የጥገኝነት ማመልከቻዎ ውሳኔ ከተሰጠበት በኋላ

Efter beslut om din ansökan om asyl – amhariska

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ለጥገኝነት ማመልከቻዎ ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ፥ ውሳኔው ምን እንድሆነ እንዲያውቁ ለማድረግ የተለያየ መላ መጠቀም ይችላል። አንድ የጽሕፈት ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ ቢሮ ድረስ ጥርቶ ውሳኔውን በአካል እንዲገልጽሎት ማድረግ እንችላለን፣ ወይም ውሳኔው በደብዳቤ መልክ ተጽፎ በፖስታ እንዲደርሶት ማድረግም ይቻላል።

አንድ ባለ ጉዳይ የተላለፈውን ውሳኔን እንዲያውቅ ማድረግ በስዊድንኛ (delgivning) ወይም “ውሳኔ ማሳወቅ” ይባላል። ውሳኔው በፖስታ እንዲደርሶት ማድረግ ደግሞ (förenklad delgivning) ወይም በቀላል መላ ውሳኔ በደብዳቤ ማሳወቅ ይባላል። ውሳኔ በደብዳቤ እንዲደርሶት ቢደረግም ቅሉ የጽሕፈት ቤቱ መስተንግዶ ክፍል ድረስ ተጠርተው በአንድ አስተርጓሚ ረዳትነት ስለ ውሳኔው መረጃ እንዲሰጥዎትም ይደረጋል።

ውሳኔ በቀላል መንገድ ማሳወቅ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን በደብዳቤ የማሳወቅ መላ በመጠቀም፣ ወሳኔውን እርስዎ ቀድም ብለው በሰጡን የመኖሪያ አድራሻዎ በኩል በፖስታ እንዲደርስዎት ያደርጋል። በሚቀጥለው የሥራ ቀን ደግሞ፣ የውስኔው ሰነድ እርስዎ ጋር መድረሱን ለማጣራት፣ ሌላ አዲስ መቆጣጠሪያ መልዕክት እንልካለን። በዚህ መቆጣጠሪያ መልዕክት ላይ ውሳኔው የተላለፈበት ዕለት በውል ሰፍሮ ይገኛል። ውሳኔው ወደ እርሶ ከተላከ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔው ደርስዎታል ብሎ ይደመድማል።

ትክክለኛ አድራሻዎን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፣ አዋቂ የቤተሰብዎ አባላትም ስም በመኖሪያ ቤትዎ በር ላይ ወይም የፖስታ ሳጥናችሁ ላይ በግልጽ ተጽፎ እንዲታይ ማድረግም ያስፈልጋል። የፖስታ ሳጥንዎን በየጊዜው መመልከት አይዘንጉ። አድራሻዎን ሲቀይሩ አዲሱን አድራሻ ወዲያውኑ ያሳውቁን።

ስለ ውሳኔ ያለው መርጃ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን በተመለከተ ያለውን መርጃ በቀላሉ የማሳወቅ ማላ - ማሳወቅ ቢመርጥም ቅሉ፣ እርስዎ የጽሕፈት ቤታችን እንግዳ መስተንግዶ ክፍል (mottagningsenheten) ድረስ እንዲመጡና፥ አንድ ጸሃፊ ጋር እንዲገናኙ ማደረግ ሁሌ አይቀርም። ከጸሓፊው ጋር በሚገናኙበት ወቅት የውሳኔው ይዘት በአንድ አስተርጓሚ ረዳትነት ይገለጽሎታል። ውሳኔው ከደረስዎ ዕለት አንስቶ ሁለት ሳምንታት ከማለፋቸው በፊት ወደ እንግዳ መስተንግዶ ክፍል ከመጡ፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያንን ዕለት ውሳኔውን ያወቁበት ዕለት አድርጎ ይቆጥረዋል።

ውሳኔ የሚጸናበት ግዜ የሚጀምረው

ውሳኔውን እንዲያውቁ የተደረገበት ዕለት ወሳኝ ነው። ወሳኔውን የማይቀበሉት ከሆነ፣ ውሳኔውን እንዲያውቁ ከተደረገበት ዕለት ጀመሮ ባሉት ሶስት ሳምንታት ግዜ ውስጥ፥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ። ውሳኔውን እንዲያውቁ የተደረገበት ዕለት አንስቶ ሶስት ሳምንታት ሲያልፉ ውሳኔው በሕግ የጸና ይሆናል። ከዚያ በኋላ ይግባኝ ማለት አይቻልም።

ይህ ማለት ውሳኔው የሚጸናው፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በቀላል መላ የማሳወቅ መንገድ (förenklad delgivning) በመጠቀም ወሳኔውን በፖስታ እንዲደርሶት ካደረገበት ዕለት አንስቶ፥ ከአምሥት ሳምንታት በኋላ ነው።

ውሳኔው አዎንታዊ ከሆነ

የጥገኝነት ጥያቄዎ አዎንታዊ መልስ ካገኘ በስዊድን የሞኖሪያ ፈቃድ ያገኛሉ፣ ስዊድን ውስጥ የመኖርና የመሥራት መብትም ይኖርዎታል ማለት ነው። የመኖሪያ ፈቃዱ ውሳኔን ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል።ዎንታዊ መልስ ቢያገኙም፣ በሳኔ ውስጥ አንዳንድ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የማይቀበሉት ወይም የማጥምዎት ነገር ሊኖር ይችላል። ይህ በሚሆንበት ግዜ ይግባኝ ለማለት የሶስት ሳምንት ግዜ ይኖርዎታል። ሶስት ሳምቱ ግዜ የሚቆጠረው ውሳኔውን እንዲያውቁ ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ ነው።

የስዊድን መኖሪያ ፈቃድ ማግኘትን በተመለከተ የበለጠ ለማንበብ

ውሳኔው አሉታዊ ከሆነ

የጥገኝነት ጥያቄዎ አሉታዊ መልስ ካገኘ ጥያቂዎ ውድቅ ሆነ (får avslag) ማለት ነው። ይህም ማለት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት፥ እርስዎ በስዊድን የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሠጥዎት የሚችል በቂ ምክንያት አለዎት ብሎ ማመን አልቻለም ማለት ነው። አሉታዊ መልስ ካገኙ፡ ያለዎት ምርጫ ሁለት ናቸው። ውሳኔውን በጸጋ ተቀብለው ወደ መጡበት መመለስ ወይም ደግሞ የይግባኝ ማመልከቻ ማስገባት ነው።

የጥያቄዎ ውድቅ መሆንን በተመለከተ የበለጠ ለማንበብ

Last updated: