መቀመጥ ከተፈቀደልዎ

Om du får stanna – amhariska

የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብተው የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ካገኙ ስዊድን ውስጥ የመኖርና የመሥራት መብት ይኖርዎታል።

የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብታችሁ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያገኛችሁ፥ በእነዚህ ገፃት ውስጥ ጠቃሚ መረጃዎች ታገኛላችሁ። (አንዳንዶቹ ገፃት በሁሉም ቋንቋዎች ላይገኙ ይችላሉ።)

የመኖሪያ ፍቃድዎን እንደ ፖለቲካ ስደተኛ አግኝተው ከሆነ ፈቃድዎ ለሦስት ዓመት ፀንቶ ይቆያል።

ስለ መኖሪያ ፍቃድ እንደ ፖለቲካ ስደተኛ የበለጠ ያንብቡ

የመኖሪያ ፍቃድዎን እንደ አማራጭ ከለላ ፈላጊ ስደተኛ አግኝተው ከሆነ ፈቃድዎ ለ13 ወራት ፀንቶ ይቆያል።

ስለ መኖሪያ ፍቃድ እንደ አማራጭ ከለላ ፈላጊ የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

እንደ አንደ የፖለቲካ ጥገኛ ወይም እንደ አንድ አማራጭ ከለላ እንደሚያስፈልገው ሰው ወይም ወደ ትውልድ አገርዎ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ በመከሰቱ ወይም የተለየ አስጨናቂ ሁኔታ በመኖሩ ምክንያት፡ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ከሆነ፥ ከቤተሰብዎ ጋር መልሰው የመሰባሰብ መብት ይኖርዎታል።

ስለ ከቤተሰብ ጋር መልሶ ለመገናኘት ያለው ዕድል የበለጠ ያንብቡ

የሀገርዎን ፓስፖርት የማውጣት ዕድል ከሌልዎት ከኢሚግሬሽን ፓስፖርት እንዲወጣልዎት ማመልከት ይችላሉ።

ስለ የዕንግዳ ጉዞ ሰነድ (främlingspass) የበለጠ ያንብቡ

ስለ ጊዜያዊ የዕንግዳ ጉዞ ሰነድ (provisoriskt främlingspass) የበለጠ ያንብቡ

ስለ ፖለቲካ ጥገኞች የሚሰጥ የጉዞ ሰነድ (resedokument) የበለጠ ያንብቡ

በጊዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድዎ ከወደቀ በኋላ ስዊድን ውስጥ መቀመጥ የሚሹ ከሆነ ፈቃድዎ ከመውደቁ በፊት ቀደም ብለው ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል። የመኖሪያ ፈቃድዎ ለማደስ ወይም ለማራዘም በሚያመለክቱበት ግዜ፥ በዚያው አጋጣሚ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጥዎት ማመልከት ይችላሉ።

ስለ የተራዘመ መኖሪያ ፈድቃ ጉዳይ የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: