ወዲያው ተግባራዊ የሚደረግ ክልከላ

Avvisning som ska genomföras omedelbart – amhariska

የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ከለላ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ለመጠየቅ የሚያስፈልግ ምክንያት ከሌለዎት ወዲያውኑ ተግባራዊ  የሚደረግ የፈቃድ ክልከላ ትእዛዝን ጽሑፍ ይሰጣል። እንደዚያ ዓይነት ትእዛዝ ከተቀበሉ፣ ወዲያውኑ ስዊድንን ለቀው መሄድ አለብዎ።

የእርስዎን ማመልከቻ ያለመቀበል  ውሳኔው ለአራት ዓመታት ያህል ሥራ ላይ ይውላል። ወዲያውኑ ተግባራዊ የሚደረገው አገር ውስጥ መግባትን የሚከለክለውን ትእዛዝ  ከደረሰዎ፣ ወደ አገር ውስጥ መልሶ የመግባት እገዳ እንዲጣልብዎ ያደርጋል፤ ማለትም በማንኛውም በሸንገን አገሮች ውስጥ፣ ወይም ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያህል  ወደ ሮማኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ እና ክሮሽያ መግባት አይችሉም።

ትእዛዝን መቀበል

መቀበልዎትን የሚገልጸው ወረቀት ላይ በመፈረም ትእዛዙን መቀበልዎትን ማሳየት ይችላሉ። መግለጫውን አንድ ጊዜ ከፈረሙ በኋላ፣ መልሰው አቤቱታ ማቅረብ የማይችሉ ሲሆን ስዊድንን ወዲያውኑ ለቀው መሄድ አለብዎት። ምንም እንኳን ትእዛዙን ባይቀበሉትም አንዴ ትእዛዙ ከደረሰዎ ስዊድንን ለቀው መሄድ ይኖርብዎታል።

ትእዛዙ ላይ አቤቱታ ማቅረብ

ትእዛዙን የማይቀበሉ ከሆነ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለዎት፣ ነገር ግን ወዲያውኑ ስዊድንን ለቀው መሄድ አለብዎት። የእርስዎ አቤቱታ ትእዛዙን ካወቁት በኋላ ቢያንስ በሦስት ሳምንታት ውስጥ በስደተኞች ኤጄንሲ ተቀባይነት ማግኘት አለበት።

ትእዛዙን ተቃውመው አቤቱታ ስለማቅረበ ተጨማሪ ያንብቡ።

የመልስ ጉዞዎትን ስለማቀድ

ትእዛዙን እንደተቀበሉ ወዲያውኑ ስዊድንን ለቀው መሄድ ይጠበቅብዎታል። ወደ አገርዎ የመመለስ ጉዞ እቅድ መያዝ፣ ሕጋዊ የሆነ ፓስፖርት መያዝ፣ እና ወደ አገርዎ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወደሚያገኙበት ወደ ሌላ አገር ለመመለስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ነገሮችን መያዝ የእርስዎ ኃላፊነት ነው።  የስደተኞች ኤጄንሲ ከ ትውልድ አገርዎ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ወይም የጉዞውን ትኬት በመግዛት ሊያግዝዎት እና ሊረዳዎት ይችላል።

በፈቃደኝነት ስለመመለስ ተጨማሪ ያንብቡ

መስተንግዶ፣  የባንክ ካርድ፣ እና የጥገኝነት ፈላጊዎች ካርድ

ትእዛዙን ከተቀበሉ ከሦስት ሳምንታት በኋላ አቤቱታ ማቅረብ አይችሉም። ይህም ማለት ከእንግዲህ ወዲያ ከስደተኞች ኤጄንሲ መስተንግዶና የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት አይኖርዎትም።  እርስዎ የሚያሳድጉት ከ18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ ጋር የማይኖሩ አዋቂ ሰው ከሆኑ ይህ በእርስዎ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል።

ስዊድንን ለቀው ከመሄድዎ በፊት የጥገኝነት መጠየቂያ ካርድዎን (LMA-card) ወደ ስደተኞች ኤጄንሲ መመለስ አለብዎት ከስደተኞች ኤጄንሲ የባንክ ካርድ ተቀብለው ከሆነ፣ ገንዘቡን ከሂሳብዎ ውስጥ አውጥተው ካርድዎን መመለስ አለብዎት።  በአንዱ የስደተኞች ኤጄንሲ ማስተናገጃ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፣ ማስተናገጃውን መልቀቅ እና ቁልፉን ማስረከብ አለብዎት።

የጤና እንክብካቤ እና ትምህርት ቤት

ስዊድንን ለቀው እስከሚሄዱበት ቀን ድረስ ቀድሞ እንደነበረዎት አይነት የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት አለዎት፤ ነገር ግን ለቀው እንዲሄዱ የሚያዘው ትእዛዝ ተግባራዊ ከተደረገ ለመድኃኒት እና ለጤና ህክምና ምንም ዓይነት የገንዘብ ክፍያ የማያገኙ ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ ማግጀት የሚችሉበት የግዜ ገደብም ያበቃል። 

ልጆች ስዊድን እስካሉ ድረስ ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ መብት አላቸው።

ስለ ልጆች እና ስለጥገኝነት የበለጠ ያንብቡ

ውሳኔውን የማያከብሩ ከሆነ

ስዊድንን በመልቀቅ የማይተባበሩ ከሆነ፣ የስደተኞች ኤጄንሲ በቁጥጥር ሥር ሊያውልዎት ወይም በእስር እንዲቆዩ ሊወስን ይችላል። ቁጥጥር ማለት የስደተኞች ኤጄንሲ ወይም በመደበኛነት ከፖሊስ ጋር መፈረም አለብዎት ማለት ነው።  በእስር ቤት ከቆዩ፣ ለቀው እስኪወጡ  ድረስ በዝግ በሆነ ተቋም ውስጥ መቆየት አለብዎት ማለት ነው።

እስከ አሁንም ድረስ ከስደተኞች ኤጄንሲ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት ካለዎት (ለምሳሌ፦ ልጆች ያላቸው ቤተሰቦች)፣ አገሪቱን ለቀው ለመሄድ የማይተባበሩ ከሆነ መጠኑ የቀነሰ የውሎ አበል ሊቀበሉ ይችላሉ።

የስደተኞች ኤጄንሲ ትእዛዙን ለማስፈጸም ኃይል መጠቀም አለብኝ ብሎ ከወሰነ፣ ኃላፊነቱን የሚወስደው የስዊድን ፖሊስ ነው።

ውሳኔውን የማያከብሩ ከሆነ ምን እንደሚከሰት ለማወቅ ተጨማሪ ያንብቡ።

ተቀባይነት ካጣ በኋላ የሚኖሩ አዲስ ክስተቶች

ለመመለስ የማይችሉበት ሁኔታ ከተፈጠረ፣ ለእርስዎ የእንግዳ ተቀባይ ክፍል መናገር አለብዎት። የስደተኞች ኤጄንሲ ከአገር ለማስወጣት አስቸጋሪ እንቅፋቶች መኖራቸውን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባል እነዚህ እንቅፋቶች ውሳኔውን ከተቀበሉ በኋላ በተከሰቱ ሁኔታዎች ምክንያት ከተገኙ አዳዲስ መረጃዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆን አለባቸው።

ተቀባይነት ካጡ በኋላ ስለሚፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶች የበለጠ ያንብቡ

የሚከተሉት አገራት በ ሼንጌን ስምምነት ውስጥ የተካተቱ ናቸው

ኦስትሪያ፣ቤልጄም፣ቼክ ሪፐብሊክ፣ዴንማርክ፣ኢስቶኒያ፣ፊንላንድ፣ፈረንሳይ፣ጀርመን፣ግሪክ፣ሀንጋሪ፣አይስላንድ፣ጣሊያን፣ላቲቪያ፣ሊቱኒያ፣ሎክሰምበርግ፣ማልታ፣ኔዘርላንድ፣ኖርዌይ፣ፖላንድ፣ፖርቹጋል፣ስሎቫኪያ፣ስሎቬኒያ፣ስፔን፣ስዊድን እና ስዊዘርላንድ።

Last updated: 30 January 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.