የመልሶ ማቋቋሚያ የገንዘብ ድጋፍ

Ekonomiskt stöd till återetablering – amhariska

እርሶዎ አገርዎ የሚመለሱ ከሆኑ ከስዊድን የስደተኞች ቦርድ (ሚግራሾንስቨርክ) የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት የማመልከት እድል አለዎት። የእርዳታው አላማ እርሶዎ  ወደ ሀገርዎ  በሚመለሱበት ወቅት፤ ግጭት ያለበት ቦታ መሆኑ፤ እርሶዎን መልሶ ለማቋቋም ችግር እንዳይገጥሞዎት ተብሎ የታሰበ ነው። እርሶዎ ድጋፍን ለማግኘት ማመልከት ያለቦዎት ስዊድን ሀገር ውስጥ እስካሉ ድረስ ብቻ ነው።

እርስዎ  የሚመለሱበት አገር፤ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት አገሮች በአንዱ ውስጥ ከሆነ ለመመለስ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ:

አፍጋኒስታን፥ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፥ ኮንጎ፥ በአይቮሪ ኮስት፥ ኤርትራ፥ ኢራቅ፥ የመን፥ ላይቤሪያ፥ ሊቢያ፥ ማሊ፥ ሴራሊዮን፥ ሶማሊያ፥ ፍልስጤም፥ ሱዳን፥ ደቡብ ሱዳን፥ ሶርያ እና ቻድ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ።

ድጋፍለማግኘትየሚያስችሉሁኔታዎች

እርስዎ ከሚከተሉት ዝርዝሮች ውስጥ ከሆኑ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፥

 • የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነ ወይም እርስዎ ስዊድን ውስጥ ጥገኝነት የጠየቁትን ማመልከቻዎን በገዛ ፈቃድዎ ያቋረጡት ከሆነ
 • እርስዎ በፈቃደኝነት ወደ ሀገርዎ ለመመለስ ከወሰኑና ለማቋቋሚያ የሚያስችሉ ሁኔታዎች በተለያዩ ምክንያት ከባድ ሁነው ሲገኙ
 • በሀገርዎ ተመልሰው ለመኖር የሚይስችል ሁኔታ አለ ተብሎ ከታመነበት
 • በስዊድን ሀገር ውስጥ ሆነው የማቋቋሚያ ማመልከቻ ቅፅ ሞልተው ያስገቡ እንደሆን ነው።

ለቤተሰብዎድጋፍ

የእርስዎ የቤተሰብ አባላት የእርስዎ ባል፥ ሚስት፥ ጓደኛ፥ ከእርስዎ ጋር የሚኖሩ ወይም የቅርብ ዘመዶች ከ18 ዓመት በታች በታች የሆኑ ልጆች ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።  የእርስዎን ማመልከቻ ቅፅ ሞልተው በሚያስገቡበት ጊዜ  የቤተሰብ አባላትን ድጋፍ ለማግኘት የግዴታ እርሶዎ በሲውድን ሀገር ውስጥ ሆነው ነው ማመልከት ያለብዎት።

ማመልከቻውንተንተርሶየሚሰጥውሳኔ

የጥገኝነት ማመልከቻዎ ተቀባይነት ካላገኝ፤ ወይም የጠየቁትን ጥገኝነት ማመልከቻዎን በገዛ ፈቃድዎ ያቋረጡት ከሆነ፤ የመልሶ ማቋቋሚያ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኝት ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ። የማቋቋሚያ ድጋፍ ማመልከቻ ማቅረቡ፤ የጥገኝነት ማመልከቻዎ ተቀባይነቱ ውድቅ ከሆነበት ወይም  የጠየቁትን ጥገኝነት ማመልከቻዎን በገዛ ፈቃድዎ ካቋረጡበት ቀን ኣንስቶ፤ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ መሆን አለበት።

የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ለማግኝት የእርሶዎን የመቀበያ ሀላፊ ጋር በመሄድ ማመልከት ይችላሉ። ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ ወይም ማግኘት አይችሉም ብሎ የሚውስነው፤ የስደተኞች ቦርድ (ሚግራሾንስቨርክ) ነው። የስደተኞች ቦርድ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ላይ የወሰነው ውሳኔ ይግባኝ የለውም።

የገንዘቡክፍያበእርስዎአገርውስጥይከፈላል

የስደተኞች ቦርድ ከIOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) ጋር በመተባበር ስራውን ያካሄዳል። IOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) በአብዛኞቹ  የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ለተወሰነላቸው አገሮች ላይ፤ ውክልና ያለው ድርጅት ነው። ስለዚህ ክፍያው የሚፈጸመው በIOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) በእርሶዎ ሀገር ውስጥ ነው።ከስዊድን ሀገር ለቀው ከመውጣትዎ በፊት በእርስዎ ሀገር የሚገኝውን IOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) ቢሮ ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ይወስዳሉ። ሀገርዎ ሲደርሱ ደውለው ቀጠሮ በመያዝ የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ክፍያ ይወስዳሉ።

ክፍያው የሚፈጸመው በአሜሪካ ዶላር ሲሆን አጠቃላይ ክፍያውም በአንድ ጊዜ ይፈጸማል። ገንዘቡን በሚወስዱበት ጊዜ የግዴታ የፓስፖርትዎ ፎቶ ኮፒ እና የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ ክፍያ እንዲከፈልዎት የሚያረጋግጠውን የተወሰነበትን ኮፒ ይዘው መቅረብ አለብዎት። IOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) በእርስዎ አገር ውስጥ ቢሮ የሌላቸው ከሆነ እርስዎ ስዊድን ሀገርን ለቀው ከመውጣትዎ በፊት ማቋቋሚያ ድጋፍ ክፍያ ገንዘብ እዚሁ ስዊድን ሀገር ይከፈልዎታል።

ተጨማሪ ማብራሪያ  ስለ IOM (አለም አቀፍ  የስደተኞች ድርጅት) ከፈለጉ በ(http://www.iom.int/) ድረ-ገጽ ይገኛል።external link, opens in new window (በእንግሊዝኛ)

የመልሶማቋቋሚያድጋፍክፍያመጠን፥

የመልሶ ማቋቋሚያ ድጋፍ በነፍስ ወከፍ ለያንዳዱ  30 000 የስዊድን  ክሮነር ከ 18 ዓመት በላይ  ለሆነው ሰው እናም ለያንዳዱ 15 000 የስዊድን  ክሮነር ለያንዳዱ ልጆች ከ 18 ዓመት በታች ለሆናቸው ይከፈላል። አንድ ቤተሰብ ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን75 000 የስዊድን  ክሮነር ሊያገኝ  ይችላል።

ትክክልያልሆነመረጃሰጥተውእንደሆነ፥

የስዊድን የስደተኞች ቦርድ፤ ሁሉንም ወይም በከፊል ገንዘቡን እንዲመልሱ  ሊወስን ይችላል።

 • በፈቃደኝነት ለመመለስ ካልፈለጉ ወይም አንዴ ከተመለሱ በኋላ፤ ደግሞው ስዊድን ሀገር ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ከሆነ
 • እርሶዎ እውነት ያልሆነ መረጃ መስጠትዎ ከተረጋገጠ ወይም በሌላ መንገድ አሳስተው ገንዘብ እንዲከፈልዎ ካርደረጉ፤ ወይም ከልክ በላይ ገንዘብ የመቀበል ምክንያት ከሆኑ ነው።  

  Last updated: 12 April 2017

  Was the information on this page helpful to you?

  Thank you for helping us improve our website!

  Thank you for helping us improve our website!

  Tell us how we can make this page better*


  If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.