የመልሶማቋቋሚያድጋፍበሀገርዎ

Stöd till återetablering i hemlandet – amhariska

የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነ እና እርሶዎ ወደ ሀገርዎ የሚመለሱ ከሆን፤  ከስዊድን የስደተኞች ቦርድ (ሚግራሾንስቨርክ) የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት የማመልከት እድል አለዎት። ማመልከቻ ለገንዘብ እርዳታ ማቅረብ ይችላሉ፤ በተጨማሪ እርሶዎን ወደ ሀገርዎ ተመልሰው ለማቋቋም ይችሉ ዘንድ፤ ወደ ህብረሰቡ ተመልሰው ለመቀላቀል፤ ሁኔታዎች ለማመቻቸት የመልሶማቋቋሚያ የተባለውን ድጋፍ  ይሰጥዎታል።   

የመልሶማቋቋሚያየገንዘብድጋፍ

የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት እድል የሚሰጠው፤ እንደርሶ የመሰለ ወደ ሀገሩ ለመመለስ ዕቅድ ያለው፤ ሆኖም ባገሩ ባለው ችግር እና ግጭት ምክንያት፤ ወደ ሀገሩ ተመልሶ የማቋቋምና የመደራጀት የተወሰነ ፈንታ ሊያጋጥመው የሚችል ሰው ነው።    

የስደተኞች ቦርድ ባሁኑ ጊዜ ያለው ግንዛቤ፤ ቀጥሎ ወደ ተዘረዘሩት አገሮች ለሚመለሱ ሰዎች፤ የመልሶ ማቋቋሚያ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

አፍጋኒስታን፥ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፥ ዲሞክራስያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ፥ አይቮሪ ኮስት፥ ኤርትራ፥ ኢራቅ፥ የመን፥ ላይቤሪያ፥ ሊቢያ፥ ማሊ፥ ሴራሊዮን፥ ሶማሊያ፥ ፍልስጤም፥ ሱዳን፥ ደቡብ ሱዳን፥ ሶርያ እና ቻድ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻልና ስለ ገንዘቡ ድጋፍ ተጨማሪ ማብራሪያ እዚህ ያገኛሉ።  

ተመልሰው  ከህብረተሰቡ ጋር ለማወሃድ ድጋፍበሀገርዎ

ወደ ሀገርዎ ተመልሰው እንደገና ከህብረተሰቡ ጋር ለመቀልቀል ይቻልዎት ዘንድ፤ የመልሶ ማቋቋሚያ  የተባለውን ድጋፍ  ይሰጥዎታል። የድጋፉ ተቀባይ የመሆን እድል የሚያገኙት፤ ወደ አገርዎ የመመለስ እቅድ ካልዎትና፤ ለምሳሌ ወደ ስራ ገበያ ለመግባት እርዳታ የሚያስፈልግዎት ወይም የጠበቃ ምክር የሚያስፈልግዎት ከሆን ነው። 

በዚሁ ጊዜ እርዳታ የማግኘት እድል ያላቸው፤ ከአፍጋኒስታን፥ ኢራቅ (ኩርዲስታን)፥ ዒራቅ (ማዕከላዊና ደቡባዊ)፥ ማሮኮ፥ ፓኪስታንና ሩስያ ናቸው።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻልና ስለ፤ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ተጨማሪ ማብራሪያ እዚህ ያገኛሉ። (በእንግሊዝኛ)

Last updated: 2017-10-19

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.