የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ያመልክቱ

Ansök om provisoriskt främlingspass – amhariska

አንድ መደበኛ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የማይችሉ ከሆነ ወይም ፓስፖርቱን ለማውጣት የሚፈጀውን ግዜ መጠበቅ የማይችሉበት ሁኔታ ከገጠሞት አንድ ግዜያዊ የጉዞ ሰነድ ወይም ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ይችላሉ። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የሚጸናው ለአጭር ግዜ ወይም ለአንድ የተወሰነ ጉዞ ብቻ ነው።

አንድ ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማግኘት ከሚከተሉት አማራጭዎች ውስጥ አንዳንዶቹን ማሟላት ይኖርብዎታል፡-

ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲጠይቁ የተገደዱበት ምክንያት

ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማግኘት ማሟላት የሚገባዎት ጉዳይ

የአገርዎን ፓስፖርት ሆነ ሌላ ተቀባይነት ያለው የጉዞ ሰነድ፣ ወደ ሌላ አገር ሄደው ካላመለከቱ በቀር፣ እዚሁ ስዊድን ውስጥ እንዳሉ ማግኘት የሚችሉበት ምንም መንገድ የለም።

ከስዊድን ውጭ ተጉዘው የአገርዎን ፓስፖርት መቼ፣ የት ሄደውና በምን መንገድ ማውጣት የሚችሉበትን የጉዞ ዕቅድ አለዎት።

እጅግ አስቸኳይ በሆነ ጉዳይ ወደ ውጭ አገር በፍጥነት ለመሄድ ቢያስፈልግዎትና እና፥ የአገርዎ ፓስፖርት ባይኖርዎት።

በአሁኑ ሰዓት የእንግዳ ፓስፖርት ለምን እንዳስፈለግዎ እና በምን ምክንያት የአገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ከአገርዎ ባለስልጣናት፣ ለምሳሌ ከአገርዎ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንዳልቻሉ ለስዊድን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መግለጽ ይኖርብዎታል። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ሲያመለክቱ፣ ችግርዎን የሚያስረዱ ሰነዶች ካለዎት ይዘው ይምጡ።

ቀድሞ የነበርዎት የልዩ ጥገኛ የጉዞ ሰነድ (resedokument) ወይም የእንግዳ ፓስፖርት የሚጸናበት ግዜ በማለፉ ምክንያት ወይም በከባድ የወንጀል ክስ የተፈረደቦት በመሆንዎ ምክንያት የእንግዳ ፓስፖርት ሊያገኙ አልቻሉም። ይሁን እንጂ ወደ ውጭ ለመጓዝ የሚያበቃዎ እጅግ አጣዳፊ ምክንያት ስላለዎት መጓዝ የግድ ሆኖብዎታል።

በአሁኑ ሰዓት የእንግዳ ፓስፖርት ለምን እንዳስፈለግዎ እና በምን ምክንያት የአገርዎን ፓስፖርት ወይም ሌላ የጉዞ ሰነድ ከአገርዎ ባለስልጣናት፣ ለምሳሌ ከአገርዎ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማግኘት እንዳልቻሉ ለስዊድን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መግለጽ ይኖርብዎታል። ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ሲያመለክቱ፣ ችግርዎን የሚያስረዱ ሰነዶች ካለዎት ይዘው ይምጡ።

የስዊድን አገር የመኖሪያ ፈቃድ እያለዎት (ከመጡበት አገር ሳይህን ማለት ነው) ውጭ አገር ወጥተው ባሉበት ሰዓት የእንድግዳ ፓስፖርትዎ ወይም የጉዞ ሰነድዎ በመጥፋቱ ምክንያት ወደ ስዊድን ለመመለስ ፓስፖርት ለማግኘት ኣስፈላጊነቱ ቢያጋጥምዎት።

ፓስፖርትዎ መጥፋቱን በወቅቱ ለሚገኙበት አገር ፖሊስ ያመለክታሉ፣ ክዚያም ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለመጠይቅ በዚያ አገር ከሚገኘው የስዊድን ኤምበሲ ወይም የስዊድን ቆንስላ ዘንዳ፥ የፖሊስ ማመልከቻውን ግልባጭ ወይም ኮፒ ይዘው ይሄዳሉ።

ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት በዚህ መንገድ ያመለክታሉ

ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት፥ (ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማመልከት) ”Ansökan om provisoriskt främlingspass, 192011” የሚል ቅጽ ሞልተው ካበቁ በኋላ፥ በአካል ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሄደው ማመልከቻውን ያስገባሉ።

Ansökan om provisoriskt främlingspass (ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት በዚህ መንገድ ያመለክታሉ), ስዊድንኛ ቅጽ 192011 Pdf, 731.3 kB, opens in new window.

Application for an emergency alien's passport (ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት በዚህ መንገድ ያመለክታሉ), እንግሊዝኛ ቅጽ 193011 Pdf, 787.3 kB, opens in new window.

ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች

ከ 18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በራሳቸው ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲሰጣቸው መጠየቅ የለባቸውም። በእነሱ ፈንታ መጥየቅ የሚችለው የልጁ አሳዳጊ ወይም ሞግዚት መሆኑ በህግ የሚታወቀው ሰው ራሱ በግሉ ነው።

የልጁ አሳዳጊዎች ተብለው በህግ የሚታወቁት ሰዎች ሁለት ከሆኑ፥ (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ)፥ “Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass (främlingspass eller resedokument) för barn under 18 år, 246011”፥ የሚለው ቅጽ ላይ የሰፈርውን ውል ሁለቱም አሳዳጊዎች መቀበላቸውን በፊርማቸው ማረጋገጥና፥ ይህንኑ በሁለት እማኞች ማስመስከር ይኖርባቸዋል።

Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass (främlingspass eller resedokument) för barn under 18 år (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ), ስዊድንኛ ቅጽ 246011 Pdf, 657.8 kB, opens in new window.

Consent for the Swedish Migration Agency to issue a passport (alien's passport or travel document) for a child under the age of 18 (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ), እንግሊዝኛ ቅጽ 247011 Pdf, 701.3 kB, opens in new window.

እንደ ልጁ ሞግዚት ሆነው ማመልከቻ የሚያስገቡ ከሆነ ሞግዚትነትዎ የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰንድና የመታወቂያ ወረቀትዎን ኮፒ ከማመልከቻው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርብዎታል።

ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የማይቀመጡ ልጅ ፎቶግራፍ ለመነሳትና የጣት አሻራውን ለመስጠት ሲመጣ፥ ሞግዚቱ ከልጁ ጋር አብሮት በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት መገኘት ይኖርበታል።

ቀነ ቀጠሮ

ማመልከቻ ለማስገባት ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከመምጣትዎ በፊት ቀነ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው ለየራሱ ቀጠሮ መያዝ እና ለያንዳንዱ ሰው የየራሱን ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልጋል። ብዙ ቀነ ቀጥሮች በቅደም ተከተል መያዝ ይቻላል።

ቀነ ቀጠሮ ለመያዝ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

በውጭ አገር የሚገኙ ከሆነና ወደ ስዊድን ለመመለስ ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የሚፈልጉበት ሁኔታ ከተፈጠረ፥ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው የስዊድን ኤምበሲ ወይም የቆንስላ ጽ/ ቤት ዘንድ ሄደው ምን ማድረግ እንዳለብዎት መረጃ ይጠይቁ።

ማመልከቻ ያስገቡ

ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ግዜ የሚከተሉትን መያዝ አይዘንጉ

  • የማመልከቻ ቅጽ፣ የተሞላ እና የተፈረመበት (አንድ ቅጽ ለአንድ ሰው)
  • ቀደም ብሎ ያወጡት የእንግዳ ፓስፖርት ካለዎት
  • የአገርዎ ፓስፖርት ወይም ሌላ ማንነትዎን የሚገልጽ ሰነድ ወይም መታወቂያ (የሆነ ፓስፖርት ከሌለዎት ማለት ነው) ለምሳሌ ያህል የተለመደው መታወቂያ ካርድ፣ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም የውትድርና ደብተር ሊያቀርቡ ይችላሉ።
  • ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ ማመልከቻውን እንዲያስገባ ከወላጆቹ ወይም ከሕጋዊ ሞግዚቱ የይሁንታ ፈቃድ መስጫ፥ ማለትም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ልጁ የእንግዳ ፓስፖርት እንዲሰጥው መፍቀዱን የሚገልጽ ቅጽ (Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass (främlingspass eller resedokument) för barn under 18 år (የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች (የእንግዳ ፓስፖርት ወይ የጉዞ ሰነድ) እንዲሰጥ ፈቃድ መስጫ ሰነድ), 246011) ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • በፊት የነበርዎት የእንግዳ ፓስፖርት በመጥፋቱ ምክንያት፥ አዲስ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ካለብዎት፣ የእንግዳ ፓስፖርቱ መጥፋቱን የሚጠቅስ መረጃ የያዘ ከፖሊስ የተሰጥዎትን ሰነድ ግልባጭ ወይም ኮፒ
  • ከስዊድን ውጭ ተጉዘው የአገርዎን ፓስፖርት ማውጣት አስበው ከሆንና ይህን ጉዳይ ለመፈጸም ወደ ትውልድ ሃገርዎ መጓዝ ካለብዎት ወይም የሃገርዎ ኤምበሲ ወደ ሚገኝበት አገር መጓዝ ካለብዎት፣ መቼ፣ የትና እንዴት አድርገው ማውጣት እንደፈለጉ የሚገልጽና የጉዞ ዕቅዶን የሚያሳይ የጉዞ ካርታ፣

የትውልድ ሃገርዎ ፓስፖርት ወይም አሮጌ የእንግዳ ፓስፖርት ካለዎት ለስድተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤት (Migrationsverket) ማስረከብ ይኖርብዎታል። አንዳንድ ግዜ ጉዳዩን የያዘችው የስድተኛ ጉዳይ ጽ/ ቤት ጸሃፊ ከኦርጅናሉ ይልቅ የፓስፖርትዎን ኮፒ ከማመልከቻዎ ጋር እንዲሰጡ ልትጠይቅዎት ትችላለህ። ይሁን እንጂ ማመልከቻዎ መታየት ሲጀምር ወይም ውሳኔ ተሰጥቶበት አዲሱን ፓስፖርት ሊያወጡ ሲመጡ ኦሪጂናሉን ፓስፖርት እንዲያስረክቡ መጠየቅዎ አይቀርም።

ማመልከቻ ሊያስገቡ በሚመጡበት ግዜ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ፎቶግራፍ ያነሳዎታል፣ የጣት አሻራዎንም ይወስዳል። የተነሱት ፎቶግራፍ፣ የጣት አሻራዎ እና ሌሎች የግልዎ መረጃዎች በሙሉ የግዚያው እንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ በተለጠፈችው ኤሌክትሮኒክ ካርድ ውስጥ ይቀመጣሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ዘንድ የሚቀመጥ እርስዎን የሚመለከት ምንም መረጃ አይኖርም፣ እነዚህ መረጃዎች የሚቀመጡት እዚያው ፓስፖርቱ ላይ በተለጠፈችው ትንሽ ኤለክትሮኒክ ካርድ ወይም ቺፕ ውስጥ ብቻ ነው። ከ6 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት የጣት አሻራ እንዲሰጡ አይጠበቅባቸውም።

የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ከሚያስገቡ ሰዎች መሃል አብዛኛዎቹ የተወሰነ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። ከፍያውን ግዜያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ማመልከቻ ለማስገባት ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሲመጡ፥ በክረዲት ካርድዎ መክፈል ይችላሉ። ክፍያውን እዚያው መክፈል ሳያስፈልግዎት፣ ቆየት ብለው በመክፈያ ወረቅት አማካይነት መክፍልም ይችላሉ። የስደኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የርስዎን ማመልከቻ ማስተናገድ የሚጀምረው ክፍያውን ካጠናነቀቁ በኋላ መሆኑን ያስተውሉ።

እንዴት እንደሚከፍሉና ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ምን ያህል እንደሚከፍሉ ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ማመልከቻ ካስገቡ በኋል፣ ጉዳዩ ውሳኔ እስኪያገኝ በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል ግዜ መጠበቅ እንዳለብዎት የሚገልጽ መረጃ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ድረገጽ ላይ ማንበብ ይችላሉ። ጉዳይዎ መታየት ከጀመረ በኋላ በመሃል ተጭማሪ መረጃ እንዲያቀርቡ የሚጠየቁ ከሆነ፥ የጥበቃ ግዜው ሊራዘም ይችላል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ማመልከቻዎን ተመልክቶ ሲያበቃ ውሳኔውን በፖስታ እርስዎ ወደ ሚኖሩበት አድራሻ ይልካል።

በአሁኑ ሰዓት ማመልከቻ ለማስተናገድ የሚፈጀው ግዜ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ውሳኔው ወደ ሚኖሩበት አድራሻ በፖስታ ይላካል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የማግኘት መብት አለዎት ብሎ ከወሰነ፣ ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርቱን የሚወስዱበት ወቅት ሲቃረብ ውሳኔውን የሚገልጽ መልዕክት በፖስታ ይደርስዎታል። ውሳኔ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ፣ ፓስፖርቱን ለመውሰድ ማመልከቻውን ያስገቡበት የአገልግሎት ማዕከል ድረስ እስኪመጡ 14 ቀናት ያህል ሊወስድ ይችላል።

ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነ

የስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ ጊዜያዊ የውጭ ዜጋ ፓስፖርት ለማግኘት ያቀረቡትን ማመልከቻ ውድቅ ካደረገው ውሳኔውን ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

ይግባኝ የሚሉ ከሆነ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የትኛውን ውሳኔ እንዲለውጥሎት እንደፈለጉ፥ ውሳኔው ምን ላይ ስህተት እንዳለበት በሚገልጽ መልኩ፥ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባት አለብዎት። ደብዳቤው ላይ የእርስዎን ማንነት የሚገልጹ መረጃዎች፥ የጉዳዩ መዝገብ ቁጥር እና የእርስዎ የራስዎ ፊርማ በሚገባ መስፈር ይኖርበታል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔ በሰጥዎት በሶስት ሳምንት ግዜ ውስጥ፥ የይግባኝ ጥያቄዎን ማስገባት እንዳለብዎት ልብ ይበሉ።

ይግባኙን በእርስዎ ፈንታ ሌላ ሰው እንዲያደርግልዎት ከፈለኩ፥ ለግለ-ሰቡ የውክልና ሥልጣን በጽሑፍ መስጠት ይኖርብዎታል።

የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ከተፈቀደሎት፣ ፓስፖርቱን ለመውሰድ ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከመምጣትዎ በፊት የግዜ ቀጠሮ መያዝ ይኖርብዎታል። ፓስፖርት የሚወስደው እያንዳንዱ ሰው ለራሱ የግዜ ቀጠሮ መያዝ አለበት። የልጅዎችዎን ፓስፖርት ለመውሰድ የሚመጡ ከሆነ ለያንንዳንዱ ፓስፖርት የግዜ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል።

ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርትዎን ከሌላ አካባቢ ከሚገኝ የአገልግሎት ማዕከል ዘንድ ሄደው እንዲወስዱ ካልተነገርዎት በቀር፣ ፓስፖርቱን የሚወስዱት ከዚያው መጀመሪያ ማመልከቻዎን ካስገቡበት አገልግሎት ማዕከል ነው። ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርትዎን ከሌላ አካባቢ ከሚገኝ የአገልግሎት ማዕከል ዘንድ ሄደው መውሰድ የሚፈልጉ ከሆነ፣ ፎቶግራፍ ሊነሱና የጣት አሻራ ለመስጠት ወደ አገልግሎት ማዕከል ሲመጡ ይህንኑ ፍላግዎቶን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ሰራተኛ መንገር ይችላሉ።

ፓስፖርትዎን ራስዎ በአካል መጥተው መውሰድ አለብዎት። ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ልጅ ፓስፖርት በተመለከተ ግን፥ አሳዳጊው ወይም ህጋዊ ሞግዚቱ ልጅየውን ሳያስከትል መጥቶ መውሰድ ይችላል።

ከ 15 ዓመት በላይ የሆነ ልጅን በተመለከት፣ አሳዳጊው ወይም ሕጋዊ ሞግዚቱ ማመልከቻውን በሚያስገባበት ግዜ፣ ልጅየው ራሱ ፓስፖርቱን መጥቶ እንደሚወስድ አስታውቆ ማስታውሻ ካስያዘ፣ ልጁ ራሱ በአካል መጥቶ ፓስፖርቱን መውሰድ ይችላል።

ቀነ ቀጠሮ ለመያዝ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

በግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት ስለ መጓዝ

ግዚያዊ የእንግዳ ፓስፖርት የአውሮፓ ሕብረትን መስፈርት የሚያሟላ ነው፣ ስለሆነም በዚህ ፓስፖርት ወደ ሁሉም አገሮች መጓዝ ይቻላል። ይሁን እንጂ ወደ አንዳንድ አገሮች ለመሄድ ቪዛ ሊያስፈልግዎ ይችላል። ስለዚህ ለጉዞ ከመነሳትዎ ቀደም ብለው፥ የዚያን የሚሄዱበትን አገር ኤምበሲ በማነጋገር የበለጠ መረጃ ያግኙ።

የመኖሪያ ፈቃድዎን ያገኙት የጥገኛ ከለላ እንዲሰጥዎ በመጠይቅዎ ምክንያት ከሆነ፣ ወደ ትውልድ ሃገርዎ ወይም አምልጠው ከወጡበት አገር ዘንድ እንዳይጓዙ የሚከለክል መረጃ በግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርቱ ላይ ይሰፍራል።

መታወቂያ ያላሳዩ ወይም ማንነትዎን በተገቢው መንገድ ማራጋገጥ ያልቻሉ ሰው ከሆኑ፣ ይህንኑ የሚገልጽ መረጃ በግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ ይሰፍራል። ይህም ወደ አንዳንድ አገሮች የሚያደርጉት ጉዞ ላይ ችግር ለፈጥርብዎ ይችላል።

ፓስፖርቱ ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ

አብዛኛውን ግዜ፣ ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርት ጸንቶ የሚቆየው ቢበዛ ለሰባት ወራት ነው። ፓስፖርቱ ለአንድ ጉዞ ብቻ ተወስኖ የሚያገለግል ሊሆንም ይችላል ወይም ከስዊድን መውጫና መግቢያ በሁለት አቅጣጫ ብቻ የሚያገለግል ሊሆን ይችላል። ያም ሁነ ይህ፣ ጉዞዎን ካጠናቀቁ በኋላ ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርቱን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማስረከብ ይኖርብዎታል።

ፓስፖርቱ ከጠፋ

ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርትዎ ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቀብዎት፣ መጀመሪያ በአቅራቢያዎ ከሚገኘው ፖሊስ ዘንድ ሄደው ፓስፖርትዎ መጥፋቱን ወይም መሰረቁን ማመልከት ይኖርብዎታል። ሌላ አዲስ ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ከፈለጉ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት አለብዎት። ግዚያዊው የእንግዳ ፓስፖርት ፈልገው አዲስ ማመልከቻ ለማስገባት ሲመጡ ከፖሊስ ጣቢያ የተሰጥዎትን ወይም በቤትዎ አድራሻ የተላከውን የፖሊስ ማመልከቻ ግልባጭ ወይም ኮፒ ይዘው ይምጡ።

Last updated: