ: በጉዞ ፓስፖርትህ ላይ ማንነትህ እንዳልተረጋገጠ ተጽፍዋል። ስለሆነም ወደ ኣንዳንድ ኣገሮች በምትጓዝበት ግዜ ችግር ሊያጋጥምህ ይችላል። 

ኣንዳንድ ኣገሮች ቪዛ ይጠይቃሉ። ስለሆነም ጉዞህ ከመጀመርህ በፊት ያገሪቱን ኤምባሲ መጠየቅ ይኖርብሃል።

ፓስፖርትህ  የሚያገለግልበት ግዜ

የጉዞ ፓስፖርት እንደ ተለመደው ለኣምስት ዓመት ያገለግላል: ሊራዘም ግን ኣይችልም። የጉዞ ፓስፖርትህ ከወደቀ በኋላ ሌላ የምትፈልግ ከሆነ: እንደገና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርብሃል።

ኣዲስ የጉዞ ፓስፖርት ስትጠይቅ እንደገና ፎቶ መነሳትና የጣት ኣሻራ መስጠት ይኖርብሃል። ምክንያቱም ፎቶህና የጣት ኣሻራህ በኮምፕዩተር ውስጥና በፓስፖርትህ በሚገኘው የኮምፕዩተር ቺፕስ ውስጥ ካልሆነ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውስጥ ስላልተከማቸ ነው።

የጉዞ ሰነድዎ ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቁ

የጉዞ ሰነድዎ (resedokument) ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቁ፥ መጀመሪያ የሚወስዱት እርምጃ በአቅራቢያዎ የሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሄደው ማመልከት ነው። ሌላ አዲስ የጉዞ ሰነድ የሚያስፈልግዎት ከሆነ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል። አዲስ የጉዞ ሰነድ ፈልገው ማመልከቻ ለማስገባት ሲመጡ፥ ከፖሊስ ጣቢያው የተሰጥዎትን ወይም እቤትዎ ድረስ በፖስታ የሚላክልዎትን የፖሊስ ማመልከቻ ግልባጭ ይዘው ይምጡ።

የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ

ማመልከቻህ ውድቅ ሲሆን 

የጉዞ ፓስፖርትህና የሚመለከት ማመልከቻህ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውድቅ ቢሆን የይግባኝ ኣቤቱታ ማቅረብ ትችላለህ። የመጣል ውሳኔ ከተቀበልክ ቢረዝም ከሶስት ሳምንት በኋላ የይግባኝ ኣቤቱታህ ለስደተኞች ጽ/ቤት እንዲደርሳቸው ኣድርግ።

Last updated: 23 May 2019

Was the information on this page helpful to you?