የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር በፈቃደኝነት መመለስ

Återvända självmant när du har fått avslag på din ansökan om asyl – amhariska

በፈቃደኝነት መመለስ ማለት በስዊድን ውስጥ በጥገኝነት እንዲኖሩ አልተፈቀድልዎትም  የሚለውን ውሳኔ ተቀብለው ወደ መጡበት አገር በመመለስ ይተባበራሉ ማለት ነው፡፡

የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት እንዳላገኘ የተወሰነው ውሳኔ ከደረሰዎ በኋላ ወደመጡበት አገር ስለሚመለሱበት ሁኔታ ከሚመለከተው አካል ጋር ለመወያየት ስብሰባ ይጠራሉ፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ወደ መጡበት አገር ሊመለሱ ስለሚችሉባቸው የተለያዩ አማራጭ መንገዶች መረጃ ይሰጥዎታል በተጨማሪም ማንኛውንም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሚመለሱበትን ሁኔታ በራስዎ ማመቻቸት ካልቻሉ ጉዳዩ ከሚመለከተው ባለሙያ ጋር በመሆን እርሶ ማድረግ ያለብዎትንና የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው ማድረግ ያለበትን ሁኔታ ያካተተ ዕቅድ ታዘጋጃላችሁ። ለምሳሌ፡- እርስዎ ፓስፖርት ለማግኝት የአገርዎን ኤምባሲ ማነጋገር ሲኖርብዎት ኤጀንሲው ደግሞ ወደ አገርዎ ሲመለሱ የትራንዚት ቪዛ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡

በሁለት ወይም በአራት ሳምንታት ውስጥ መመለስ

ከሃገር እንዲወጡ የተወሰነው ውሳኔ በደረሰዎት በአራት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አገሪቱን ለቀው መውጣት አለብዎ፡፡ በውሳኔው ላይ የተለየ ቀን ካልተገለጸ በስተቀር ወደ ስዊድን መግባት እንደማይችሉ የተወሰነው ውሳኔ በደረሰዎት በሁለት ሳምንታት ውስጥ አገሪቱን ለቀው መውጣት አለብዎት፡፡

ውሳኔው በደረሰዎ በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ ካልጠየቁ ውሳኔው ተግባራዊ ይሆናል፡፡

በውሳኔው ላይ በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ ስዊድንን ለቀው ካልወጡ ሮማንያን፣ ቡልጋሪያን እና ክሮሺያን ጨምሮ ወደ ሁሉም የሼንጌን አባል አገራት ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እገዳ ይጣልብዎታል፡፡ ተመልሶ ያለመግባት እገዳው ለአንድ ዓመት የጸና ነው።

ተመልሶ ያለመግባት እገዳው በእርስዎ ላይ ተፈጻሚ እንዳይሆን እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ ስለ እገዳው የበለጠ ያንብቡ።

ወዲያው ተግባራዊ የሚደረግ ወደ ያለመግባት እገዳ

ወዲያው ተግባራዊ የሚደረግ  ያለመግባት እገዳ ውሳኔ ከደረሰዎት ውሳኔውን እንደተቀበሉ ወዲያውኑ ሃገሪቱን ለቀው መውጣት አለብዎት፡፡ ውሳኔው በደረሰዎት በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ውሳኔውን በመቃወም ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን እስኪያሳውቅ ድረስ ስዊድን ውሰጥ መቆየት አይችሉም፡፡

ምንም እንኳን ስዊድንን ወዲያው ቢለቁም ባስቸኳይ ተግባራዊ የሚሆን ያለመግባት የእገዳ ትዕዛዝ ሲደርሶት፣ በዚያውምወደ ስዊድን ተመልሶ ያለመግባት እገዳ አብሮ እንደተጣለብዎት ይወቁ፡፡ ይህም ማለት ባስቸኳይ ተፈጻሚ የሚሆን የመግባት እገዳ ትዕዛዝ ከደረሰዎት ሮማንያን፣ቡልጋሪያን እና ክሮሺያን ጨምሮ በሼንጌን አካባቢ ወዳሉ ወደ ሁሉም አገሮች በትንሹ ለሁለት ዓመት መግባት አይችሉም ማለት ነው፡፡

ከትውልድ አገርዎ ውጪ ወደሆኑ አገሮች መመለስ

በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ወዳሉ ሌሎች ሃገራት

የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው ወደሌላ የአውሮፓ ህብረት አገራት እንዲመለሱና የጥገኝነት ጥያቄዎም በዛ እንዲታይ ሊወስን ይችላል፡ ይህ የሚሆነው ወደ ስዊድን ከመምጣትዎ በፊት በሌላ የአውሮፓ ህብረት አገራት ከነበሩ ወይም ከሌላ የህብረቱ አገር ቪዛ ካገኙ ወይም ለሌላ የህብረቱ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ካቀረቡ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች በደብሊኑ መመሪያ ውስጥ ይገኛሉ

ወደ መጡበት አገር መመለስ የሚፈልጉ ከሆነና የሚመለሱበት ሂደት ረጅም ጊዜ እና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ካልሆነ ፍላጎትዎ ይሟላል፡፡

የደብሊኑን መመሪያ ደንብ የበለጠ በማንበብ የጥገኝነት ጥያቄዎ የሚታይበትን አገር ለምን እርሶ መምረጥ እንደማይችሉ የበለጠ ይረዳሉ፡፡ (በእንግሊዝኛ)

በውሳኔው ላይ ከተገለጸው የተለየ ሌላ አገር

ወደ ሃገር እንዳይገቡ ወይም ከሃገር እንዲወጡ በተወሰነው ውሳኔ ላይ ወደ ተገለጸው አገር መመለስ አለብዎት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በውሳኔው ላይ የሚገለጸው አገር እርሶ ዜጋ የሆኑበት አገር ነው፡፡

ሆኖም እርስዎ በሌሎች አገሮች ተቀባይነት ማግኘት እንደሚችሉ ማረጋገጥ ከቻሉ በውሳኔው ላይ ከተገለጸው አገር ሌላ እርሶን ሊቀበል ወደሚችል አገር ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ህጋዊ ፓስፖርት እና በሚሄዱበት አገር መኖር የሚያስችል የመኖሪያ ፈቃድ ሊኖርዎት ይገባል፡፡ የጉብኝት ቪዛ ወይም ቪዛ የማይጠየቅበት ሁኔታ ለዚህ ሂደት በቂ አይደለም። የሚመለሱበት ጊዜ የተራዘመና ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ከሆነ አይፈቀድም።

ለጉዞ የሚያስፈልጉዎትን ማስረጃዎች የመያዝ ሃላፊነት አለብዎት

በተወሰነው የጊዜ ገደብ ለመመለስ እንዲችሉ ፓስፖርትዎን ወይም ጊዜያዊ የጉዞ ማስረጃዎን የመያዝ ሃላፊነት አለብዎት፡፡

የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲውን ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ ኤጀንሲው በትውልድ አገርዎ ያሉትን የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር ፓስፖርት እንዲያገኙ ያመለክትልዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው በአገርዎ ላሉ የሚመለከታቸው አካላት ስለ እርሶ የግል መረጃ መስጠት አለበት፡፡ ነገር ግን ለስዊድን አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብዎን አይገልፅም፡፡

ፓስፖርትዎን የሚያገኙበት ምንም ዓይነት መንገድ ከሌለ ለውጪ አገር ዜጎች የሚሰጥ ጊዜያዊ ፓስፖርት ከስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው ያገኛሉ፡፡ ይህ ጊዜያዊ ፓስፖርት የሚያገለግለው ወደ አገርዎ ለመመለስ ብቻ ነው፡፡

የመጓጓዣ ቲኬት

 በመጀመሪያ ደረጃ ወደ አገርዎ ለመመለስ የሚያስፈልግዎትን የጉዞ ወጪ የመክፈል ሃላፊነት አለቦት፡፡ እርሶ መክፈል የማይችሉ ከሆነ የስደተኞች ማስተባበሪያ ኤጀንሲው የቲኬት ወጪዎን ይሸፍናል ።

ማመልከቻዎን ማቋረጥ ይችላሉ

የጥገኝነት ጥያቄዎ በሚመለከታቸው አካላት መታየት ከመጀመሩ በፊት ጥያቄዎን በማቋረጥ በፈቃደኝነት ወደመጡበት አገር መመለስ ይችላሉ፡፡ የእርሶን ጉዳይ የያዙትን ባለሙያዎች በማነጋገር ወደ አገሮ ለመመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ለመመለስ የሚደረግ ድጋፍ

በእንግዶች መቀበያ የሚገኙ ባለሙያዎችን ለመመለስ ስለሚያስፈልግዎት ድጋፍ ሊያነጋግሯቸው ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በስዊድን የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ድርጅቶች በማነጋገር በሚመለሱበት አገር ስላለው ሁኔታና ለመመለስ ስለሚያስፈልገው የጉዞ ድጋፍ መመካከር ወይም በሚመለሱበት አገር ካሉ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ከተመለሱ በኋላ ድጋፍ ማግኘት እንዲችሉ ሊያመቻችልዎት ይችላል፡፡

በራስዎ ፈቃድ የሚመለሱ ከሆነ ወደ መጡበት አገር ለሚመለሱ የሚደረገውን ድጋፍ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ይህን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ እነማን እንደሆኑና በድጋፉ ውስጥ የተካተቱ ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ የበለጠ ያንብቡ፡፡

Last updated: 2017-02-21

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.