የቀን አበል እና የመኖሪያ ቤት ወጪን የሚመለከት ለውጥ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእርስዎን የቀን አበልና እና የመኖሪያ ቤት ድጎማ የማግኘት መብት በሚያጣራበት ወቅት ከአሁን በኋላ የባለቤትዎን ወይም የኑሮ ጓደኛዎን ገቢ ከግምት የሚያስገባና በዚያ ላይ ተመስርቶ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል።

እናንት ጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም የገፍ-ስደት-መመሪያ (massflyktsdirektivet) መሰረት ግዚያዊ ከለላ የተሰጣችሁ ሰዎች፣ የራሳችሁ መተዳደሪያ ገንዘብ ከሌላችሁ ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብት አላችሁ። ከሁን በፊት፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት፣ የኢኮኖሚ ድጋፍ ማግኘት ይገባዎት እንደሆነ በሚያጣራበት ወቅት የርሶን ባለቤት ወይም የኑሮ ጓደኛ ገቢ ይኑራቸው/ አይኑራቸው ከግምት አስገብቶት አያውቅም ነበር። ዳሩ ግን፣ በስዊድን ሕግ መሰረት በጋብቻ የሚኖሩ ሰዎች ወይም በትዳር መልክ አብረው የሚኖሩ ሰዎች፣ የቤተሰብ ኢኮኖሚን በተመለከተ የጋራ ሃላፊነት ስላላቸው፣ ከአሁን በኋላ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት እርስዎ የኢኮኖሚ ድጎማ የሚገባዎት መሆኑን በሚያጣራበት ወቅት የኑሮ ጓደኛዎን ገቢ ከግምት አስገብቶ የሚያሰላ ይሆናል።

ሁለቱም ወላጆች የመኖሪያ ቤት ወጪ ይሸፍናሉ

የተደረገው ለውጥ ሁለቱም ወላጆች የመኖሪያ ቤታቸውን ወጪ መሸፈን አለባቸው የሚል ነው፣ ከሁለቱ አንዱ ብቻ የሚሰራና ገቢ ያለው ቢሆንም።

ለመኖሪያ ቤት ወጪ ምን ያህል መክፈል እንዳለብዎት ለማወቅ እዚህ ያንብቡ

ብዙዎች ከፍተኛውን የቀን አበል እርከን ማግኘት ይችላሉ

እስከ አሁን በነበረው ሁኔታ ከአንድ የትዳር ወይም የኑሮ ጓደኛው ጋር እየኖረ የመኖሪያ ቤት ወጪውን በጋራ የሚሸፍን አዋቂ ሰው በነፍስ ወከፍ በቀን 61 ክሮኖር ያህል ገንዘብ ያገኝ ነበር። ከአሁን በኋላ በጋብቻ እና በአብሮ ነዋሪነት (sambor) የሚኖሩ ብቻ ናችው እንደ አብሮ ነዋሪ የሚቆጠሩት። ይህም ማለት አንድ ብቻውን የሚኖር አዋቂ ሰው በአንድ መኖሪያ ቤት በደባልነት የሚኖር ወይም ከጓደኞቹ ጋር አንድ ቤት የሚጋራ ከሆነ በቀን 71 ክሮኖር ያህል ከፍ የሚል ገንዘብ ያገኛል ማለት ነው። በ 18 – 20 የዕድሜ ክልል ወስጥ ያሉ የት/ ቤት ታዳጊዎች ከፍ ሲል እስከ 61 ክሮኖር በቀን ሊያገኙ ይችላሉ።

ምን ያህል የኢኮኖሚ ድጋፍ ሊያገኙ እንደሚችሉ ለማወቅ እዚህ ያንብቡ

ኢኮኖሚዎ ሲቀየር ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያሳውቁ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት፣ እርስዎ የኢኮኖሚ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ መሆንዎን በሚገባ ማጣራት እንዲችል ኢኮኖሚዎ በሚቀየርበት ግዜ ለጽሕፈት ቤቱ መንገር አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ እርስዎ ወይም የኑሮ ጓደኛዎ ሥራ ከያዙና ገቢ ማግኘት ከጀመሩ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤትን መገናኘትና መንገር ይኖርብዎታል። የመኖሪያ ቤትዎን ራስዎ ፈልገው ካገኙ፣ የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ፣ ቤት ያገኙበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የሚወሰን ይሆናል። ሁሌ የመኖሪያ አድራሻዎን በሚቀይሩበት ግዜ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያሳውቁ።