የድጋፍ ጥረቶች

Stödinsatser – amhariska

ወደ ትውልድ ሀገርዎ የሚመለሱ ከሆነ፣ ከሚገጥምዎት ማህበራዊው ኖሩ ጋር እንደገና እንዲላመዱ የሚያግዝዎትን ልዩ-ድጋፍ (stödinsatser) መጠየቅ የሚችሉበት ዕድል አለዎት። ይህ ልዩ-ድጋፍ የሚሰጠው አገርዎ ውስጥ በሚገኝ ድርጅት አማካይነት ሲሆን፣ ስራው የሚከናውነው ግን በአውሮፓ ሕብረት የመልሶ ማቋቋም አገልግሎት የጋራ መርሃ ግብር (EU Reintegration Programme, EURP) በኩል ነው።

ለፍልስጤም የሚደረገው ድጋፍ ቆሟል

”Caritas” የተባለው የአሁኑ አጋር ድርጅት፥ በሀገሪቱ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት፥ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ዕድል አመቺ አለመሆኑን አስታውቃዋል።

ወደ ኢራቅ ለመመለስ ለሚፈልጉ የሚሰጥ የሰፋ የድጋፍ እድል

ከጁን 2023 ጀምሮ ማንኛውም ሰው በራሱ ፍላጎት ወደ ኢራቅ የሚመለስ ለያንዳንዱ ሰው 5,000 ዩሮ እርዳታ ለማግኘት ማመልከት ይችላል። ይህ ሰፋ ያለ የተራዘመው የድጋፍ እድል እስከ ጃንዋሪ 31 ቀን 2024 ድረስ፥ ለተወሰነ ጊዜ ይሠራል። ለሰፋ እና ለተራዘመ ድጋፍ የማመልከት እድሉ፥ ቀደም ሲል የመመለስ አሉታዊ አመለካከት ለነበራቸው፥ አሁን ግን በራሳቸው ፈቃድ ለመመልሰ ለሚመርጡ ሰዎችም ሊሠራ ይችላል።

የሚሰጥዎት ልዩ-ድጋፍ (Stödinsatserna) በዋናነት እርስዎ ስራ እንዲያገኙና ራስዎን ማስተዳደር እንዲችሉ የሚያበቃዎት አገልግሎይት ሲሆን ከእርሶ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ነው።

ከታች ከተዘረዘሩት ሃገራት ወደ አንዱ የሚመለሱ ከሆን ድጋፉን መግኘት ይችላሉ፣

አርመኒያ፣ ባንግላድሽ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ፣ ኤል ሳልቫዶር፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ጋምቢያ፣ ኢራቅ፣ ጆርዳን፣ ሞንጎሊያ፣ ሞሮኮ፣ ናይጀሪያ፣ ፓኪስታን፣ ፍልስጤም፣ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድ።

ወደ ሞንጎሊያ በግዳጅ የሚመለሱ ሰዎች (በፖሊስ ታጅበው ለሚሸኙ ማለት ነው)፥ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ድጋፍ ማግኘት አይችሉም።

የልዩ ድጋፍ ዓይነቶች

ወደ ሃገራችሁ ለምትመለሱ ሰዎች የሚደረግላችሁ ድጋፍ ከግል ፍላጎታችሁ ጋር የሚጣጣም ሲሆን የድጋፍ ዓይነቶቹም የሚከተሉትን ያካትታሉ ።

  • አገርዎ ሲገቡ በአይሮፕላን ማረፊያ አቀባበል
  • ግዚያዊ የማረፊያ ቦታ
  • የግል ድርጅት እንዲከፍቱ፣ ድጎማ
  • ወደ ስራ ዓለም እንዲገቡ ፣ እርዳታ
  • ስልጠና (የሙያ ስልጠናን ጨምሮ)
  • የስራ ምክር
  • ከባለ-ስልጣናት ጋር በሚገናኙበት ግዜ፣ ድጋፍ
  • የሕግ ምክር
  • የሕክማና አገልግሎት

ድጋፉን ለማግኘት ማሟላት ያለብዎት

አዋቂም ይሁኑ ልጅ የሚከተልቱን ካሟሉ ድጋፉን ማግኘት ይችላሉ፣

  • የጥገኝነት ማመልከቻው ውድቅ ከሆነ ወይም ስዊድን ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት ያስገቡትን ማመልከቻ ከሳቡ፣
  • ሊመለሱበት ያሰቡት አገር እርስዎን ይቀብሎታል ተብሎ የሚታመን ከሆነና እርስዎም ራስዎን በዚያ አገር ለማቋቋም እቅድ ያለዎት ከሆነ፣
  • ማመልከቻውን በሚያስገቡበት ወቅት ስዊድን ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፣

በፍርድቤት ከሃገር እንዲወጡ ተበይኖበት ከሆነ ድጋፉን የማግኘት መብት አይኖርዎትም።

ማመልከቻ እና ውሳኔ

የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነ ወይም ስዊድን ውስጥ ጥገኝነት ለማግኘት ያስገቡትን ማመልከቻ ከሳቡ ድጋፍ መጠየቂያ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። ጉዳይዎ በስድተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት እየታየ ከሆነ ማመልከቻውን የእርስዎን ጉዳይ ለያዘው ጸሐፊ ያቀርባሉ፣ በዚህ መሰረት ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ወይም አለመሆኑን በተመለከተ ውሳኔ የሚሰጠው የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ይሆናል። ጉዳይዎን የያዘው ፖሊስ ከሆነ ማመልከቻውን የሚያስገቡት ለፖሊስ ይሆናል፣ ውሳኔ የሚሰጥውም ፖሊስ ነው። ውስኔውን ይግባኝ ማለት አይቻልም።

የድጋፉ መጠን

በራስ ተነሳሽነት ወደ ሀገርዎ መመለስ ምርጫዎ ከሆነ 2500 ዩሮ ያክል ልዩ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። የፖሊስ ባለ-ስልጣን እርስዎ አገር ውስጥ ከጥቂት ሳምታት በላይ እንዳይቆዩ (avvisa) ወይም ሀገሪቱ ውስጥ ረዘም ላለ ግዜ ከቆዩ በኋላ ከሃገር እንዲወጡ (utvisa) የማድረግ ሃላፊነት ወስዶ ከሆነ፣ በአንዳንድ ሃገራት 2000 ዩሮ የሚያክል ድጋፍ የሚሰጥበት ሁኔታ አለ። እናንት አሳዳጊ ወይም ሞግዚት የሌላችሁ ልጆች፣ ፖሊስ ከሃገር እንዲያስወጣችሁ ሃላፊነት ቢወስድም ቅሉ የሚሰጣችሁ የድጋፍ መጠን አይቀንስም።

አገርዎ በገቡበት ለመጀመሪያዎቹ ሶስት ቀናት ውስጥ የሚጠቀሙበት፣ ከግል ፍላጎትዎ ጋር የሚጣጣም፣ የገቢ ድጋፍም (ankomststöd) ማግኘት ይችላሉ። ድጋፉ ለአንድ ሰው እስከ 615 ዩሮ የሚደርስ ሲሆን ገንዘቡን እርስዎ ለፈለጉት ጉዳይ ሊያውሉት ይችላሉ። .

ስለ ድጋፉ ተጨማሪ መረጃ

ድጋፍ መጠየቂያ ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም መረጃ ከፈለጉ ስዊድንን ለቅቀው ከመሄድዎ በፊት፣ ጉዳዩ የሚመለከተውን ድርጅት በስልክ ወይም ኢ-ሜል ማግኘት ይችላሉ። ድርጅቱን ሊያገኙ የሚችሉበትን የስልክ ወይም የኢ-ሜል አድራሻዎችን በአቅራቢያዎ ካለው መስተንግዶ ክፍላችን ማግኘት ይችላሉ።

Last updated: