አቤቱታ ማቅረብ ከፈለጉ

Om du vill överklaga – amhariska

የስደተኞች ኤጀንሲ ውሳኔ ለጥገኝነት ያቀረቡትን የእርስዎን ማመልከቻ አልተቀበለም ማለት እርስዎ በስዊድን ውስጥ የመኖር ፈቃድ የለዎትም ማለት ነው።  ውሳኔውን መቀበል ወይም አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ። አቤቱታ ለማቅረብ ቢወስኑም ለመመለስ ዕቅድ ማዘጋጀት አለብዎት።

በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤትን የተወሰደው ውሳኔ የማይቀበሉት ከሆነ ይግባኝ የመጠየቅ መብትዎ የተጠበቀ ነው። ይግባኙን የሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ነው፣ ይሁን እንጂ የይግባኝ ማመልከቻውን የሚልኩት ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ይሆናል። የታወቀ ረዳት ካልዎት እሱ ወይም እስዋ ሊተባበርዎት ይችላል ወይም ትችላለች። በውሳኔው መግለጫ ላይ ይግባኝ የሚጠይቁበት የጊዜ ገደብ አለ፣ አብዛኛውን ጊዜ የውሳኔውን ግልባጭ ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ ሶስት ሳምንት ያህል ጊዜ ይኖራል።

ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ውስጥ በእርስዎ ጉዳይ በተወሰነውን ውሳኔ ዓይነት መሰረት  የአቤቱታውን ቀነ ገደቦች ይችላሉ።

የስደተኞች ፍርድ ቤት የእርስዎን አቤቱታ ይመረምራል

የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔው ይለወጥ ወይም አይለወጥ ለማየት መጀመሪያ የእርስዎን አቤቱታ ይቀበላል። የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን ለመለወጥ ምንም ዓይነት ምክንያት ካላገኘ፣ የእርስዎ አቤቱታ ወደ ስደተኞች ፍርድ ቤት ይላካል። ፍርድ ቤቱም ውሳኔውን ቀይሮ ለእርስዎ ሊወስን ወይም ከስደተኞች ኤጄንሲ ጋር ሊስማማ ይችላል።

የስደተኞች ፍርድ ቤት አንዴ የእርስዎን አቤቱታ ከተቀበለ፣ ስለ እርስዎ አቤቱታ ወይም ስለ ሂደቱ ማንኛውንም ጥያቄዎች መመለስ ያለብዎት ለስደተኞች ኤጄንሲ ሳይሆን ለፍርድ ቤቱ  ነው። የእርስዎ ጉዳይ አንዴ ወደ ፍርድ ቤት ከተላከ በኋላ የስደተኞች ኤጄንሲ ከአማካሪዎ ጋር ለመገናኘት የሚያደርጉትን የጉዞ ወጪዎች  አይከፍልም።

ሀሳብዎትን ከለወጡ እና አቤቱታዎትን ማንሳት ከፍለጉ፣ የመጀመሪያውን ውሳኔ መቀበልዎትን ለስደተኞች ኤጄንሲ ማስወቅ ይችላሉ። ከዚያም የእርስዎ አቤቱታ አይመረመርም፤ በውሳኔውም ላይ ከአሁን በኋላ አቤቱታ ማቅረብ አይችሉም።

አቤቱታ እንዴት ይጽፋሉ

የስደተኞች ኤጄንሲው ውሳኔ ላይ አቤቱታ ማቅረብ ከፈለጉ የስደተኞች ኤጄንሲው እንዲለውጥ የሚፈልጉትን ውሳኔ እና ለምን እንዲለወጥ እንደፈለጉ በመግለጽ ደብዳቤ መጻፍ አለብዎት። የእርስዎን ምክንያቶች የሚደግፉ ዶክመንቶችን (ዋናውን ቅጅ ቢሆን ይመረጣል) ወይም ሌሎች መረጃዎችን ያካትቱ።

የእርስዎ አቤቱታ የእርስዎን የግል መረጃ እና የጉዳዩን ቁጥር ያካተተ መሆን አለበት። የጉዳዩ ቁጥር በእርስዎ የጥገኝነት ፈላጊነት ካርድ ላይ ( በስዊድን LMA ውስጥ) ይገኛል። ስልክ ቁጥርን እና የስደተኞች ኤጄንሲው እና የስደተኞቹ ፍርድ ቤት እርስዎን ማግኘት የሚችሉበትን አድራሻ ያካትቱ።

የእርስዎ አቤቱታ ከቀነ ገደቡ በፊት ለስደተኞች ኤጄንሲ መድረሱ በጣም አስፈላጊ ነው። ከዚህ በታች በውሳኔው ዓይነት ላይ ተመስርቶ፣ በእርስዎ ጉዳይ ላይ የጊዜውን ቀነ ገደብ ማየት ይችላሉ።

አቤቱታውን ራስዎ ማቅረብ የማይችሉ ከሆነ፣ ሌላ ሰው እንዲያቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ። በዚያ ሁኔታ ውስጥ ለስደተኞች ኤጄንሲ የውክልና ማስረጃ ማስገባትአለብዎት።

የውክልና ሥልጣን ምንድን ነው?

የውክልና ሥልጣን፥ አንድ አመልካች ሌላን ሰው በእሱ/ሷ ፈንታ እንደ እሱ/ሷ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲፈጽምለት በጽሁፍ መብት የሰጠበትና በፊርማው ያረጋገጠው ሰነድ ነው። አንድ የውክልና ሥልጣን፥ ለምሳሌ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ማመልከቻ እንዲያስገባለት፥ ለውሳኔ ምክንያት የሆኑትን ነጥቦች እንዲወስድ ወይም ውሳኔውን ይግባኝ እንዲልለት መብት የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። የውክልና ሥልጣን በውክልና ሰጪው የተጻፈ መሆን ይኖረታል፥ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በጠየቀ ጊዜ ዋናውን ቅጂ ማቅረብ መቻል ያስፈልጋል።

የውክልና ሥልጣን ለሌላ ሰው ሲሰጡ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አንድ ደብዳቤ ይጽፋሉ

  • የውክልና ሥልጣን መሆኑ
  • የውክልና ሰጪው ሥም፥ ዕድሜና አድራሻ
  • ውክልና ተቀባዩ እንዲያከናውን የተሰጠው መብት
  • የውክልና ተቀባዩ ሥም፥ ዕድሜና አድራሻ
  • የውክልና ሰጪው ፊርማ
  • ደብዳቤው ውስጥ የውክልና ሥልጣኑ መቼ፥ የትና ለማን እንደተሰጠ የሚያሳይ ፊርማ የሰፈረበት መሆን አለበት።

በውሳኔው ላይ ለስደተኞች ፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረብ ከፈለጉ

የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት በሚሰጠው ፍርድ ቅሬታ ካልዎት፥ የፍርዱ ውሳኔ ግልባጭ በደረስዎት በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለስደተኞች ጉዳይ የበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት ይችላሉ። የስደተኞች ጉዳይ የበላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻው ተቋም ነው፣ በዚህ ተቋም የሚሰጠው ውሳኔም የስድተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትና የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ለሚወስዱት አቋም ሁሉ እንደ መመሪያ ይሆናል።

የስደተኞች ይግብኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሚያየው የተወሰኑ ጉዳዮችን ብቻ ነው፣ ይህም አጋጥመው የማያውቁ (በዚህም ምክንያት መመሪያ የሌላቸው) ስሆኑ ወይም በስደተኞች ፍርድ ቤት በትክክል ያልተያዙ ሲሆን ነው። አብዛኛዎቹ አቤቱታዎች ወደ በስደተኞች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርገዋል። ይህም ማለት  በእነዚያ ጉዳዮች ላይ በስደተኞች ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ የጸና ይሆናል።

ለተለያዩ ውሳኔዎች የሚሰጡ የተለያዩ የአቤቱታ ማቅረቢያ ቀነ ገደቦች

የስደተኞች ኤጄንሲ የማስረከቢያ ቀነ ገደብ ከማለፉ በፊት የእርስዎን አቤቱታ መቀበል አለበት።  የስደተኞች ፍርድ ቤት ውሳኔ ላይ አቤቱታ የሚያቀርቡ ከሆነ፣ ቀነ ገደቡ ከማለፉ በፊት ወደ ፍርድ ቤቱ መላክ አለብዎት።  የሚቀበሉት የውሳኔ ወረቀት በእርስዎ ጉዳይ ላይ ቀነ ገደቡ መቼ እንደሆነ ይገልጻል።

ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ በውሳኔው ላይ አቤቱታ ማቅረብ የማይችሉ ሲሆን፣ ይህም ሕጋዊ ሃይል አግኝቷል ይባላል።

 የአቤቱታዎች ማቅረቢያ ቀነ ገደብ

ተቀብለዋል

አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ

የማስወጫ ትዕዛዝ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

ወዲያው ተፈፃሚ የሚደረግ የመግባት ክልከላ ውሳኔወዲያው ተፈፃሚ የሚደረግ የመግባት ክልከላ ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በስደተኞች ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በሁኔታ መግለጫ ላይ የተሰጠ ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በጉዞ ወረቀት ላይ የተሰጠ ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በውጭ ዜጋ ፓስፖርት ላይ የተሰጠ ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

እርስዎ ስዊድንን ለቀው ባለመውጣትዎ ወደ ሸንገን ሃገሮች በድጋሚ እንዳይገቡ መከልከል

የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን ካስተላለፈ በኋላ ባሉት በሦስት ሳምንታት ውስጥ

በሌላ ምክንያት የተሰጠ በድጋሚ ያለመግባት ክልከላ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በልዩ ድጋፍ ላይ የተሰጠ ውሳኔ

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

የቀን አበል ቅነሳ ወይም ማቋረጥ ላይ የተሰጠ ውሳኔ

የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን ካስተላለፈ በኋላ ባሉት በአምስት ሳምንታት ውስጥ

የእርዳታ ሁኔታ አማራጭ መግለጫ (ካመኑ የጥገኝነት ደረጃ ይስጥዎታል)

የውሳኔ ግልባጭ ከደረስዎት ቀን ጀምሮ በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

በማንኛውም ሰዓት ቁጥጥር ሥር የማድረግ እና በእስር ቤት ውስጥ የማዋል ውሳኔ

በማንኛውም ሰዓት

ውሳኔውን ከተቀበሉ እና መቀብልዎን ገልፀው ከፈረሙ በኋላ

  • በውሳኔው ላይ አቤቱታ ማቅረብ አይችሉም
  • የስደተኞች አቤቱታ ሰሚ ፍርድ ቤት  የእርስዎን ጉዳይ ላለማየት ያሳለፈው ውሳኔ
  • ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያሰጥ ውሳኔ

Last updated: 21 April 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.