ለጥገኝነት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ከተደረገ በኋላ አዳዲስ ሁኔታዎች

Nya händelser efter avslag – amhariska

አቤቱታ ሊቀርብበት የማይችል ውሳኔ ማለት በውሳኔው ላይ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ አገሩን ለቀው ይወጣሉ ማለት ነው። በአንዳንድ ልዩ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ወደ አገርዎ እንዲመለሱ የሚገልጸው ውሳኔ ቢኖርም እንኳን ወደ አገርዎ ሊመለሱበት የማይችሉባቸው አንዳንድ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። ይህም የአፈጻጸም እንቅፋት ይባላል- ወደ አገር ውስጥ መግባትን የሚከለክለውን ወይም የማስወገድ ትእዛዝን ለመፈጸም የተጋረጠ እቅፋት መፈጠር ማለት ነው።

የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን ከተቀበሉ በኋላ አዲስ መረጃ ከመጣ ብቻ ወደ ሃገርቤትዎ የመመለስዎትን ጉዞ ሊሰርዝ ይችላል። ይህም ምናልባት፣ ለምሳሌ ሊያመለክት የሚችለው

 • በትውልድ አገርዎ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የተለወጠ ከሆነ እና በዚህም ምክንያት መመለስ የማይችሉ ከሆነ፤
 • ጉዞ ለማድረግ የማይችሉበት ህመም ካለብዎት፤
 • ለሕይወትዎ የሚያሰጋ ህመም ከተሰማዎት፣ እና በትውልድ አገርዎ የህክምና እንክብካቤ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ፤ ወይም
 • የቤተሰብዎ ሁኔታ ከተለወጠ።

ወደ አገር ስለሚያደርጉት ጉዞ መጨነቅዎ፣ ወይም በትውልድ አገርዎ ውስጥ ማኅበራዊ ወይም የኢኮኖሚ ችግር ያለብዎ መሆኑ፣  የስደተኞች ኤጄንሲን ውሳኔ ለማስቀየር በቂ ምክንያቶች አይደሉም።

ለስደተኞች ኤጄንሲ መጻፍ ይችላሉ

ከመመለስ የሚከለክሉዎትን አዳዲስ ምክንያቶች እንድናይልዎት ከፈለጉ ለስደተኞች ኤጄንሲ ደብዳቤ መጻፍ ይችላሉ። በሚፅፉት በደብዳቤ ውስጥ

 • የእርስዎ የጉዳይ ቁጥር (የእርስዎ የጉዳይ ቁጥር በ LMA card ላይ ተመዝግቧል)፤
 • በእርስዎ ጉዳይ ላይ ያለው አዲስ ነገር እና ወደ አገርዎ መመለስ ለምን እንደማይችሉ፤ እና 
 • አድራሻዎ።

ስለ ጻፉት ደብዳቤ ሊያረጋግጥ የሚችል ዶክመንት ካለዎት፣ ቢቻል ዋናውን ቅጂማካተት አለብዎ።

ደብዳቤውን በራስዎት ስም መፈረም አለብዎት። እባክዎ ውሳኔውን በፍጥነት እንዲያገኙ በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድን ቋንቋ ይጻፉ።

ራስዎ መጻፍ የማይችሉ ከሆነ፣ ሌላ ሰው እንዲጽፍልዎ መጠየቅ ይችላሉ፤ ያ በሚሆንበት ጊዜ ለስደተኞች ኤጄንሲው የውክልና ማስረጃ ማስገባት አለብዎ።

ድራሻ

Migrationsverket
601 70 Norrköping

የውክልና-ሥልጣን ምንድን ነው?

የውክልና-ሥልጣን፥ አንድ አመልካች፡ ሌላ ሰው በእሱ/ሷ ፈንታ ወይም እንደ እሱ/ሷ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲፈጽምለት በጽሁፍ መብት የሰጠበት እና በፊርማው ያረጋገጠው ሰነድ ማለት ነው። አንድ የውክልና-ሥልጣን ለምሳሌ፥ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ማመልከቻ እንዲያስገባለት፥ ለውሳኔ ምክንያት የሆኑትን ነጥቦች እንዲወስድ ወይም ውሳኔውን ይግባኝ እንዲልለት መብት የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። የውክልና-ሥልጣን በውክልና ሰጪው የተጻፈ መሆን አለበት። እንዲሁም “ሚግራሾንስቨርከት” በጠየቀ ጊዜ፥ ዋናውን ቅጅ (ኦሪጂናል ሰነድ) ማቅረብ መቻል ያስፈልጋል።

የውክልና-ሥልጣን ለሌላ ሰው መስጠት እንዲችሉ፥ ”ለሚግራሾንስቨርከት” የሚቀጥሉት ነጥቦች ያካተተ አንድ ደብዳቤ ይጽፋሉ፡-

 • የውክልና-ሥልጣን መሆኑ
 • የውክልና-ሥልጣን ሰጪው ሙሉ ስም፥ የልደት-ቀን እና ኣድራሻ
 • ውክልና-ሥልጣን ተቀባዩ፥ ማድረግ የሚችለው የተሰጠው መብት
 • የውክልና-ሥልጣን ተቀባዩ ስም፥ የማንነት-ቁጥር (ፐርሾን-ኑመር) እና አድራሻ
 • የውክልና-ሥልጣን ሰጪው ፊርማ
 • የውክልና-ሥልጣን የተፈረመበት ቀን እና ቦታው

Power of Attorney, form number 107011 (ባእንግሊዝኛቋንቋ) Pdf, 641.6 kB, opens in new window.

የስደተኞች ኤጄንሲ፣ በራሱ ተነሳሽነት ወደ አገርዎ የሚያደርጉትን ጉዞ ሊሰርዝ ይችላል

የስደተኞች ኤጄንሲ እርስዎን ወደ አገርዎ ከመመለስ የሚያግድ አዲስ ክስተት መፈጠሩን ማወቅ አለበት።  ምንም እንኳን እርስዎ ስለ አስገዳጅ እንቅፋቶች ባይጽፉልንም እንኳን፣ የስደተኞች ኤጄንሲ ወደ አገርዎ የመመለስዎን  ጉዞ ሊሰርዝ ይችላል። ወደ አገርዎ የሚያደርጉት ጉዞ ለማድረግ የማይችሉ ከሆነ ፖሊስም ለስደተኞች ኤጄንሲ የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት።

ውሳኔ

የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ውሳኔውን በፖስታ ይልክልዎታል።

ውሳኔ ምንም እንኳን ለጊዜው ቢገታም፡ ወደ አገርዎ የመመለስ ስራ ይቀጥላል

የመግታት ውሳኔ ቢስጥዎትም፥ ማለት፡ እርሶን ካገር የማስወጣት ውሳኔው ግብር ላይ ለሟል ባይቻልም፥ ወደ አገርዎ የመመለስ ስራው ግን የሚቀጥል ይሆናል። የርሶ ሀላፊነት ለምሳሌ፡ ፓስፖርት ወይም ሌላ ጊዚያዊ የጉዞ-ሰነድና፥ ወደ ትውልድ አገርዎ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት መብት ወደ ተሰጦት ሌላ አገር ለመመለስ የሚይስፈልጉ ነገሮች ሟሟላትን ያካትታል። ተጨማሪ ሀላፊነትዎም፡ ለንግግር ወይ ስለ ተሰጠው ውሳኔ መረጃ ለማግኘንት ተጠርተው እንዲገኙ ነው። ገና ውሳኔ ያልተሰጠበት፡ በግብር የሟል መደናቀፍ አስመልክቶ የገባ ማመልከቻ ቢኖርዎም፥ ጉዳዩን ይመለከቷል።

ወደ አገርዎ ከመመለስዎ በፊት ማድረግ ስላለብዎ ተጨማሪ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

“ያስፈጻሚነት-እገዳ” ማለት፡ የማባረር ወይም የማስወጣት ውሳኔ ብጊዚያዊነት ማስቆም ማለት ነው።

”ሚግራሾንስቨርከት” ሰው ለተወሰነ ጊዜ ወደ አንድ አገር ለማባረር ወይም ለማስወጣት የተደረገ ዕቅድ ለማስቆም ውሳኔ መውሰድ ይችላል። ይህ፡ ”ያስፈጻሚነት-እገዳ” (verkställighetsstopp) ይባላል።

ስለ ”ያስፈጻሚነት-እገዳ” (verkställighetsstopp) እዚህ በይበልጥ ያንብቡ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: