2019-04-16

ጥገኝነት ጠያቂዎች ሂሳብ መክፈል አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል

Svårare för asylsökande att betala sina räkningar – amhariska

በ2019 ዓ. ም ብዙዎቹ የስዊድን ክፍያ አገልግሎት ወኪሎች (Sveriges betaltjänstombud) ሊዘጉ ነው። በዚህ ምክንያት ጥገኝነት የጥየቃችሁ ሰዎች፡ ሂሳባችሁን መክፈል ከባድ ሊሆንባችሁ ይችላል። ስለዚህ የጤና አገልግሎት በምትሹበት ጊዜ፥ አስቀድማችሁ ሂሳቡን እንዴት መክፈል እንዳለባችሁ፥ የጤና አገልግሎት ሰጪውን አካል መጠየቅ ይኖርባችኋል።

ዛሬ በመላ አገሪቱ 370 የክፍያ አገልግሎት ወኪሎች አሉ። ከነዚህ ውስጥ 200 የሚሆኑት በዚህ ዓመት ይዘጋሉ፥ ከሚቀሩት ውስጥ ደግሞ ብዙዎቹ በትልልቅ ከተሞች የሚገኙት ይሆናሉ። ስለዚህ፡ ይህ ሁኔታ ሂሳብ የምትከፍሉ ጥገኝነት ጠያቄዎችን፥ ለምሳሌ ለጤና ጥበቃ የሚከፈል ሂሳባችሁን በክፍያ አገልግሎት ወኪሎች በኩል ትከፍሉ የነበራችሁትን ይነካል።

በመላ ሱዊድን የሚገኙ ሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች በሙሉ የሚተዳደሩት በተለያዩ ክፍላተ ሃገር ሥር ነው። በየትኛው ክፍለ ሃገር ውስጥ እንደምትገኝ የሚወስነው የምትኖርበት ከተማ ነው። እያንዳንዱ ክፍለ ሃገር ታካሚዎችን ሂሳብ የሚያስከፍልበትን መንገድ ራሱ ስለሚወስን፥ እርስዎም የሚኖሩበት አካባቢ የየትኛው ክፍለ ሃገር አካል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፥ የተለየ የሂሳብ አከፋፈልመንገድ ሊጠቀም ይችላል። በአንዳንድ ክፍለ ሃገራት የጤና ማዕከሉን በሚጎበኙበት ወቅት፥ ሂሳብዎን እዚያው በካርድ ወይም በካሽ የሚከፍሉብት ሁኔታ ይኖራል። በሌሎች ክፍለ ሃገራት ሂሳብዎን በፋክቱር እንዲከፍሉ ቤትዎ ድረስ ሊልክሎት ይችላል። ስለዚህ ለሕክምና ብለው ወደ ጤና ተቋሙ ሲመጡ፥ ሂሳብዎን እንዴት መክፈል እንደሚኖርብዎት፥ የጤና አገልግሎት የሚሰጥዎትን አካል፥ እርስዎ ራስዎ መጠየቅ ይኖርብዎታል።

ወደ ሆስፒታል ወይም ጤና ጣቢያ ከመሄድዎ በፊት የአገልግሎት ሂሳብዎን በምን ዓይነት መንገድ መክፈል እንደሚችሉ ይጠይቁ። የጤና አገልግሎት ሰጭው በፋክቱር ብቻ ሂሳብ የሚያስከፍል ከሆነ፥ ቦታው ድረስ ተመልሰው በመምጣጥ መክፈል የሚችሉ መሆንዎን ይጠይቁ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት (ሚግራሾንስቨርከት) የሂሳብ አከፋፈልን በተመለከተ ሊረዳዎት የሚችለው ምንም ነገር የለም።