የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ካላገኘ

Om du får avslag på din ansökan om asyl – amhariska

ጥያቄዎ ተቀባይነት ካለገኘ፣ ስዊድን ሀገር ውስጥ ለመቆየት በቂ የሆነ ምክንያት የለዎትም ማለት ነው ስለዚህ የስዊድን የፍልሰት ቦርድ ጥያቄዎን አልተቀበለውም ማለት ነው፡፡ ተቀባይነት ካላገኙ ሁለት ምርጫ አለዎት፤ መልሱን ተቀብለው ወደትውል ሀገርዎ መመለስ ወይም ይገባኝ ማለት፡፡ ይግባኝ ካሉ ፍርድ ቤቱ ጥያቄዎን እንደገና ይመለከተዋል፡፡ ይግባኙንም ቢያቀርቡ እንኳን መመለስዎን ማቀድ አለብዎ::

ውሳኔውን ከተቀበሉ የደስተኝነት እወጃ የሚል ወረቀት ይፈርማሉ፡፡ ይህንን ከፈረሙ በኃላ ይግባኝ መጠየቅ የማይችሉ ሲሆን ወደሀገርዎ የመመለስ እቅድዎን ማስተካከል ይጀምራሉ፡፡

ወደሀገርዎ መመለስዎን ያቅዱ

መመለስዎን የማቀድ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ የእርሶ ነው፤ ይህም ፓስፖርት ማግኘት እና ወደ ትውልድ ሀገርዎ ለመመለስ ወይም የመኖርያ ፈቃድ የተሰጦት ሀገር ለመመለስ የመያስፈልገውን ነገር በሙለ ሟሟላትን ያካትታል፡፡ የስዊድን የፍልሰት ቦርድ የመመለስ እቅድዎን ለማሳካት እና የትውልድ ሀገርዎ የሚገኙ ሰወችን ለማግኘት የሚያስፈልግ ነገር ላይ ትብብር ያደርጋል፡፡ እንደመጡበት ሀገር ታይቶ ወደ ትውልድ ሀገርዎ ሲመለሱ የመጀመሪየዎቹን የቆይታ ቀናት ቀላል ለማድረግ ይሆን ዘንድ የገንዘብ እርዳታ እናደርጋለን፡፡ የሚቀበልዎትን አካል ስለ “ዳግም የመመለስ ድጋፍ” ጥያቄ ያቅርቡ፡፡

በራስ ስለመመለስ ተጨማሪ ያንብቡ

ዳግም የመመለስ ድጋፍ ለማን እንደሚሰጥ ተጨማሪ ንባብ ያድርጉ

ውሳኔው ለ አራት አመታት የጸና ይሆናል

ተቀባይነት ያለማግኘት ውሳኔዎች በተለምዶ ለአራት አመታት የጸኑ ይሆናሉ

ይግባኝ

ይግባኝ የሚጠይቁ ከሆነ ፍርድ ቤቱ የስዊድን ፍልሰት ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ በድጋሚ እንዲያየው እየጠየቁ ነው ማለት ነው፡፡ ወደሀገርዎ እንዲመለሱ የተወሰነ ከሆነ የይገባኝ ጥያቄዎ እንደገና እስከሚታይ ድረስ ስዊድን ውስ መቆየት ይችላሉ፡፡ ከስዊድን መውጣትዎ ወዲያው እንዲተገበር የተወሰነ ከሆነ ግን ይግባኝ ቢጠይቁም እንኳን ከስዊድን ሀገር ውስጥ መውጣት አለብዎ፡፡

ይግባኝ ስለመጠየቅ ተጨማሪ ያንብቡ

ወዲያው ስለሚተገበር ከሀገር መባረር ተጨማሪ ያንብቡ

ውሳኔውን የማይተገብሩ ከሆነ

ውሳኔው ከጸና በኃላ እና ይግባኝ የማለት እድልዎ ካለቀ በኃላ (ትግበራው ከተጀመረ በኃላ) ስዊድንን ለቀው መውጣት አለብዎ፡፡ ከሀገር በመውጣት ውሳኔው ላይ ስዊድንን ለመልቀቅ ምን ያህል ጊዜ እንደቀረዎ የሚገለጽ ይሆናል፡፡ የተሰጠው ጊዜ ካለቀ በኃላ የፍልሰት ቦርዱ የገንዘብ ድጋፍ የማያደርግ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ የመኖር መብትም አይኖርዎትም፡፡ ይህ ለሁሉም አቅመ አዳም እና ሄዋን የደረሱ ሰወችን የሚያካትት ሲሆን ይህም በእነሱ ሀላፊነት ስር ያለ ከ18 አመት በታች እድሜ ያለው ልጅ አብሯቸው ከሌለ ነው፡፡

የፈልሰት ቦርዱ ስለ ማማከር እና ስለ ደህንነት ውሳኔ መስጠት ይችላል፡፡ ማማከር ማለት የፍልሰት ቦርዱ ጋር ወይም ፖሊስ ጋር በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መመዝገብ አለቦት ማለት ነው፡፡ ስለደህንነት ውሳኔ ተሰጥቶት ከሆነ መመለሻዎን እየጠበቁ በኪራይ ቤት ውስጥ መቆየት ይችላሉ፡፡ ድጋሚ እንዳይመለሱ የሚያደርግ ውሳኔም ሊሰጥዎ ይችላል፡፡

የፍልሰት ቦርዱ ውሳኔውን ለማስተግበር ሀይል መጠቀም እንደሚያስፈልግ ካመነ ይህንን ለማስፈጸም ፖሊስ ሀለፊነቱን ይወስዳል፡፡

ውሳኔውን ካልተገበሩ ምን እንደሚከሰት ተጨማሪ ያንብቡ

ዳግም ለመመለስ መከልከል

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ስዊድንን ለቀው የማይወጡ ከሆነ ዳግም ለመመለስ እገዳ ሊጣልብዎ ይችላል ይህም ማለት ከሼንን ሀገሮች ውስጥ ማናቸውም ጋር እንዳይገቡ ለተወሰነ ጊዜ ይታገዳሉ ማለት ነው፡፡

ወዲያውኑ ከሀገር እንዲወጡ ከተወሰነ ሁልጊዜም የዳግም መመለስ እገዳ ይሰጥዎታል፡፡

ስለ ዳግም መመለስ እገዳ እና ይህ ሁኔታ እንደይደርስብዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ተጨማሪ ያንብቡ

ወዲያው ስለመመለስ ተጨማሪ ያንብቡ

ከውሳኔ በኃላ የሚፈጠር አዲስ ክስተት

መመለስ የማይችሉበት አዲስ ክስተት ከተፈጠረ ይህንኑ ለተቀበልዎት አካል ያሳውቃሉ፡፡ የፍልሰት ቦርዱም ይህንን ይመለከት እና ውሳኔውን ለማካሄድ የሚያስቸግር ነገር ካለ ያጣራል፡፡ ስለ ሁኔታዎ ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ስለጉዳይዎ አዲስ መረጃ መመንጨት አለበት፡፡

ከክልከላው በኃላ ስላለ መረጃ እና ተቀባይነት ስላለው መረጃ ተጨማሪ ያንብቡ

መኖሪያ፣ የባንክ ካርድ እና የ እል ኤም ኤ ካርድ

የክልከላ ውሳኔ  ወይም ወደሀገርዎ የመመለስ ውሳኔ ከተሰጥዎ እና ውሳኔው መተግበር ከተጀመረ ወይም በፈቃድዎ የሚቆዩበት ወቅት ካለቀ የመኖርያ ቦታ ፈቃድ መብትዎን እና የገንዘብ እርዳታ መብትዎን  ያጣሉ፡፡ ይህም ከእርሶ ጋር የሚኖር ከ 18 አመት እድሜ በታች ያለ ልጅ ካለና እርሶ የነሱ ሀላፊ ከሆኑ ነው፡፡

የመኖርያ ቤት መብት በማይኖርዎ ጊዜ ወይም የገንዘብ እርዳታ ማግኘት በማይችሉበት ጊዜ ወደ ኤል ኤም ኤ መመለስ አለብዎ፡፡ ከ ፍልሰት ቦርዱ የባንክ ካርድ ተቀብለው ከሆነ ገንዘቡን አውጥተው ካርዱን መመለስ ይጠበቅቦታል፡፡ በፍልሰት ቦርዱ አንድ የመኖሪያ ቦታ ውሰጥ ይኖሩ ከነበር ቤቱን ለቀው ቁልፎችን መመለስ አለብዎ፡፡

የጤና ጥበቃ እና ትምህርት ቤት

ስዊድንን እስከሚለቁበት ወቅት ድረስ በፊት የነበርዎት የጤና መብት ይኖርዎታል ነገር ግን ምንም አይነት የገንዘብ  ድጋፍ ለመድሀኒት እና እንክብካቤ አያገኙም ይህም የገንዘብ እርዳታ መብትዎ ካበቃ ነው፡፡

ልጆች ስዊድን ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ ትምህርት ቤት የመሄድ መብት አላቸው፡፡

ስለጥገኝነት እና ስለ ልጆች ተጨማሪ ያንብቡ

Last updated: 20 February 2017

Was the information on this page helpful to you?

Thank you for helping us improve our website!

Thank you for helping us improve our website!

Tell us how we can make this page better*


If you wish to ask the Migration Agency a question you can find our contact details under the heading Contact us.