The Swedish Migration Agency logotype

የጉዞ ፓስፖርት ለመጠየቅ

Så ansöker du om resedokument – amhariska

1

ፎርሙንሙላው

የጉዞ ፓስፖርት ስትጠይቅ: በቍ.108021 በተመለከተው የመጠየቅያ ፎርም ሙላው: በኋላ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚገኘው የፈቃድ ኣሃዱ በኣካል ሂደህ ኣቅርበው። 

የጉዞ ፓስፖርት የሚፈልግ ህጻን ቢኖርህ: የህጻኖች ልዩ ማመልከቻ ኣቅርብ። ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በራሳቸው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ ኣይችሉም። ወላጆቻቸው ወይም ኣሳዳጊዎቻቸው ነው በኣካል ወደ ጽ/ቤት ሂደው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የሚጠይቁላቸው። 

ህጻኑ ሁለት ኣሳዳጊዎች ቢኖሩት ሁለታቸው መጠየቕያው ፎርም ላይ በመፈረም ስምምነታቸው መግለጽ ይኖርባቸዋል። ከኣሳዳጊዎቹ ኣንዱን ብቻ ልጁን ይዞ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ቢሄድና ማመልከቻውን ቢያቀርብ ሌላው ኣስቀድሞ በማመልከቻው ፎርም መፈረም ይገባዋል። ፊርማው በሶስተኛ ምስክር መታየት ይኖርበታል።

የጉዞ ፓስፕርት መጠየቕያ ቍ. 108021 (በሽወደን ቋንቋ)PDF

የጉዞ ፓስፖርት መጠየቅያ ቍ. 109021 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ)PDF

2

ማመልከቻህን ለማቅረብ ቀጠሮ ያዝ

ማመልከቻህን ለማቅረብ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ መያዝ ይገባሃል። የጉዞ ፓስፖርት የሚጠይቁ ሁሉ ካንተ ጋር መኖር እንዳለባቸው መርሳት የለብህም። ህጻናትን ቢሆኑ። እያንዳንዱ ማመልከቻ የሚያቀርብ ሰው የራሱ ቀጠሮ መኖር ያስፈልጋል። ለያንዳንዱ ቀጠሮ ያዝለት።   

ማመልከቻህን ለማቅረብ በሚቀጥለው  ኣድራሻ ቀጠሮ ያዝ፤ www.migrationsverket.se/book-appointment

3

ወደ የስደትኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሂድ

ማመልከቻ ስታቀርብ የሚከተሉትን ይዘህ ና፤

  • የመጠየቅያ ፎርም: የተሞላና የተፈረመ (ኣንድ ፎርም ላንድ ሰው)። ለህጻኑ የጉዞ ፓስፖርት ስትጠይቅለት ሁለቱም ኣሳዳጊዎች መፈረም እናለባችው ኣትዘነጋ።
  • ማንነትህን የሚያጠነክር ያገርህ ፓስፖርት ወይም ሌላ ተመሳሳይ ሰነድ (ሌላ ፓስፖርት የሌለህ ከሆን) ለምሳሌ የመታወቅያ ወረቀት: የልደት ምስክር: ወይም የወታደር ካርድ ሊሆን ይችላል።
  • የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጥፋቱ የሚመሰክር የፖሊስ ሪፖርት ቅጅ (ኣሮጌው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ስለጠፋብህ ኣዲስ ስትጠይቅ)።

ያገርህ ፓስፖርት ወይም የድሮ  የጉዞ ፓስፖርት ያለህ እንደሆነ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ማስረከብ ይኖርብሃል። ኣንዳንድ ግዜ ጉዳዩን የሚከታተል ሰው የፓስፖርት ቅጂ ከማመልከቻው ጋር ባንድ ላይ ይቀበላል: ሆኖም ጉዳይህ ሲመረመር ወይም ፓስፖርትህን በምትወስድበት ግዜ: ኦሪጂናሉ  ለማስረከብ ግዴታ ኣለህ።  

ማመልከቻ ስታቀርብ: የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ፎቶግራፍ ሊያነስህ እንዲሁም የጣቶችህ ኣሸራ ሊወስድ ነው። ፎቶህንና ኣሻራህን እንዲሁም ኣንተን የሚመለከት መረጃ ኮምፕዩተር ውስጥ ሊመዘገብ ነው። መረጃው የሚከማቸት በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሳይሆን በካርድ ውስጥ በሚገኘው ቺፕስ ነው። ከ6 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የጣት ኣሻራ ኣይስፈልጋቸውም።

ያገርህ ፓስፖርት ወይም እንደ ፓስፖርት የሚያገለግል ሌላ ስነድ  ለማግኘት የሚቻል ከሆነ ለማወቅ ላንዳንድ ጥያቄዎች መልስ ትሰጣለህ።  ስለሆነም ማመልከቻህን ለማቅረብ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ስትሄድ ግዜ የጥያቄ ፎርም ይሰጠሃል።

4

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጉዳዩን ይከታተላል

በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የመረጃ ኢንተርነት ባሁኑ ግዜ የጉዳዩ ፕሮሰስ ምን ያህል ግዜ እንደሚወስድ ማንበብ ትችላለህ። ጉዳዩን የሚከታተለው ሰው ተጨማሪ መረጃ ከጠየቀህ: ግዜውም በዚያ ኣኳያ ሊራዘም ይችላል። ስለዚህ ተጨማሪ ሰነዶች እንዳትጠየቅ ሰነዶችህ በሙሉ ካንተ ጋ መኖራቸውን ማረጋገጥ ይኖርብሃል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የጉዞ ፓስፖርትህን ሲመረምረው ከፖሊስ ወንጀል ምርመራም መረጃ ይላክለታል። 

የጉዞ ፓስፖርት ጉዳይ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ

5

ውሳኔን ማግኘት

ውሳኔው በፖስታ እቤትህ ድረስ ይላካል፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የጉዞ ፓስፖርት ለማግኘት መብት እንዳለህ ከወሰነ በኋላ እና የጉዞ ፓስፖርቱ ዝግጁ ሲሆን: መጥተህ እንድትወስደው እንነግርሃለን። ውሳኔ ከተሰጠበት ግዜ ኣንስቶ: ማመልከቻ ካቀረብክበት የፈቃድ ኣሃዱ ፓስፖርቱን እስክትወስድ ድረስ 14 ቀናት ኣሉ።

የጉዞ ፓስፖርትና በሚመለከት ያቀረብከው ማመልከቻ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውድቅ ሲሆን ይግባኝ ልትልበት ትችላለህ።

6

ፓስፖርትህን ለመውሰድ ቀጠሮ ያዝ

ኣንተ: ማለት የጉዞ ፓስፖርት የምትወስድ ሰውየ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ ያዝ። ፓስፖርትን ለሚወስድ ሰው ሁሉ ቀጠሮ ለመያዝ ኣትርሳ። ለልጆችህ ፓስፖርት ልታወጣላቸው ከፈለግክ ለያንዳንዳቸው ቀጠሮ ያዝላቸው።

7

የጉዞ ፓስፖርት ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ውሰደው

ፓስፖርትህ በኣካል መጥተህ ነው የምትወስደው። ከ 18 ዓመት በታች የሆኑት ህጻናት በሚመለከት ወላጅ ወይም ኣሳዳጊ ነው መጥቶ የሚወስደው። ህጻኑ መምጣት ኣያስፈልገውም።

ህጻኑን የሚያሳድግ ሰው ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚያቀርበው ማመልከቻ ኣስቀድሞ ኣሳውቆ ከሆነ ግን ከ15 ዓመት በላይ የሆነው ህጻን ራሱ መጥቶ ፓስፖርቱን ለመውሰድ ይችላል። 

የጉዞ ፓስፖርትህን ለመውሰድ መክፈል ይኖርብሃል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ስትጎበኝ የፈቃድ ኣሃዱ በሚባለው ቦታ ሂደህ ክፍያው በካርድ ክፈል።

የጉዞ ፓስፖርት ክፍያ

Last updated: 6 November 2018

Was the information on this page helpful to you?