ጥገኝነት ለሚፈልጉ ስደተኞች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ

Permanent uppehållstillstånd för asylsökande – amhariska

በስዊድን ሀገር ውስጥ በቋሚነት ለመኖር ፈቃድ የተሰጥዎ እንደሆነ በስዊድን ውስጥ እንደሚኖር እንደማንኛውም ሰው የመኖር እና የመስራት መብት ይኖርዎታል

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድዎ የሚሠራው በስዊድን ሀገር ውስጥ እስከኖሚኖሩበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው የመኖሪያ ፈቃድ እንዳለዎ የሚያሳይ ማረጋገጫ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጥዎታል ይህ ካርድ መታወቂያ ወይም ከቦታ ቦታ መዘዋወሪያ ፈቃድ አይደለም ከሀገር መውጣትም ወይም መግባት ይችላሉ፣ ነገር ግን ከስዊድን ሀገር ለመውጣት ከፈለጉ ህጋዊ ፓስፖርት ልኖርዎ ይገባል እንዲሁም ወደ ሀገር ተመልሰው ለመግባት የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ያስፈልግዎታል  ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ የሚል መረጃ ያለበትን ወረቀት በአገግባቡ ማስቀመጥ ይኖርብዎታል ሌሎች የመንግስት ወኪሎችን ለማግኘት  ከፈለጉ ይህን በጣም ጠቃሚ ማስረጃ ሆኖ ያገኙታል

የመኖሪያ ፈቃድ ጊዜዎ እንድራዘም መጠየቅ አይኖርቦትም ነገር ግን የመኖሪያ ፈቃድ ካርዱ የሚያገለግለው ለአምስት አመታት ብቻ ነው አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለማግኘት ወደ ስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ በመሄድ ፎቶ መነሳት እና እንደገና የጣት አሻራ  ማስነናት ይኖርቦታል፡፡

ስለ መኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይበልጥ አንብብ

በሕዝብ ቆጠራ ውስጥ መካተት 

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሲወስዱ በተቻለ ፍጥነት በስዊድን  ግብ ኤጄንሲ (ስካተቨርከት) የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ መመዝገብ ይኖርቦታል ስዊድንኛ ለስደተኞች (ኤስ ኤፍ አይ) ክፍልን ከመካፈልዎ በፊት እና የስዊድን ሶሻል ሴኩሪት ሲስተም ጥቅማ ጥቅምን ከማግኘትዎ በፊት በሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ መመዝገብ ይኖርቦታል፡፡  አንድ ጊዜ በሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ ከተመዘገቡ በኋላ ለእርስዎ አስፈላጊ የሆነውን የስዊድን የማንነት መታወቂያ ያገኛሉ፣  ለምሳሌ  የባንክ ሂሳብ ደብተር ለመክፈት የሚፈልጉ ከሆነ ፡፡ 

በሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ ለመመዝገብ በመጀመሪያ መኖሪያዎትን፣ የትዳር ሁኔታዎትን (ያገቡም  ያላገቡም ቢሆን)፣ ዜግነትዎን እና የተወለዱበትን ቦታ ወደሚመዘግበው ወደ ስዊድን ግብ ኤጄንስ መሄድ ይኖርቦታል ወደ ስዊድን ግብ ኤጄንስ ሲሄዱ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎን  እንዲሁም የማንነት መለያ ማስረጃ ይዘው መሄድ ይኖርቦታል የማንነት መለያ መስረጃዎ በስዊድን ፍልሰት ኤጄንስ የተያዘ ከሆነ ፎቶ ኮፒ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡  ኮፒ የተደረገው ከኦርጅናሉ ጋር አንድ አይነት ለመሆኑ ማረጋገጫ በሚሰጠው ሰው ሊፈረምበት ይገባል፡፡ ፊርማውን ያስቀመጠው ግለሰብ ሙሉ ስሙን በካፒታል ፊደላ መፃፍ እና ሰልክ ቁጥሩን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

በሕዝብ  ምዝገባ ላይ የስዊድን ታክስ ኤጄንስ መረጃ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window

የመቋቋሚያ ድጋፍ እርምጃዎች

በቅርቡ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያገኛችሁ፥ እዚህ ሥራ ለመስራት መብት ኣላችሁ፤ ወደ ሥራው ዓለም ለመግባት ደረጃ የሚያስችል መቋቋሚያ ድጋፍ የማግኘት መብትም አላችሁ። የመቋቋሚያ ድጋፍ፥ ከሚሰጠው ዕርዳታ ውስጥ የስዊድንኛ ቋንቋ መማርን፥ ወደ ሥራው ዓለም ወደ መግባት ደረጃ የሚያደርሱና ራስን መቻልን የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ይገኙበታል። የመቋቋሚያ ድጋፍን የመስጠትና ሥራ የማፈላለጉ ኃላፊነት ያለው ባለ ስልጣን፤ የስዊድን የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ተቋም (Arbetsförmedlingen) ነው።

ተጨማሪ መረጃ የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ተቋም (Arbetsförmedlingen) ድረገጽ ላይ ያገኛሉ። መረጃው በተለያዩ ቋንቋዎች ቀርቧል። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window

የቤተሰብ ዳግም መገናኘት

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት ቤተሰቦ በስዊድን ውስጥ ከእርሶ ጋር ለመኖር ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት ይችላሉ፡፡

ማሟላት የሚጠበቅብዎ መሥፈርቶች ይኖራሉ ይህም ማለት ራስዎን እና ቤተሰብዎን ማስተዳደር መቻል ይኖርብዎታል፡፡  ቤተሰቦችህ ወደ ስውድን ስመጡ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ልያኖራቸው የሚችል ሠፊ ቤተ ሊኖርህ ይገባል

ስለ ቤተሰብ ዳግም መገናኘት እና ማሟላት ስለሚያስፈልጉ ነገሮች ተጨማሪ አንብብ

የመኖሪያ ፈቃድ ሊወሰድ ይችላል

ስዊድን ሀገርን ለቀው ከሄዱ የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለስዊድን የስደተኞች ኤጄንስ የመኖሪያ ፈቃድዎን ይዘው መቆየት የሚፈልጉ መሆኑን ካሳወቁ ለሁለት ዓመታት ያክል ፈቃድዎ ምንም ሳይሆን ከስዊድን ውጭ መኖር ይችላሉ

ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ስዊድን ካልተመለሱ የስደተኞች ኤጄንስው የመኖሪያ ፈቃድዎን ሊሰርዝ ይችላል ለመኖሪያ ፈቃድ ሲያመለክቱ የውሸት መታወቂያ ከሰጡ ወይም ለመኖሪያ ፈቃድ አስፈላጊ የሆነ ማስረጃን ሆን ብላችሁ ከደበቁ የመኖርያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡

ወንጀል ሠርተው ተፈርዶብዎ ከሆነ ፍርድ ቤት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ሊወስን ይችላል፡   ከዚህም ቀጥሎ የስደተኞች ኤጄንስው የመኖሪያ ፈቃድዎን ይሰርዘዋል፡፡  ምንም እንኳ ለብዙ ዓመታት የመኖር ፈቃድ የተሰጥዎ ቢሆንም  የመኖሪያ ፈቃድዎ ሊሰረዝ ይችላል፡፡

የመኖሪያ ፈቃድህን ይዘህ መቆየት እንደሚትፈልግ ማሳወቅ

በሌላ ሀገር ውስጥ ለረጅም ጊዜ የምትቆይ ሲሆን የመኖሪያ ፈቃድህን ይዘህ መቆየት እንደሚትፈልግ ለመግልጽ የ Anmälan om att få behålla ቋሚ uppehållstillstånd ቅጽ (የቋሚ መኖሪያ ፈቃድ አንዳይወሰድ ፍላጎት ማሳወቂያ ) መሙላት ይኖርቦታል፣ ቁጥር 180611፡፡  ይህንን ቅጽ በዚህ አድራሻ ላክ migrationsverket@migrationsverket.se ወይም 

Migrationsverket
601 70 Norrköping

ይህ ማሳወቅያ የስዊድን ሀገርን ለቀህ ከመውጣትህ አንድ ሳምንት በፊት ለስዊድን የስደተኞች ኤጄንስ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ጉዞ ከተሰረዘ ለስውድን የስደተኞች ኤጄንስ ሁኔታውን ለመሄድ ካሰቡበት ቀን በፊት ማሳወቅ ይኖርቦታል፡፡

Anmälan om att få behålla permanent uppehållstillstånd, blankett nummer 186011 (በስዊድሽኛ ቋንቋ)PDF

የመኖሪያ ፈቃድ ይዞ ለመቆየት የሚሞላ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር 187011 (ባእንግሊዝኛቋንቋ)PDF

የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ወደ ስውድን በቅርብ ለገቡ ሰዎች የሚሆኑ መረጃዎች

ካዲሶች ወዳእዚህ ኣገር ለመጡexternal link, opens in new window የተለያዩ ፕሮግራሞች ስለ መብትና ግዴታ እስዊድን አገር ይገኛሉ።

ስለ መግዛት (የገዢ )ማስታወቂያና ኣገልግሎትexternal link, opens in new window ስለመግዛትና፤ውሎች ምክርና ድጋፍ ይሰጣሉ።

አንዳንድ ግዛቶች የግዛቶች የቤቶች አስተዳደር ኤጄንስ ስላላቸው የመኖሪያ ቤት መፈለግ ይቻላል፡፡፡ አስተዳደሮቹም ከግለሰቦች እንዴት መኖሪያ ቤት ማግኘት እንደሚቻል ምክር ልሰጧችሁ ይችላሉ

ከ18 ዓመት በላይ ከሆንክ የመኖሪያ ቤትህን በዕቃ ለመሙላት ብድር ለማግኘት ማመልከት ትችላለህ፡፡ www.csn.seexternal link, opens in new window

የምትኖርበት አከባቢ አስተዳዳር የሕጻናት ጥበቃ እና ለልጆች ትምህርት ያቀርባል፡፡

 የስዊደን ስደተኖችን ክፍልን አስመልክቶ ጥያቄ ቢኖርብህ የምትኖርበት አከባቢ ያለውን አስተዳደር መጠየቅ ትችላለህ፡፡  በተጨማሪም ይህንን የድረ ገጽ ተመልከት Sveriges kommuner och landsting.external link, opens in new window

ሥራ ከፈለክ በዚህ ተመዝግበህ መፈለግ ትችላለህ Arbetsförmedlingen.external link, opens in new window

ስለ ሕክምናዎች ጥያቄ ከወረዳዊ ማስተዳደሪያ ቤት ወይንም ወደ ዞባዊ ቦታ በምተኖርበት ቀበሌ ትሄዳለህ። አጥጋቢ ማስታወቂያ ለማግኘት 1177 ስልክ ደውለህ ማስተወቂያ ታገኛለህ።external link, opens in new window

በኮሌጅ እና ዩንቨርስቲ ውስጥ ለመማር መረጃ ከፈለግህ Antagning.seexternal link, opens in new window ላይ ወይም studera.nu.external link, opens in new windowላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለትምህርት ክፍያ የሚሆን ፈንድ ለማግኘት CSN, Centrala studiestödsnämnden.external link, opens in new window

የመንጃ ፈቃድን አስመልክቶ አስፈላጊውን ጥያቄ ለመጠየቅ  Swedish Transport Agency.external link, opens in new window

የመምረጥ መብትን አስመልቶ ለመጠየቅ  Valmyndigheten.external link, opens in new window

በስዊድን ሀገር ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን አስመልክቶ ከስዊድን ብሄራዊ ኤጄንስ ኦፍ ኤዱኬሽን (ስኩልቨርኬት) መረጃ በእነዚህ ውስጥ ይገኛል Skolverket nyanländaexternal link, opens in new window.

ስለስዊድን ማህበረሰብ መረጃዎች በተለያዩ ቋንቋዎች በእነዚህ ውስጥ ይገኛል Information om Sverige.external link, opens in new window

ተጨማሪ ማሰታወቂያ ስለ ስዊድን አገር እስዊድን ኢንስቲቲዩትexternal link, opens in new window ኢንተርነት ልታገኝ ትችላለህ።

በገጽ ስዊድሽኛ ለመማር www.informationsverige.seexternal link, opens in new window ኣስፈላጊዎች ማገናኞች (ሊንክስ) ብዙ ፕሮገራሞች አድርገህ የስዊድሽኛ ቋንቋ በራስህ ልትማር ትችላለህ።

Last updated: 17 April 2019

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.