የመጓጓዣ ሰነድ (resedokument) ለማውጣት ስለማመልከት

Ansök om rese­do­ku­ment – amhariska

መሰረት እንደ አንድ ስደተኛ ዕውቅና ሲያገኙ ወይም አገር-የለሽ ሆነው የ1954 ዓ. ምቱን የኒውዮርክ ጉባዔ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሲሁኑ ነው። የስዊድን ሃገር ዜግነት እያለዎት ፓስፖርት ማውጣት ከፈለጉ ከፖሊስ ጽ/ ቤት ዘንድ ሄደው የስዊድን ፓስፖርት እንዲሰጥዎት ማመልከት ይኖርብዎታል።

የመጓጓዣ ሰነድ (rese­do­ku­ment) ለማግኘት መሟላት ያለበት

የመጓጓዣ ሰነድ ማውጣት የሚቻለው፡-

  • በ1951 ዓ. ምቱ የጄኔቫ ጉባዔ መሰረት እንደ አንድ ስደተኛ ዕውቅና ሲያገኙ ወይም አገር-የለሽ ሰው ሆነው የ1954 ዓ. ምቱን የኒውዮርክ ጉባዔ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለብዎት

የመጓጓዣ ሰንድ (resedokument) አይሰጥዎትም እንዲህ ከሆነ፡-

  • የስዊድን አገር ዜግነት ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል/ኢኢኤስ አገሮች (EU/EES) ዜግነት ካለዎት አይሰጥም።

የፖለቲካ ጥገኛ ካልሆኑ፥ በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት ”የእንግዳ-መጓጓዣ ፓስፖርት” (främlingspass) ሊያገኙ ይችላሉ።

የእንግዳ-መጓጓዣ ሰነድ ”främlingspass” እንዴ ሚጠየቅ እዚህ ያንብቡ።

ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-tjänsten) ለመጠቀም የሚያስፈልግዎት

የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-tjänsten) ለመጠቀም የሚከተሉት ያስፈልጋሉ፥

  • ስዊድን ውስጥ ተቀማጭ መሆንና በህዝባዊ መዝገብ የተመዘገቡ መሆን
  • የባንክ መታወቂያ (e-identification) ሲኖርዎት
  • የስዊድን አገር መታወቂያ ካርድ
  • ምናልባት ቀደም ብሎ የወጣ “የመጓጓዣ ሰነድ” (resedokument) ካለዎት፥ እዚያ ላይ ያለውን ማንነት የሚገልጽ ገጽ እና ማሕተም የተደረገባቸውን ሌሎች ገጻት ሁሉ ቅጅ/ ኮፒ ማድረግ ወይም መጓጓዣ ሰነዱ መጥፋቱን የሚገልጽ የፖሊስ ማመልከቻ ማቅረብ።

ከማመልከቻዎ ጋር የፓስፖርት ቅጅ እንዴት አያይዘው መላክ እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Lለልጅ ”የእንግዳ-መጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት፥ ከ18 ዓመት በታች ላሉ ልጆች በሚል ርዕስ ስር ያለውን መረጃ ያንብቡ

ማንነትዎን ከዚህ በፊት በሚገባ ያላረጋገጡ ከሆነ (ምንም ዓይነት ፓስፖርት ከሌልዎት) የትውልድ ሃገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትዎን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ኮፒ ወይም ቅጂ ማያያዝ ይችላሉ፣ ለምሳሌ መታወቂያ ካርድ፥ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም ወታደራዊ ደብተር ሊሆን ይችላል።

ከማመልከቻዎ ጋር አያይዘው እንዲያቀርቡ የጠየቅኖትን ሰነዶች በሙሉ ካልላኩልን፥ ውሳኔ የሚያገኙብት ቀን ሊረዝም የሚችል መሆኑን ያስተውሉ።

Ett främlingspass

በኤሌክትሮኒ አገልግሎት (e-tjänsten) ቀነ ቀጠሮ መያዝ

በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አማካይነት ማመልከቻዎን ከመላክዎ በፊት የጣት አሻራ እና ፎቶግራፍ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ቀነ ቀጠሮ የመያዙ ሂደት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቱ (e-tjänsten) አንድ አካል ነው።

በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አማካይነት የያዙትን ቀነ ቀጠሮ የሚሰርዙበትን ወይም የሚቀይሩበትን መንገድ የሚገልጽ መረጃ፥ በኢሜል በምንልከው፣ ማመልከቻ ማስገባትዎን የሚመሰክር ደረሰኝ ላይ ያገኛሉ።

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች በራሳቸው የመጓጓዣ ሰነድ (resedokument) ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት አይችሉም። በልጆቹ ፈንታ የመጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት የሚችለው የልጁ ህጋዊ አሳዳጊ ወይም ህጋዊ ሞግዚት (gode man) ነው።

ልጅዎ ሁለት አሳዳጊዎች ወይም ህጋዊ ያሉት ከሆነ እና ማመልከቻውን በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚያስገቡ ከሆነ፥ ”Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass” ቅዕ ቁጥር 246011 ማለትም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ለሆነ ልጅ ”የእንግዳ-ፓስፖርት” ወይም ”የመጓጓዧ-ፓስፖርት” እንዲያወጣለት ፈቃድ የሚሰጠውን ቅጽ ሞልተው በኤሌክትሮኒክ አገልገሎት መላክ ያስፈልጋል። ቅጹ ላይ ሁለቱም አሳዳጊዎች፡ ምስክሮች ባሉበት በፊርማቸው ማረጋገጥ አለባቸው።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 246011 (በሽወደንኛ) Pdf, 657.8 kB, opens in new window.

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 247011 (በእንግሊዝኛ) Pdf, 701.3 kB, opens in new window.

ማመልከቻውን የሚያስገቡት እንደ ሞግዚት በመሆን ከሆነ፥ የሞግዚትነት ሥልጣን ማስረጃ ሰነድ እና መታወቂያ ወረቀትዎን አያይዘው መላክ ይኖርብዎታል።

ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የሌሉ ልጅ ፎቶግራፍ ለመነሳትም ሆነ የጣት አሻራ ለመስጠት በሚሄድበት ግዜ፥ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት አብሮት መሄድ ይገባዋል።

የመጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት ምንም ገንዘብ አያስከፍልም፥ ይሁን እንጂ የመጓጓዣ ሰነዱን ለመረከብ ሲመጡ የሚከፍሉት ገንዝብ ይኖራል። ክፍያውን፡ የመጓጓዣ ሰነድ ለመረከብ ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ሲመጡ በካርድ መፈጸም ይችላሉ።

ክፍያውን በካርድ መክፈል የማይችሉ ከሆነ በባንክጂሮ (bankgiro) በኩል መክፈል ይችላሉ። አልያም የጣት አሻራ ለመስጠት እና ፎቶግራፍ ለመነሳት ሲመጡ የመክፈያ ወረቀት እንዲሰጥዎት ጽ/ ቤታችን ውስጥ የሚያስተናግድዎትን ሰራተኛ ይጠይቁ። ክፍያውን፡ ኋላ የመጓጓዣ ሰነድ ማውጣት የሚችሉ መሆንዎ የሚገልጽ ውሳኔ ሲደርስዎት፥ መፈጸም ይችላሉ።

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ጥሬ ገንዘብ አይቀበልም፥ እንዲሁም ክፍያው ገቢ ሳይሆን የመጓጓዣ ሰነዱን አያስረክብም።

ለመጓጓዣ ሰነድ የሚደረጉ ክፊያዎች (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የመጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት በድረገጽ ማመልከቻ ማስገባት የማይችሉ ከሆነ “Ansökan om resedokument, 108021” የሚል ርዕስና የቅፅ ቁጥር ያለበትን ፎርም መሙላትና የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት የፈቃድ ልዩ ክፍል ድረስ በአካል ሄድው ማስገባት ይኖርብዎታል። ወደ ጽ/ ቤት ከመምጣትዎ በፊት ቅጹ መሞላት አለበት።

ለመጓጓዣ ሰነድ ለማመልከት፡ ቅፅ ቁጥር 108021 ይጠቀማሉ (በስዊድንኛ) Pdf, 688.4 kB, opens in new window.

ለመጓጓዣ ሰነድ ለማመልከት፡ ቅፅ ቁጥር 109021 ይጠቀማሉ (በእንግሊዝኛ) Pdf, 791.5 kB, opens in new window.

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች በራሳቸው የመጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት አይችሉም። በልጆቹ ፈንታ የመጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት የሚችለው የልጁ ህጋዊ አሳዳጊ ወይም በህግ ሥልጣን የተሰጠው ሞግዚት ነው።

ልጁ ሁለት ህጋዊ አሳዳጊዎች ካለቱ ሁሉቱም ማመልከቻው እንዲገባ ፈቃደኞች መሆናቸውን በማመልክቻው ቅፅ ላይ በመፈረም ማረጋገጥ አለባቸው። ማመልከቻውን ለማስገባት ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት የሚመጣው አንደኛው አሳዳጊ ብቻ ከሆነ፥ ሌላኛው በማመልከቻው ቅፁ ላይ አስቀድሞ ፊርማውን ማስፈር ይኖርበታል። ፊርማው በሌላ ሶስተኛ ሰው እማኝነት መመስከር አለበት።

ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የሌሉ ልጅ፥ ፎቶግራፍ ለመነሳትም ሆነ የጣት አሻራ ለመተው በሚሄድበት ግዜ፥ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት አብሮት መሄድ ይገቧል። በተጨማሪ፡ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት፥ የሞግዚትነት ሥልጣን ማስረጃ ሰነድ እና መታወቂያ ወረቀቱን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ

ማመልከቻዎን ለማስገባት ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ከመሄድዎ በፊት ቀነ- ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። የመጓጓዣ ሰነድማውጣት የሚፈልግ እያንዳንዱ ግለ-ሰብ፣ ልጅም ቢሆን፣ መምጣት እንዳለባቸው ልብ ይበሉ። ማመልከቻ የሚያስገባ እያንዳንዱ ግለ ሰብ የየራሱን ቀጠሮ መያዝ ይኖርበታል። ብዙ ቀጠሮች በተከታታይ መያዝይችላሉ።

ማመልከቻዎን ለማስገባት ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ማመልከቻዎን ሲያስገቡ

ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ግዜ መያዝ የሚገባዎት ሰነዶች

  • የስዊድን አገር መታወቂያ ካርድ
  • የማመልከቻ ፎርም ወይም ቅፅ፥ የተሞላና የተፈረመበት (እያንዳንዱ አመልካች የየራሱ አንዳንድ ፎርም) ለአንድ ልጅ የመጓጓዣ ሰንድ እንዲወጣለት ሲያመለክቱ ሁለቱም አሳዳጊዎች መፈረም እንዳለባችሁ ልብ በሉ።
  • ምናልባት የመጓጓዣ ሰነድ ቀድሞ ተሰጥቶት ከነበረ የእሱን አንድ ኮፒ ወይም ጠፍቶብዎት ከሆነ ፓስፖርቱ መጥፋቱን የሚያሳይ ፖሊስ የሰጥዎት የማመልከቻውአንድ ኮፒ ወይም ቅጅ

ማንነትዎን ከዚህ በፊት በደንብ ያላረጋገጡ ከሆነ የትውልድ ሃገርዎን ፓስፖርት አንድ ኮፒ ማያያዝ፥ አልያም (ምንም ዓይነት ፓስፖርት ከሌልዎት) ሌላ ማንነትዎን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ኮፒ ማያያዝ ይችላሉ፣ ለምሳሌ መታወቂያ ወረቀት፥ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም ወታደራዊ ደብተር ሊሆን ይችላል።

የትውልድ ሃገርዎ ፓስፖርት ወይም ግዜው ያለፈየመጓጓዣ ሰንድ ካለዎት እነዚህን ሰነዶች ለስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት መመለስ አለብዎት። አንዳንድ ግዜ ጉዳይዎን የሚያስተናግደው ጸሃፊ (handläggaren) ከማመልከቻዎ ጋር የፓስፖርት ኮፒ ብቻ ትተው እንዲሄዱ ሊነግርዎት ይችላል፣ ይሁን እንጂ ጉዳይዎ ውሳኔ ሊሰጥበት መታየት ሲጀምር ወይም ውሳኔ ተሰጥቶበት አዲሱን ሰነድ ሊወስዱ ሲመጡ ኦሪጅናሉን ፓስፖርት እንዲያስረክቡ መጠየቅዎ አይቀርም።

ማመልከቻዎን ሊያስገቡ ሲመጡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ፎቶግራፍ ያነሳዎታል፥ የጣት አሻራዎንም ይወስዳል። ፎቶዎ፥ የጣት አሻራውና ሌላው እርስዎን የሚገልጽ መረጃ ሁሉ በአንድ ዳታ-ቺፕ ውስጥ ተጠናቅሮ የመጓጓዣ ሰነዱ ላይ ይቀመጣል። እነዚህ መረጃዎች የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ዘንድ ከቶ አይቀመጡም፥ መረጃዎቹ የሚገኙት የመጓጓዣ ሰነድዎ ላይ ካለው ዳታ-ቺፕ ውስጥ ብቻ ነው። ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የጣት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም።

የትውልድ ሃገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ ለመጓጓዝ የሚያገለግል ሰነድ ማውጣት የሚችሉብት እድል ይኖርዎት እንደሆነ ሊጠየቁ ይችላሉ። ይህ ሲሆን የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ዘንድ ማመልከቻ ሊያስገቡ ሲመጡ አንድ የመጠይቅ ቅፅ እንዲሞሉ ይሰጥዎታል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ደረ-ገጽ ላይ የእርስዎ ጉዳይ ውሳኔ እስኪያገኝ በአሁኑ ወቅት ካለውን ሁኔታ አንጻር ምን ያህል ግዜ ሊያስጠብቅዎት እንደሚችል ማየት ይችላሉ። በጉዳይዎ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች እንዲያቀርቡ የሚጠየቁበት አጋጣሚ ከተከሰተ፣ ውሳኔ ለማግኘት ከሚጠበቀው በላይ ረዘም ያለ ግዜ ሊወስድብዎት ይችላል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእርሶ ጉዳይን ተመልክቶ ሥራውን ሲያጠናቅቅ፥ የደረሰበትን ውሳኔ በፖስታ ወደ እርስዎ ይልካል።

ባሁኑ ወቅት ማመልከቻዎች ለመወሰን የሚወስደው ጊዜ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ውሳኔው በፖስታ እቤትዎ ድረስ ይላካል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የመጓጓዣ ሰነድ የማግኘት መብት እንዳልዎት ከወሰነልዎት፥ ሰነዱን ለማስረከብ በቦታው ሲደርስ እርስዎ መጥተው እንዲወስዱ የሚያሳስብ መልዕክት እንዲደርስዎት ያደርጋል። ውሳኔው ከደረስዎት ቀን ጀምሮ፥ የመጓጓዣ ስነዱን ማመልከቻ ካስገቡበት የፍቃድ ዋና ክፍል ድረስ መጥተው እስኪወስዱ የ14 ቀናት ግዜ ያህል ሊያስጠብቅ ይችላል።

የመጓጓዣ ሰነድ ማመልከቻዎን ውድቅ ከሆነ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔን ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነስ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የመጓጓዣ ሰነድ ማመልከቻዎን ውድቅ እንዲሆን ከወሰነ፥ ውሳኔውን ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

ይግባኝ የሚሉ ከሆነ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የትኛውን ውሳኔ እንዲለውጥሎት እንደፈለጉ፥ ውሳኔው ምን ላይ ስህተት እንዳለበት በሚገልጽ መልኩ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባት አለብዎት። ደብዳቤው ላይ የእርስዎን ማንነት የሚገልጹ መረጃዎች፥ የጉዳዩ መዝገብ ቁጥር እና እርስዎ ራስዎ ፊርማዎን ማስፈር ይኖርብዎታል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔ በሰጥዎት በሶስት ሳምንት ግዜ ውስጥ የይግባኝ ጥያቄዎን ማስገባት እንዳለብዎት ልብ ይበሉ።

ይግባኙን በእርስዎ ፈንታ ሌላ ሰው እንዲያደርግልዎት ከፈለኩ፥ ለግለ-ሰቡ የውክልና ሥልጣን በጽሑፍ መስጠት ይኖርብዎታል።

የመጓጓዣ ሰነዱን የሚረከቡት (የመጓጓዣ ሰነዱን ከሌላ ቦታ ዘንድ ሄደው እንዲያወጡ የሚያሳስብ አንዳች ምልከታ ካልደረሶት በቀር) ማመልከቻውን ካስገቡበት የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት የፈቃድ ልዩ ክፍል (tillståndsenhet) ወይም የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (servicecenter) ነው።

የመጓጓዣ ሰነዱን እርሶ በሚፈልጉት ልዩ ቦታ ሄደው መረከብ የሚፈልጉ ከሆነ፥ ይህንኑ ፍላጎትዎን ፎቶግራፍ ሲነሱና የጣት አሻራ ሲስጡ ለሚያገኙት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ጸሓፊ ያሳውቁ።

የመጓጓዣ ሰነድ እንድታገኙ የተወሰነላችሁ ሁሉ፥ ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ከመምጣታችሁ በፊት ቀነ ቀጠሮ መያዝ ይኖርባችኋል። የመጓጓዣ ሰነድ ለተፈቀደለት እያንዳዱ ሰው አንዳንድ ቀጠሮ መያዝ እንዳለባችሁ ልብ በሉ። የልጆችዎን የመጓጓዣ ሰነድ የሚረከቡ ከሆነ፥ ለያንዳንዱ የመጓጓዣ ሰነድ አንዳንድ ቀጠሮ መያዝ አስፈላጊ መሆኑን ያስተውሉ።

የመጓጓዣ ሰነዱን ራስዎ በአካል በመገኘት ነው መረከብ የሚችሉት። ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች አሳዳጊታቸው ወይም የሞግዚትነት ሥልጣን የተሰጠው ሰው፥ ከፈለገ ልጆቹን ሳያስከትል፥ መጥቶ መውሰድ ይችላል።

ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ራሳቸው በአካል መጥተው መውሰድ የሚችሉት አሳዳጊያቸው ቀደም ብሎ ማመልከቻ ባስገባበት ወቅት ልጁ ራሱ ብቻውን መጥቶ እንደሚወስድ አሳውቆ ከነበረ ነው።

የመጓጓዣ ሰነዱን ለመውሰድ ሲመጡ አንድ የጸና ማለትም የአገልግሎት ግዜው ያልወደቀ መታወቂያ ይዘው እንዲመጡ ያስፈልጋል። በፊት ያወጡትንየመጓጓዣ ሰነድ ቀደም ብለው ያላስረከቡ ከሆነ አሁን አዲሱን ለመውሰድ ሲመጡ ያስረክቡ።

የመጓጓዣ ሰነድ መጥተው ለመውሰድ ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ክፍያ ስለመፈጸም

የመጓጓዣ ሰነድዎን ለመረከብ አንድ ክፍያ መፈጸም ይገባዎታል። የመጓጓዣ ሰነድዎን ለመቀበል ወደ ሰደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ሲመጡ ክፍያውን በመክፈያ ካርድ ይከፍላሉ።

ክፍያውን በካርድ መክፈል የማይችሉ ከሆነ፥ የመክፈያ ወረቀት እንዲሰጥዎት ይጠይቁና የመጓጓዣ ሰነዱን ለመውሰድ ከመምጣትዎ በፊት በባንክ-ጂሮ አመካኝነት ገንዘቡን ይክፈሉ። የሰደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ጥሬ ገንዘብ እንደማይቀበል ሁሉ፥ ክፍያው ሳይፈጸም የመጓጓዣ ሰነዱን አያስረክብም።

ክፍያውን ቀደም ብለው ከፍለው ከሆነ፥ የመጓጓዣ ሰነዱን ለመውሰድ ሲመጡ፥ መክፈልዎን የሚያረጋግጡበት አንድ ደረሰኝ ማሳየት ይኖርብዎታል።

ለመጓጓዣ ሰነድ የሚደረጉ ክፊያዎች (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

በመጓጓዣ ሰንድ መጓዝ

የመጓጓዣ ሰነዱ የአውሮፓ ህብረትን የመጓጓዣ ሰነደ መስፈርቶች የሚያሟላ ሰነድ ስለሆነ ወደ ሁሉም አገሮች ሊጓዙበት ይችላሉ። ነገር ግንበ 1951 ዓ. ምቱ የጄኔቫ ጉባዔ መሰረት እንደ ስደተኛ ዕውቅና ያገኙ ከሆነ፥ የመጓጓዣ ሰነዱ ላይ ወደ ትውልድ ሃገርዎ ወይም ለስደት የተነሱበ ሃገር ዘንድ መጓዝ የማይችሉ መሆንዎን የሚገልጽ ምልከታ ይሰፍርበታል።

ማንነትዎን በደንብ ሊያረጋግጡ ያልቻሉ ሰው ከሆኑ፥ በመጓዣጓ ሰነዱ ላይ ማንነትዎ በደንብ ያልተረጋገጠ ሰው እንደሆኑ የሚገልጽ ምልከታ ይሰፍርበታል፣ ይህ ምልከታ ወደ አንዳንድ አገሮች የሚያደርጉትን ጉዞ አስቸጋሪ ሊያደርግብዎት ይችላል።

ወደ አንዳንድ አገሮች ሲጓዙ የአገሮቹ ቪዛ ሊያስፈልጎት ይችላል። ስለዚህ ወደ እነዚህ አገሮች ከመጓዝዎ በፊት፥ የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሃገራቱን ቆንስላ ጽ/ ቤቶች ያነጋግሩ።

የመጓጓዣ ሰነዱ አገልግሎት የሚጸናበት ግዜ

የመጓጓዣ ሰነድ (Ett resedokument) ጸንቶ የሚቆየው ቢረዝም እስከ ሁለት ዓመት ነው። የመጓጓዣ ሰነድን ማራዘም አይቻልም። ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ በማለቁ ምክንያት አዲስ የመጓጓዣ ሰነድ ማውጣት ካስፈለግዎት ግን እንደገና አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል።

አዲስ የመጓጓዣ ሰነድ ሲያወጡ አሁንም እንደገና ፎቶግራፍ መነሳትና የጣት አሻራ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ። በፊት የሰጡት ፎቶግራፍና የጣት አሻራ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የመረጃ ቋት ወይም ዳታ ቋት ውስጥ አይቀመጥም።

የመጓጓዣ ሰነድ ሲጠፋብዎትስ

የመጓጓዣ ሰነዱ ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቀ፥ በመጀመሪያ ለፖሊስ ማመልከት ይኖርብዎታል። በጠፋው ምትክ አዲስ ማውጣት የሚፈልጉ ከሆነ፥ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት የግድ ነው። ፖሊስ በመኖሪያ ድራሻዎ የሚልከውን የማመልከቻዎን ቅጂ ወይም ኮፒ ወይም መጥፋቱን በሚያመለክቱበት ግዜ፥ እዚያው በእጅዎ የሚሰጥዎትን የማመለከቻዎን ቅጂ ወይም ኮፒ ይዘው ይምጡ።

Last updated: