ጊዜያዊ የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት ለመጠየቅ

Så ansöker du om provisoriskt främlingspass – amhariska

1

ፎርሙንሙላው

ጊዜያዊ የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት ስትጠይቅ: በቍ.1920 11 በተመለከተው የመጠየቅያ ፎርም ሙላው: በኋላ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚገኘው የፈቃድ ኣሃዱ ወይም በውጭ ኣገር የምትገኝ  ከሆነ ብቅርብ ያለውን የስዊድን ኤምባሲ ወይም ቆንስል በኣካል ሂደህ ኣቅርበው። 

የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት የሚፈልግ ህጻን ቢኖርህ: የህጻኖች ልዩ ማመልከቻ ኣቅርብ። ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ህጻን የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የወላዶቹ ወይም የኣሳዳጊዎች ፈቃድ ያስፈልጋል። ይሄም ፈቃድ በተባለው ለ18 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው የተዘጋጀ ቍ. 246011 ተሞልቶ ይቀርባል።

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 192011 (በሽወደን ቋንቋ) Pdf, 772.2 kB, opens in new window.

የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጠየቅያ ፎርም ቍ 193011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ) Pdf, 820.8 kB, opens in new window.

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ  ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 246011 (በሽወደን ቋንቋ) Pdf, 724.6 kB, opens in new window.

 የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆነው ህጻን የውጭ  ዜጋ ፓስፖርት እንዲሰጠው የሚሞላው የወላጆች የፈቃድ ፎርም 247011 (በእንግሊዝኛ ቋንቋ) Pdf, 695.3 kB, opens in new window.

2

ማመልከቻህንለማቅረብቀጠሮያዝ

ማመልከቻህን  ለማቅረብ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ መያዝ ይገባሃል። የውጭ ኣገር ዜጋ ፓስፖርት የሚጠይቁ ሁሉ ካንተ ጋር መኖር እንዳለባቸው መርሳት የለብህም። ህጻናት  ቢሆኑም። እያንዳንዱ ማመልከቻ የሚያቀርብ ሰው የራሱ ቀጠሮ መኖር ያስፈልጋል። ለያንዳንዱ ሰው ቀጠሮ ያዝለት።   

ማመልከቻህን ለማቅረብ በዚሁ የኢንተርነት ኣድራሻ ቀጠሮ ያዝ www.migrationsverket.se/book-appointment

በውጭ ኣገር ስትገኝ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለማግኘት ወይም የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ከጠፋ ወደ ስዊደን ኤምባሲ ወይም ኣጠቃላይ ቆንስል በመሄድ ልታመልክት ትችላለህ፡ ወይም የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህ ጊዜው ቢወድቅና ወደ ስዊደን ኣገር ለመመለስ ጊዜያዊ ፓስፖርት ሲያስፈልግህ።  

3

ወደየስደተኞችጉዳይጽ/ቤትሂድ

ማመልከቻ ስታቀርብ የሚከተሉትን ይዘህ ና፤

  • የመጠየቅያ ፎርም: የተሞላና የተፈረመ (ኣንድ ፎርም ላንድ ሰው)
  • ኣስቀድሞ የተሰጠህ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ካለህ
  • ማንነትህን የሚያጠነክር ያገርህ ፓስፖርት ወይም ሌላ ተመሳሳይ ሰነድ (ሌላ ፓስፖርት የሌለህ ከሆነ) ለምሳሌ የመታወቅያ ወረቀት: የልደት ምስክር: ወይም የወታደር ካርድ ሊሆን ይችላል።
  • ለ18 በታች ዕድሜ ያላቸው ህጻናት በሚመለከት ከወላጆች ወይም ኣሳዳጊዎች የሚሰጥ ፈቃድ (ይሀም ፈቃድ በተባለው ለ18 ዓመት በታች ዕድሜ ላላቸው የተዘጋጀ ቍ. 246011 ተሞልቶ ይቀርባል)።
  • የውጭ ዜጋ ፓስፖርት መጥፋቱ የሚመሰክር የፖሊስ ሪፖርት ቅጂ (ኣሮጌው የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በመጥፋቱ ኣዲስ ስትጠይቅ)።
  • ከስዊድን ውጭ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለማግኘት: ወደ ኣገርህ ለመሄድ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ወይም ያገርህ ፓስፖርት ለመጥየቅ ወደ ኣገርህ ኤምባሲ ስትሄድ መቼ: የት: እንዴት የሚገልጽ የጉዞ ፕላን

ያገርህ ፓስፖርት ወይም የድሮ  የየውጭ ዜጋ ፓስፖርት ሲኖርህ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ማስረከብ ይኖርብሃል። ኣንዳንድ ግዜ ጉዳዩን የሚከታተል ሰው የፓስፖርት ቅጂ ከማመልከቻው ጋር ባንድ ላይ ይቀበላል: ሆኖም ጉዳይህ በሂደት ላይ እያለ ወይም ፓስፖርትህን ስትወስድ ግዜ: ኦሪጂናሉ  ለማስረከብ ግዴታ ኣለህ።  

ማመልከቻ ስታቀርብ: የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ፎቶግራፍ ሊያነስህ እንዲሁም የጣቶችህ ኣሸራ ሊወስድ ነው። ከ6 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የጣት ኣሻራ ኣይስፈልጋቸውም።

ኣብዛኞቹ: የውጭ ዜጋ ፓስፖርት በሚጠይቁበት ግዜ  ይከፍላሉ። ማመልከቻ ስታቀርብ ብካርድ ኣድርገህ ነው የምትከፍለው: ወይም መጀመርያ የክፍያ ካርድ ትወስዳለህና  በኋላ ቆይተህ ትከፍላለህ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመክፈልህ በፊት ጉዳይህ መከታተል ኣይጀምርም።

ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ክፍያ

ፈልገን

4

የስደተኞችጉዳይጽ/ቤትጉዳዩንይከታተላል

ጉዳዩን የሚከታተለው ሰው ተጨማሪ መረጃ ከጠየቀህ: ግዜው በዚያ ኣኳያ ሊረዝም ይችላል። ስለዚህ ተጨማሪ ሰነዶች እንዳይጠይቅህ ሰነዶችህን በሙሉ ካንተ ጋ መኖራቸው ማረጋገጥ ይኖርብሃል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የውጭ ዜጋ ፓስፖርትህን ሲመረምረው ከፖሊስ ወንጀል ምርመራም መረጃ ይላክለታል። 

5

ውሳኔ ማግኘት

ውሳኔው በፖስታ እቤትህ ድረስ ይላካል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለማግኘት መብት እንዳለህ ከወሰነ እና የውጭ ዜጋ ፓስፖርቱ ዝግጁ ሲሆን: መጥተህ እንድትወስደው እንነግርሃለን።  ውሳኔ ከተሰጠበት ግዜ ኣንስቶ: ማመልከቻ ካቀረብክበት የፈቃድ ኣሃዱ ፓስፖርቱን እስክትወስድ ድረስ 14 ቀናት ኣሉ።

ለጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ያቀረብከው ማመልከቻ ውድቅ ሲሆን ይግባኝ ማለት ኣትችልም።

እንዴት ይግባኝ እንደሚባል በተጨማሪ ኣንብብ።

6

ፕስፖርትን ለመውሰድ ቀጠሮ ያዝ

ኣንተ: ማለት የውጭ ዜጋ ፓስፖርት የምትወስድ ሰውየ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመሄድህ በፊት ኣስቀድመህ ቀጠሮ ያዝ። ፓስፖርትን ለሚወስድ ሰው ሁሉ ቀጠሮ ለመያዝ ኣትርሳ። ለልጆችህ ፓስፖርት ልታወጣላቸው ከፈለግክ ለያንዳንዳቸው ቀጠሮ ያዝላቸው።

7

ፓስፖርትህ ከስደተኞች ጉዳይ  ጽ/ቤት ወሰደው

ፓስፖርትህ በኣካል መጥተህ ነው የምትወስደው። ከ 18 ዓመት በታች የሆኑት ህጻናት በሚመለከት ወላጅ ወይም ኣሳዳጊ ነው መጥቶ የሚወስደው። ህጻኑ መምጣት ኣያስፈልገውም።

ህጻኑን የሚያሳድግ ሰው ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚያቀርበው ማመልከቻ ኣስቀድሞ ኣሳውቆ ከሆነ ግን ከ15 ዓመት በላይ የሆነው ህጻን ራሱ መጥቶ ፓስፖርቱን ሊወስድ ይችላል። 

Last updated: