የጥበቃ ሁናቴ

Skyddsstatus – amhariska

የስዊድን  መንግስት የተባበሩት መንግስታትን የስደተኞች ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ በዚህ ስምምነት ውስጥም ስደተኞች ስደተኛ እንደሆኑ እውቅትና የማግኘት መብት ተጠቅሷል::

በስዊድን ውስጥ ተግባራዊ የሚሆነው የስደተኞች መብት በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ከተደረገው ስምምነት መሠረትም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡ በዚህም ስምምነት መሠረት ሁሉም የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙ ሰዎች ይህንን የሚያገኙት በዚያ ሀገር ውስጥ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ከመኖር በተጨማሪ ጥበቃ ስለሚያስፈልጋቸው ነው፡፡

ስደተኛ ተደርገው መቆጠር ከፈለጉ ስደተኛ መሆንዎን የሚገልጽ ወረቀትይሰጥዎታል- ይህ በጄኔቫ ስመምምነት እንዲሁም በአውሮፓ ሕብረት ስምምነት መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ወረቀት ነው፡፡

እንደ ፖለቲካዊ ስደተኛ ታስበው መኖሪያ ፈቃድ ስለ ማግኘት እዚህ ያንብቡ

ውስን የሆነ ጥበቃ የሚያስፈልገው ሰው ሆነህ የምትታይ ከሆነ ውስን የሆነ ጥበቃ እንደሚደረግልህ የሚጠቁም ወረቀት ይሰጣህ- ይህ በአውሮፓ ሕብረት ውስጥ ባለ መመሪያ መሠረት የሚሰጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡

አማራጭ ከለላ እንደ ሚያስፈልገው ሰው ታስበው መኖሪያ ፈቃድ ስለ ማግኘት፥ እዚህ ያንብቡ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመኖሪያ ፈቃድ ካገኛችሁ በበኋላ ልዩ ለሆነ ፈቃድ ማመልከት

ስዊድን አገር ለመኖር ፈቃድ የተሰጦት ከሆነ፥ ሆኖም ምንም የጥገኝነት መገለጫ ካልተሰጦት፥ ቆይተው እንዲሰጥዎ ማመልከቻ ማቀረብ ይችላሉ። ይህ ጉዳይ፡ ለርሶ አማራጭ ከለላ እንደ ሚያስፈልገው ሰው ታስበው መገለጫ የተሰጥዎትም፥ የስደተኛ መገለጫ እንዲሰጦት የሚፈልጉም ይመለከታል።

የመኖሪያ ፈቃድ ካገኛችሁ በኋላ በቁጥር 158011 የተቀመጠውን የጥበቃ መጠየቂያ ቅጽ በመሙላት የጥበቃ ፈቃድ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Ansökan om skyddsstatus, blankett nummer 158011 (በስዊድሽኛ ቋንቋ) Pdf, 688.6 kB, opens in new window.

የጥበቃ ፈቃድ እንዲሰጥ ይግባኝ መጠየቅ

ከመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔ ውጪ ለጥበቃ የቀረበ ማመልከቻ ውድቅ በሚሆበት ሰዓት እንደገና ይግባኝ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ይህ ማለት አንድ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጠው ሰው እንኳን የጥበቃ ፈቃድ ለምን እንዳልተሰጠው ይግባኝ መጠየቅ ይችላል ማለት ነው፡፡

እንዴት ይግባኝ መጠየቅ እንደሚቻል ተጨማሪ ያንብቡ

የጥበቃ ፈቃዳችሁ ተመልሶ ሊወሰድ ይችላል

የጥበቃ ፈቃዳችሁ እንደገና ሊወሰድ ይችላል፣ ለምሳሌ ከእንግዲህ ወዲያ ጥበቃ የማያስፈልጋችሁ ከሆነ ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጥበቃ እንዲሰጥ ያስፈለጋችሁ ሁኔታ የሌለ ከሆነ ወይም በጣም እና በቋሚነት የተለወጠ እንደሆነ ነው፡፡

የገዛ ሀገራችሁን ጥበቃ ለመጠቀም የሚፈልጉ ከሆነ የስደተኝነት ፈቃዳችሁ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያኸል ለአዲስ ብሄራዊ ፓስፖርት ካመለከቱ ወይም የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲን የድሮ ፓስፖርት እንዲመልስላችሁ የጠየቃችሁ እንደሆነ፡፡

የስደተኝነት ፈቃዳችሁ ተወሰደ ማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሊኖራችሁ አይችልም ማለት አይደለም፡፡  ይሁን እንጂ ከቦታ ቦታ መጓጓዥያ ፈቃድ ካላችሁ የጥበቃ ፈቃዳችሁ ሲነሳ ወዲያውኑ መመለስ ይኖርባችኋል፡፡

ስለ ስደተኞች የተጻፉ ስምምነቶችን ይበልጥ አንብቡ፡፡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

በወዳጅ ሀገራት መካከል የተደረሱ የጋራ ስምምነቶችን አንብቡ (በስዊድሽኛ ቋንቋ) External link, opens in new window.

የብቃት መመሪያውን ያንብቡ External link, opens in new window.

Last updated: