ተመልሶ መግባት የሚከለከልባቸው ሁኔታዎች

Återreseförbud – amhariska

በውሳኔዎ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከስዊድን ካልወጡ ወደ ስዊድን ተመልሶ የመግባት እገዳ ሊጣልብዎ ይችላል። በዚህ ጊዜ ወደ ሼንጌን አካባቢ አገራት ወይም ወደ ሮማንያ፣ ቡልጋሪያ እና ክሮሺያ ለተወሰነ ጊዜ መግባት አይችሉም፡፡ የስዊድን የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ እርሶ በፍቃደኝነት አገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ ካላመነ ተመልሶ ወደ ስዊድን የመግባት እገዳ ይጣልብዎታል፡፡

ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረግ ወደ አገር ውስጥ መግባትን የሚከለክል ውሳንኔ ከተላለፈብዎ፣ ሁልዜም የመግባት እገዳ ይጣልብዎታል።

ሌሎች ተመልሶ መግባት የሚከለከልባቸው ምክንያቶች

የስዊድን የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ እርሶ በፍቃደኝነት አገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ ካላመነ የሸንገን አካባቢን የሚሸፍን እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ተመልሶ የመግባት እገዳ ሊጣልብዎ ይችላል። ለምሳሌ ተመልሰው ለመግባት ከሚከለከሉባቸው ሁኔታዎች መካከል

  • ቀደም ሲል  ራስዎንደብቀው ከነበረ
  • ስዊድንን ለቀው የመውጣት ሃሳብ እንደሌለዎ ተናግረው ከነበረ
  • ሃሰተኛ የማንነት መግለጫ ተጠቅመው ከሆነ ወይም የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው የእርሶን ትክክለኛ ማንነት እንዲያውቅ ትብብር ያላደረጉ ከነበረ
  • ሆነ ብለው የተሳሳተ መረጃ ቢሰጡ ወይም ስለእርሶ ጠቃሚ መረጃዎችን ቢደብቁ
  • ለእስራት የሚያበቃ ወንጀል ፈፅመው ከሆነ

ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች በአንዱ ተመልሶ የመግበት ፈቃድ የተከለከሉ ከሆነ  በፈቃደኝነት የሚመለሱበትን ጊዜ ሳይጠብቁ በፍጥነት አገሪቱን ለቀው መውጣት አለብዎ

በፈቃደኝነት የሚመለሱበትን ጊዜ አለመጠበቅ  በተጨማሪ ከስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ማግኘት የነበረብዎትን የመኖሪያና የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት ያሳጣዎታል፡፡ (ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች አገሪቱን ስዊድንን ለቀው እስኪወጡ ድረስ ዕለታዊ ድጎማቸውን በመቀበል የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ባዘጋጀው ቦታ መቆየት ይችላሉ፡፡)

በፈቃደኝነት የመመለሻ የጊዜ ገደቡን ማክበር

ከሃገር የሚወጡበት ውሳኔ ከተላለፈ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ውስጥ ስዊድንን ለቀው መውጣት አለብዎ፡፡ ምን ያህል የመቆያ ጊዜ እንዳለዎ በውሳኔው ላይ ተገልጿል፡፡

ልዩ ምክንያት ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ ሃገሪቱን ለቀው የሚወጡበት ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥዎት ይችላል፡፡ ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ለስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው በፍጥነት ማሳወቅ አለብዎ፡፡

ሃገሪቱን ለቀው ከመውጣትዎ በፊት የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው አገሪቱን ለቀው መውጣትዎን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ይሰጥዎታል።  የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው ከሃገር መውጣትዎን ማረጋገጥ እንዲችል የስዊድንን የድንበር ጥበቃ ሲያልፉ  የተሰጠዎትን የምስክር ወረቀት በዛ ለሚገኙ የኤጀንሲው ሰራተኞች ማስረከብ አለብዎ። በተለያዩ ምክንያቶች የምስክር ወረቀቱን ማስረከብ ባይችሉም እንኳን ለምሳሌ ፓስፖርትዎን እና የጉዞ ቲኬትዎን በማሳየት ከስዊድን በትክክለኛው ሰዓት መውጣትዎን ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ ድንበሩን መሻገርዎን የሚያሳየውን ማስረጃ በአቅራቢያዎ ለሚገኝ የስዊድን ኤምባሲ  ወይም ቆንፅላ ጽ/ቤት ማቅረብ ወይም በስዊድን ለሚገኘው የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ኮፒውን በፖስታ መላክ ይችላሉ፡፡ ወደ ስዊድን ተመልሶ የመግባት እገዳ እንዳይጣልብዎ ከፈለጉ በትክክለኛው ሰዓት ሃገሪቱን ለቀው የወጡበትን ማስረጃ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ የእርሶ ሃላፊነት ነው፡፡

በተወሰነልዎት የጊዜ ገደብ ውስጥ ስዊድንን ለቀው መውጣትዎን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ የሃገሪቱ የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ተመልሶ የመግባት እገዳውን ሊያነሳልዎት ይችላል፡፡

ተመልሶ የመግባት እገዳው የማይተገበርበት ሁኔታ

የስዊድን የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲ የእርስዎን የግል ሁኔታዎች ከግንዛቤ በማስገባት ተመልሶ የመግባት እገዳን ሊያስቀርልዎት ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው ለምሳሌ በአንድ የሸንገን  አገር የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ልጆች ካለዎ ነው፡፡

የሚከተሉት አገራት በ ሼንጌን ስምምነት ውስጥ የተካተቱ ናቸው

ኦስትሪያ፣ቤልጄም፣ቼክ ሪፐብሊክ፣ዴንማርክ፣ኢስቶኒያ፣ፊንላንድ፣ፈረንሳይ፣ጀርመን፣ግሪክ፣ሀንጋሪ፣አይስላንድ፣ጣሊያን፣ላቲቪያ፣ሊቱኒያ፣ሎክሰምበርግ፣ማልታ፣ኔዘርላንድ፣ኖርዌይ፣ፖላንድ፣ፖርቹጋል፣ስሎቫኪያ፣ስሎቬኒያ፣ስፔን፣ስዊድን እና ስዊዘርላንድ።

Last updated: 30 January 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.