በመመለስዎ የማይተባበሩ ከሆነ

Om du inte samarbetar för att återvända – amhariska

በመመለስዎ የማይተባበሩ ከሆነ የስደተኞች ኤጀንሲ የቀን አበልዎን የመቀነስ፣ በክትትል ስር የማዋል፣ ጉዞዉ እስኪተገበር ድረስ እርስዎን በቁጥጥር ስር የማዋል እና / ወይም የመመለስዎን ሓላፊነት ለፖሊስ የመስጠት መብት አለዉ፡፡

ክትትል ማለት በአንዳንድ ስፍራዎች እና ጊዜያት በቋሚነት መፈረም አለብዎት ማለት ነዉ፡፡ በተጨማሪም ፓስፖርትዎን ወይም ሌላ ማንነትዎን የሚገፁ ሰነዶችን ማስረከብ አለብዎት ማለት ነዉ፡፡

በቁጥጥር ስር መሆን ማለት፤ በስደተኞች ኤጀንሲ ድርጅት በሚመራ በተዘጋ ስፍራ ዉስጥ ታስረዉ ይቆያሉ ማለት ነዉ፡፡

ስለ እስር እና ስለ ክትትል የበለጠ ያንብቡ

ፖሊስ ስለ መመለስዎ ሙሉ ሓላፊነት መዉሰድ ይችላል

ካለመተባበርዎ የተነሳ ወደ አገርዎ መልሶ መላክ የማይቻል ከሆነ፤ የስደተኞች ኤጀንሲ ድርጅት ከሃገር የመልቀቅዎን ሃላፊነት ለፖሊስ ማስተላለፍ ይችላል፡፡ ላለመገኘት ብለዉ ከተሰወሩ፤ ፖሊሶች እርስዎን የመያዣ ፈቃድ ይዘዉ እርስዎን በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላሉ፡፡ እርስዎን ከሃገር ለማስወጣት ፖሊሶች ጉልበት የመጠቀም መብትም አላቸዉ፡፡

እርስዎን ከሃገር ለማስወጣት ፖሊሲች ሓላፊነት ከተሰጣቸዉ፤ ስለመመለስዎ ምንም አይነት ጥያቄ ካልዎት እነርሱን ማግኘት አለብዎት፡፡

ተመልሶ የመግባት እገዳ ሊያገኙ ይችላሉ

የማይተባበሩ ከሆነ፤  የስደተኞች ኤጀንሲ መልሶ የመግባት እገዳ ሊያደርግብዎት መወሰን ይችላል፡፡ ይህ ማለት በሮማንያ ወይም ቡልጋሪ ባሉ የሸንገን ሃገራት ከ አንድ እስከ አምስት ዓመታት ያህል መጓዝ አይችሉም ማለት ነዉ፡፡ መልሶ የመግባት እገዳዉ ርዝመት በዉሳኔዎት ላይ ይገኛል፡፡

ስለ መልሶ የመግባት እገዳዉ እና እንዴት እንደሚያስወግዱት የበለጠ ያንብቡ

ስለ መለሶ የመቋቋሚያ ዕገዛ ቅድመ ሁኔታዎች የበለጠ ያንብቡ

Last updated: 22 August 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.