ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት

Provisoriskt främlingspass – amhariska

መደበኛ የውጭ ፓስፖርት ሊሰጥህ ካልቻለ ወይም ረጅም ግዜ ለመጠበቅ የማትችል ከሆንክ: ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ሊሰጥህ ይችላል። ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለኣጭር ግዜ ወይም ለልዩ ጉዞ ነው የሚያገለግል። 

ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በተለያዩ ምክንያቶች ይሰጡሃል፤

  • ፓስፖርት ለማግኘት ወደ ሌላ ኣገር በመሄድ ካልሆነ ያገርህን ፓስፖርት ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው የስዊደን የጉዞ ሰነዶች መጠየቅ የማትችል ከሆንክ። ስለሆነም ከስዊደን ኣገር በመውጣት ያገርህን ፓስፖርት ለማምጣት መቼ እንደምትጓዝና የት ወይ በምን ዓይነት መንገድ መሆኑን መግለጥ ይኖርብሃል። በምታቀርበው ምክንያቶች ኣንድ ግዜ ብቻ ነው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የሚሰጥህ።
  • ያገርህ ፓስፖርት የሌለህ ከሆነ እና በኣስቸኳይ ምክንያት ወደ ውጭ ኣገር መሄድ ካስፈለገህ። ይሁንና ለምን በዚሁ ወቅት የውጭ ዜጋ ፓስፖርት እንደ ምትፈልግ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት መግለጽ ይኖርብሃል። እንዲሁም፡ ያገርህ ፓስፖርት ወይ ለመጓዝ የሚያገለግልህ ጊዜያዊ ሰነድ ካገርህ ባለስልጣን፥ ማለት ለምን ከኤምባሲ ወይ ከቆንስል ማግኘት እንዳልቻልክ መግለጽ ይኖርብሃል። ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በሚመለከት ጥያቄ ስታቀርብ ምክንያቶቹን የሚያጠናክሩ ሰነዶች ይዘህ መምጣት ይገባሃል።
  • ኣስቀድሞ የተሰጠህን ፓስፖርት ለመጥፎ ድርጊት በመጠቀም ወይም በወንጀል ስለ ተከሰስክ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት ለማግኘት ካልቻልክ ግን ባንዳንድ እጅግ ኣስፈላጊ ጉዳይ ፓስፖርት መያዝ የሚያስፈልግህ ሲሆን። ኣስቀድሞ እንደ ተጠቀሰ ጉዞው ለምን ይህን ያህል ኣስፈላጊ መሆኑን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት መግለጥ ይገባሃል።
  • የስዊደን የመኖርያ ፈቃድ ኑሮህ ውጭ ኣገር ብትገኝና (ኣገርህ ውስጥ ሳይሆን): የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህን ወይም የጉዞ ፓስፖርትህን ብታጠፋው: እንዲሁም ወደ ስዊደን ልትመለስ ብትፈልግ። ስለ ጠፋው ፓስፖርት ለፖሊስ ኣሳውቅ: ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ ወደ ስዊደን ኤምባሲ ወይም ቆንስል ስትሄድ ለፖሊስ ያመለከትከውን የጽሑፍ ቅጂ ይዘሀው ሂድ።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ስለ መጠየቅ

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የምትጠይቀው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ቍ. 192011 በሞምላትና ይዘሀው ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የፈቃድ ኣሃዱ ጋ በመሄድ ነው። ይሁንና ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ ያዝ። ለያንዳንዱ ሰው ነው ቀጠሮ የሚያዝለት። እያንዳንዱ ደግሞ የራሱ ፎርም ይሞላል።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 192011 (በሽወደን ቋንቋ) Pdf, 772.2 kB, opens in new window.

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 193011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ) Pdf, 820.8 kB, opens in new window.

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በሚመለከት እንዴት እንደሚሞላ በተጨማሪ ኣንብብ።

ማመልከቻህን ለማቅረብ በሚቀጥለው የኢንተርነት ኣድራሻ ቀጠሮ ያዝ፤ www.migrationsverket.se/book-appointment

ከ 18 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው ህጻናት

ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በራሳቸው ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ ኣይችሉም። ወላጆቻቸው ወይም ኣሳዳጊዎቻቸው ነው በኣካል ወደ ጽ/ቤት ሂደው ግዚያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የሚጠይቁላቸው።

ሁለት ኣሳዳጊዎች ቢኖሩ ሁለታቸው ናቸው ለ18 ዓመት በታች ለሆኑትን ህጻናት የሚመለከት የፈቃድ ፎርም ቍ. 246011 በማጽደቅና በሞምላት ከህጻኑ ማመልከቻ ጋር ባንድ ላይ እንዲቀርብ የሚያደርጉ።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 246011 (በሽወደን ቋንቋ) Pdf, 724.6 kB, opens in new window.

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 247011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ) Pdf, 695.3 kB, opens in new window.

ክፍያ

ኣብዛኞቹ ለሚያቀርቡት ጊዜያዊ ይውጭ ዜጋ ፓስፖርት ማመልከቻ ይከፍላሉ። ማመልከቻው ስታቀርበው በካርድ ኣድርገህ ክፈል ወይም የመክፈያ ካርድ ትወስድና ቆይተህ ትከፍላለህ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ክፍያውን እስክታጠናቅቅ ድረስ ጉዳይህን መመርመር ኣይጀምርም።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ክፍያ

ጉዳዩ ለማከናወን የሚፈዽበት ግዜ

ባሁኑ ግዜ ጉዳዩ ለማከናወን የሚወስደው ግዜ ለማወቅ የስደተኞች ጽ/ቤት የኢንተርነት መረጃ ኣንብብ። ጉዳዩን የሚከታተል ሰው ተጨማሪ መረጃ የሚጠይቅህ ከሆነ በዚያ ኣኳያ ግዜው ሊራዘም ይችላል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጉዳይህን ከጨረስው በኋላ: ውሳኔውን በፖስታ ኣድርገን እንልክልሃለን።

ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በመጠቀም የሚደረግ ጉዞ

ኣገሮች በሙሉ ጌዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ኣይቀበሉም። የምትጎበኛቸውን ኣገሮች ኤምባሲ ራስህ ሂደህ ኣነጋግራቸው: ወይም ኣገሪቱ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የምትቀበል መሆኗን መረጃ ፈልግ።

የተሰጠህን የመኖርያ ፈቃድ በጥገንኘት ምክንያት ከሆነ በውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ላይ ወደ ኣገርህ ወይም ወደ የተባረርክበት ኣገር ለመሄድ እንደማትችል የሚገልጽ ጽሑፍ ኣለ።

ማንነትህን ለማጠናከር ካልቻልክ: በጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ማንነትህ እንዳልተረጋገጠ ተጽፍዋል። ስለሆነም ወደ ኣንዳንድ ኣገሮች በምትጓዝበት ግዜ ችግር ሊያጋጥምህ ይችላል።

የምትጎበኛቸው ወይ የምታልፍባቸው ኣገሮች ቪዛ የሚጠይቁ መሆናቸው ኣረጋግጥ።

ፓስፖርትህ የሚያገለግልበት ግዜ

ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ኣብዛኛው ግዜ ቢረዝም እስከ ሰባት ወር ያገለግላል። ፓስፖርቱ ከስዊድን ወደ ውጭ ኣገር ወይም ለሁለቱ ኣቅጣጫ በኣንድ ጉዞ ብቻ የተወሰነ ነው። ከጉዞው በኋላ ፓስፖርቱን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣስረክበው።

ፓስፖርትዎን ከጣሉ ወይም ከጠፋብዎት

ግዜያዊው የእንግድነት (provisoriska främlingspass) ፓስፖርትዎ ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቁ፥ መጀመሪያ የሚወስዱት እርምጃ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ድረስ ሄደው ማመልከት ነው። ሌላ አዲስ ግዚያዊ የእንግድነት ፓስፖርት የሚያስፈልግዎት ከሆነ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል። አንድ አዲስ ግዜያዊ የእንግድነት ፓስፖርት ፈልገው ማመልከቻ ለማስገባት ሲመጡ፥ ከፖሊስ ጣቢያው የተሰጥዎትን ወይም እቤትዎ ድረስ በፖስታ የሚላክልዎትን የፖሊስ ማመልከቻ ግልባጭ ይዘው ይምጡ።

ጊዜያዊ የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ

ማመልከቻህ ውድቅ ሲሆን

ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ሳይሰጥህ ሲቀር: ይግባኝ ማለት ኣይቻልም.

Last updated: