The Swedish Migration Agency logotype

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ

Uppehållstillståndskort – amhariska

የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎ በስውድን ሀገር ውስጥ መኖር እንደሚችሉ ማስረጃ ለመስጠት የመኖሪያ ፈቃድ ካርድም ይሰጥዎታል፡፡ ይህ ካርድ የእርሶን የጣት አሻራ እና ፎቶ የያዘ ኮምፒውተር ችፕ አለው  ወደ መንግስት ቢሮዎች ወይም የሕክምና አገልግሎት ወደሚሰጥበት ማንኛውም ስፍራ ስትሄዱ ይህንን ካርድ ይዛችሁ መሄድ ይኖርባችኋል፡፡

ፎቶ መነሳት እና የጣት አሻራ ስለመስጠት

የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው ያለ ማንኛውም ሰው ፎቶ መነሳት ይኖርበታል፡፡ ከስድት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የጣት አሻራ ማስነሳት አይኖርባቸውም፡፡   በአካላዊ ምንክያት የጣት አሻራ መስጠት የማይችል ሰው ማለትም እንደ ቋሚ በሆነ ሁኔታ የጣት አሻራው የጠፋ ሰው  የጣት አሻራው መወሰድ የለበትም፡፡

የጣት አሻራው እና ፎቶግራፋችሁ በካርዱ ቺፕ ላይ የሚቀመጥ ነው እንጂ ወደሌላ ቦታ አይሄድም፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ባወጣችሁ ቁጥር አዲስ ፎቶግራፍ እንድትነሱ እና የጣት አሻራ እንድትሰጡ ይደረጋል፡፡ ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ከሚከፈል ክፍያ ውጪ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለማግኘት የሚከፈል ምንም ዓይነት ክፍያ አይኖርም፡፡

ከስዊድን ውጪ  ከሆኑ

ወደ ስዊድን ለመጓዝ ቪዛ ካስፈለገህ ወደ ስዊድን ኤምባሲ ወይም ቆጽላ ጽፈት ቤት በመሄድ ፎቶግራፍ መነሳት እና የጣት አሻራ መስጠት ይኖርብሃል፡፡ ኤንባሲያችንን ወይም የቆንስላ ጽ/ቤታችንን ለመጎብኘት ከመሄድዎ በፊት፥ ሁሌ የጽ/ቤቶቹን ደረገጾች ያንብቡ።

ዜጎቻቸው ወደ ስዊድን ለመግባት ቪዛ የሚያስፈልጋቸው ሀገራት (ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window

አቅራቢያችሁ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት ቤት የቱ እንደሆነ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ፈልጉ Swedenabroad.se (ባእንግሊዝኛቋንቋ)external link, opens in new window 

ወደ ስዊድን ሀገር ለመጓዝ ቪዛ የማያሰፈልጋችሁ ከሆነ በስዊድን ሀገር ውስጥ ፎቶ እና አሻራ ይሰጣሉ፡፡ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳገኛችሁ እና ስዊድን እንደደረሳችሁ በተቻለ ፍጥነት የስደተኞች ኤጀንሲ ዘንድ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

በስዊድን ሀገር ውስጥ የሚትገኙ ከሆነ

የስዊድን ፈቃድዎን ማራዘም ወይም አዲስ “የመኖሪያ ፍቃድ ካርድ” ማውጣት ካስፈለግዎት የስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migrationsverket) ዘንድ ሄደው ፎቶ መነሳትና የጣት አሻራ መስጠት ይኖርብዎታል። ይህ መመሪያ፡ ስዊድን ውስጥ መጠጊያ ጠይቀው ምንም ፈቃድ የሌላቸውንም ይመለከታል።

የስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migrationsverket) ዘንድ ሲመጡ፥ ፓስፖርትዎን ይያዙ። ”የመኖሪያ ፍቃድ ካርድዎ” ተሰርቶ ሲያልቅ፥ ስዊድን ውስጥ በሚኖሩበት አድራሻ ወደ እርስዎ ይላካል። ስለዚህ፡ የስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት ዘንድ ፎቶ ለመነሳትና የጣት አሻራ ለመስጠት ሲመጡ፥ የሚኖሩበትን አድራሻ መንገር አስፈላጊ ነው።

ፎቶ እና አሻራ ለመስጠት ከስደተኞች ኤጄንስ ቢሮ ጋር ቀጠሮ ይያዙ፡፡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

እኛን የት ታገኙናላችሁ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

አድራሻችሁን ከለወጣችሁ

የመኖሪያ ካርዳችሁ መኖሪያ ቤታችሁ ድረስ እንዲንልክላችሁ ከፈለጋችሁ አድራሻችሁ እንፈልጋለን የአድራሻ ለውጥ ያደረጋችሁ እንደሆነ አዲሱን አድራሻችሁን ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ ስትመጡ ማሳወቅ ትችላላችሁ፡፡ ከሌላ ሰው ጋር የሚትኖሩ ከሆነ እና የጋራ አድራሻውን ለኛ መንገሩን አይርሱ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ዝግጁ ሲሆን

ፎቶ የተነሳችሁትን እና አሻራ የሰጣችሁት በኤምባኢ ወይም በቆንጽላ ጽሕፍት ቤት ውስጥ ከሆነ ካርዱን የምትቀበሉት ከእነርሱ ዘንድ ይሆናል፡፡ ኢንባስውን ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት የሚልክላችሁ ከሆነ ወይም እናንተ መምታት ካለባችሁ ጠይቋቸው፡፡ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጣችሁ ከተወሰነ በኋላ ካርዱን ለማዘጋጀት እና ወደ ኤምባሲው ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት ቤቱ ለመላክ እስከ አራት ሳምንታት ሊፈጅ ይችላል፡፡

ፎቶግራፍ የተነሳችሁት እና አሻራ የሰጣችሁት በስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ ውስጥ ከሆነ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ካርዳችሁ በመኖሪያ ቤታችሁ አድራሻ ይደርሳችኋል፡፡

የመኖሪያ ፈቃድ ካርዳችሁ የሚታተመው ውሳኔ ሲሰጥ ነው ይሁን እንጂ የመኖሪያ ፈቃዳችሁ ካርድ ሕጋዊነቱ ከሚጀምርበት ከሶስት ወራት በፊት አይደለም፡፡

ካርዱን ማዘጋጀትም ሆነ ማድረሱን ከዚህ በላይ ማፍጠን አይቻልም፡፡

Uppehållstillståndskort.

የመኖሪያ-ፈቃድ ካርዱ መልኩ ተቀይሯል

ከታህሳስ 2020 ጀምሮ፥ የመኖርያ-ፈቃድ ካርዱ አዲስ መልክ ተደርጎለታል። ቀዚህ ቀን በፊት ለተሰጡ ካርዶች ለመቀየር ግን አስፈላጊነት የለውም። የተሰጦት ካርድ፡ ለቀጣዩም የመኖሪያ ፈቃድዎ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ ወይም ቢረዝም እስከ አምስ ዓመት ድረስ ጊዜ፥ የሚያገለግል ይሆናል። የመኖሪያ ፈቃድ መራዘም ውሳኔ ከተስጦት በኋላ፥ ወይም የካርድዎ ያገልግሎት ጊዜ ካበቃ በኋላ፥ ያኔ ወደ አዲስ ካርድ ይለውጥልዎታል።

በካርዱ ላይ የሚገኙ መረጃዎች

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ እነዚህን መረጃዎች በውስጡ ይይዛል፡ ምን ዓይነት ፈቃድ እንዳላችሁ እና ካርዱ ለምን ያኽል ጊዜ ሕጋዊ እንደሆነ እና ሌሎች ነገሮችንም ይይዛል፡፡ የግል ማስረጃችሁም በዚህ ካርድ ውስጥ ተካቷል፡፡ በአንዳንድ ካርዶች ጃርባ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ይገባል “ለመስራት የተፈቀደለት” (“Får arbeta”)፡፡  ይህ ማለት የተቀበሉት ውሳኔ በቀጥታ ለስራት መብት እንዳለዎ የማያመለክት ከሆነ ማለትም ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ የተሰጦ ከሆነ፡፡ ይሁን እንጂ ስዊድን ውስጥ የሥራ ፈቃድ የተሰጣችሁ ከሆነ ውሳኔው ሥራ የመስራት ፈቃድ አላችሁ ይላል ስለዚህ ስለዚህም ካርዶ ጀርባ ላይ “ለመስራት የተፈቀደለት” ተብሎ ሊጻፍበት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ለልጆች ጽኁፉ ይካተታል (በአስፈላጊው ቦታ) እድሜቸው 16 ከሆነ ጀምሮ፡፡

በካርዳችሁ ላይ ያለውን መረጃ ተመልከቱ

ሁልጊዜ በመኖሪያ ፈቃድ ካርድህ ላይ ያለው ስምና በፓስፖርትህ ላይ ያለው ስም አንድ መሆኑን አረጋግጥ፡፡ ካርድህ የተሳሳተ ስም ካለው ወደ ስደተኛ ኤጀንሲ ወይም ኤምባሲ አዲስ ካርድ ለማግኘት ሂድ፡፡  ፓስፖርትህን ይዘህ ሂድ፡፡

ስምህን የለወጥህ እንደሆነ አዲሱ ስምህን ለማስመዝገብ በመጀመሪያ ወደ ታክስ ኤጀንሲ በመሄድ የሕዝብ መመዝገቢያ መሄድ ይኖርብሃል፡፡  ከዚያም አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለማግኘት ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ መሄድ ይኖርብሃል፡፡ 

ከሥፍራ ሥፍራ ስትዘዋወር

ከቦታ ቦታ ስትሄድ ከፓስፖርትህ ጋር የመኖሪያ ፈቃድ ካርድህን ማሳየት ይኖርብሃል፡፡ ካርዱ ብቻውን እንደ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ተደርጎ አይወሰደም፡፡

ካርዱ የሚሠራበት የጊዜ ወሰን

አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ስታገኝ ወይም የቀድሞውን የመኖሪያ ፈቃድ ሲራዘም ሁል ጊዜም አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጥሃል፡፡ የካርዱ የጊዜ ወሰን ከተሰጠህ የመኖሪያ ፈቃድ የጊዜ ወሰን ጋር እኩል ነው ይሁን እንጂ ከአምስት ዓመት ፈጽሞ አይበልጥም፡፡  አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ሲያስፈልግህ እንደገና ፎቶግራፍ መነሳት እና የጣት አሻራ መነሳት ይኖርብሃል፡፡ የስደተኞ ጉዳይ ጽ/ቤት (Migrationsverket) ዘንድ አዲሱን ካርድ ሊያወጡ ሲመጡ፥ ሁሌ አሮጌውን የመኖሪያ ፍቃድ ካርድ ይዘው መምጣት አለብዎት።

ካርድህ ከጠፋ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድህ ቢጠፋብህ ወይም ቢሰረቅብህ በመጀመሪያ ለፖሊስ ማመልከት አለብህ፡፡ ከዚያም ለአዲስ ካርድ ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ በመሄድ ፎቶግራፍ መነሳት እና አሻራ መስጠት ይኖርብሃል፡፡  ሪፖርት ባደረግክበት ወቅት ወይም ከዚያ በኋላ ከፖሊስ የተቀበልከውን የሪፖርት ቅጂ ይዘህ ሂድ፡፡

ካርዶን ያልተቀበሉ ከሆነ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎን ለመውሰድ ለረጅም ጊዜ እየጠበቁ ነው? ምክንያቱ ካርዱ ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ተመላሽ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የስደተኞች ኤጀንሲ ስህተት የሆነ የእርሶ አድራሻ ይዞ ሊሆን ይችላል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካለዎ የስደተኞች ኤጀንሲ ዘንድ በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: 2021-01-22

Was the information on this page helpful to you?