የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ

Uppehållstillståndskort – amhariska

የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎ በስውድን ሀገር ውስጥ መኖር እንደሚችሉ ማስረጃ ለመስጠት የመኖሪያ ፈቃድ ካርድም ይሰጥዎታል፡፡ ይህ ካርድ የእርሶን የጣት አሻራ እና ፎቶ የያዘ ኮምፒውተር ችፕ አለው  ወደ መንግስት ቢሮዎች ወይም የሕክምና አገልግሎት ወደሚሰጥበት ማንኛውም ስፍራ ስትሄዱ ይህንን ካርድ ይዛችሁ መሄድ ይኖርባችኋል፡፡

ፎቶ መነሳት እና የጣት አሻራ ስለመስጠት

የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጠው ያለ ማንኛውም ሰው ፎቶ መነሳት ይኖርበታል፡፡ ከስድት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የጣት አሻራ ማስነሳት አይኖርባቸውም፡፡   በአካላዊ ምንክያት የጣት አሻራ መስጠት የማይችል ሰው ማለትም እንደ ቋሚ በሆነ ሁኔታ የጣት አሻራው የጠፋ ሰው  የጣት አሻራው መወሰድ የለበትም፡፡

የጣት አሻራው እና ፎቶግራፋችሁ በካርዱ ቺፕ ላይ የሚቀመጥ ነው እንጂ ወደሌላ ቦታ አይሄድም፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ባወጣችሁ ቁጥር አዲስ ፎቶግራፍ እንድትነሱ እና የጣት አሻራ እንድትሰጡ ይደረጋል፡፡ ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ከሚከፈል ክፍያ ውጪ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለማግኘት የሚከፈል ምንም ዓይነት ክፍያ አይኖርም፡፡

ከስዊድን ውጪ  ከሆኑ

ወደ ስዊድን ለመጓዝ ቪዛ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ በተቻልዎት ፍጥነት አሚገኙበት አገር ያለውን የስዊድን ኤምበሲ ወይም ዋና ቆንስላ ዘንድ በመገኘት፣ ፎቶግራፍ መነሳትና የጣት አሻራ መስጠት ይኖርብዎታል፣ ይህን የሚያደርጉት ፓስፖርትዎን ለኤምበሲው ለማሳየት ቀደም ብሎ በመጡበት ወቅት ፎቶግራፍ ያልተነሱ፣ የጣት አሻራም ያልሰጡ ከሆነ ነው። ቀደም ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ የነበርዎት ቢሆንም እንኳ፥ አሁንም እንደገና ፎቶግራፍ መነሳትና የእጅ አሻራ መስጠት አይቀርልዎትም። ምክንያቱም የበፊቱ ፎቶግራፍዎ ሆነ የጣት አሻራዎን ማስቀመጫ ቋት ውስጥ ስለማናቆየው፣ ከእኛ ጋር የለም።

ሁሉም ኤምባሲዎቻችንና የቆንስላ ጽ/ቤቶቻችን የፎቶ ማንስት ሆነ የጣት አሻራ መውሰድ አገልግሎት ይሰጣሉ ማለት አይደለም፣ ይህን ዓይንት አገልግሎት የማይሰጡም ስላሉ ወደ ኤምበሲያችን ወይም የቆንስላ ጽ/ቤቶቻችን ዘንድ ለመሄድ ከመነሳትዎ በፊት ስለዚሁ ጉዳይ ያለውን መረጃ የኤምበሲዎቹን ወይም ቆንስላዎቹን ድረ ገጾች ያንብቡ።

ዜጎቻቸው ወደ ስዊድን ለመግባት ቪዛ የሚያስፈልጋቸው ሀገራት (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

አቅራቢያችሁ የሚገኘው የስዊድን ኤምባሲ ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት ቤት የቱ እንደሆነ በዚህ ድረ ገጽ ላይ ፈልጉ Swedenabroad.se (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window. 

ወደ ስዊድን ሀገር ለመጓዝ ቪዛ የማያሰፈልጋችሁ ከሆነ በስዊድን ሀገር ውስጥ ፎቶ እና አሻራ ይሰጣሉ፡፡ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳገኛችሁ እና ስዊድን እንደደረሳችሁ በተቻለ ፍጥነት የስደተኞች ኤጀንሲ ዘንድ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

በስዊድን ሀገር ውስጥ የሚትገኙ ከሆነ

ስዊድን ውስጥ ፈቃድዎን ማራዘም ከፈለጉ ወይም አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ማውጣት ከፈለጉ ፎቶግራፍ ለመነሳትና የእጅ አሻራዎን ለመስጠት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤትን (Migrationsverket) መጎብኘት ይኖርብዎታል። ይህን የሚያደርጉት፣ ቀደም ብሎ ፓስፖርትዎን እንዲያሳዩ በተጠየቁበት ግዜ ሲመጡ ፎቶግራፍ ያልተነሱ፣ የጣት አሻራም ያልሰጡ ከሆነ ነው።

ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ሲመጡ ፓስፖርትዎን መያዝ አለብዎት። የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎ ተሰርቶ ሲያበቃ ስዊድን ውስጥ ያለው የመኖሪያ አድራሻዎ ድረስ ይላክልዎታል። ስለዚህ ፎቶግራፍ ለመነሳትና የጣት አሻራ ለመስጠት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ዘንድ ሲመጡ እግረ መንገድዎን ስዊድን ውስጥ የሚኖሩበትን አድራሻ መንገር አስፈላጊ ነው።

ፎቶ እና አሻራ ለመስጠት ከስደተኞች ኤጄንስ ቢሮ ጋር ቀጠሮ ይያዙ፡፡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

እኛን የት ታገኙናላችሁ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

አድራሻችሁን ከለወጣችሁ

የመኖሪያ ካርዳችሁ መኖሪያ ቤታችሁ ድረስ እንዲንልክላችሁ ከፈለጋችሁ አድራሻችሁ እንፈልጋለን የአድራሻ ለውጥ ያደረጋችሁ እንደሆነ አዲሱን አድራሻችሁን ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ ስትመጡ ማሳወቅ ትችላላችሁ፡፡ ከሌላ ሰው ጋር የሚትኖሩ ከሆነ እና የጋራ አድራሻውን ለኛ መንገሩን አይርሱ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ዝግጁ ሲሆን

ፎቶ የተነሳችሁትን እና አሻራ የሰጣችሁት በኤምባኢ ወይም በቆንጽላ ጽሕፍት ቤት ውስጥ ከሆነ ካርዱን የምትቀበሉት ከእነርሱ ዘንድ ይሆናል፡፡ ኢንባስውን ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት የሚልክላችሁ ከሆነ ወይም እናንተ መምታት ካለባችሁ ጠይቋቸው፡፡ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጣችሁ ከተወሰነ በኋላ ካርዱን ለማዘጋጀት እና ወደ ኤምባሲው ወይም ቆንጽላ ጽሕፈት ቤቱ ለመላክ እስከ አራት ሳምንታት ሊፈጅ ይችላል፡፡

ፎቶግራፍ የተነሳችሁት እና አሻራ የሰጣችሁት በሚግራሾንስቨርከት ቢሮ ከሆነ፥ በአንና ወይ በሁለት ሳምንት ውስጥ፡ ካርዳችሁ ወደ መኖሪያ ቤታችሁ አድራሻ ይላክላችኋል።

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ፣ ውሳኔ ከመተላለፉ ጋር ተያይዞ ይሰራል፣ ይሁን እንጂ ፈጠነ ቢባል፣ ውሳኔው ከሚጸናበት ዕለት አንስቶ ከስድስት ሳምንታት በፊት አይደርስም።

ካርዱን ማዘጋጀትም ሆነ ማድረሱን ከዚህ በላይ ማፍጠን አይቻልም፡፡

Uppehållstillståndskort.

በካርዱ ላይ የሚገኙ መረጃዎች

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ እነዚህን መረጃዎች በውስጡ ይይዛል፡ ምን ዓይነት ፈቃድ እንዳላችሁ እና ካርዱ ለምን ያኽል ጊዜ ሕጋዊ እንደሆነ እና ሌሎች ነገሮችንም ይይዛል፡፡ የግል ማስረጃችሁም በዚህ ካርድ ውስጥ ተካቷል፡፡ በአንዳንድ ካርዶች ጃርባ ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ይገባል “ለመስራት የተፈቀደለት” (“Får arbeta”)፡፡  ይህ ማለት የተቀበሉት ውሳኔ በቀጥታ ለስራት መብት እንዳለዎ የማያመለክት ከሆነ ማለትም ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ የተሰጦ ከሆነ፡፡ ይሁን እንጂ ስዊድን ውስጥ የሥራ ፈቃድ የተሰጣችሁ ከሆነ ውሳኔው ሥራ የመስራት ፈቃድ አላችሁ ይላል ስለዚህ ስለዚህም ካርዶ ጀርባ ላይ “ለመስራት የተፈቀደለት” ተብሎ ሊጻፍበት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ለልጆች ጽኁፉ ይካተታል (በአስፈላጊው ቦታ) እድሜቸው 16 ከሆነ ጀምሮ፡፡

በካርዳችሁ ላይ ያለውን መረጃ ተመልከቱ

ሁልጊዜ በመኖሪያ ፈቃድ ካርድህ ላይ ያለው ስምና በፓስፖርትህ ላይ ያለው ስም አንድ መሆኑን አረጋግጥ፡፡ ካርድህ የተሳሳተ ስም ካለው ወደ ስደተኛ ኤጀንሲ ወይም ኤምባሲ አዲስ ካርድ ለማግኘት ሂድ፡፡  ፓስፖርትህን ይዘህ ሂድ፡፡

ስምህን የለወጥህ እንደሆነ አዲሱ ስምህን ለማስመዝገብ በመጀመሪያ ወደ ታክስ ኤጀንሲ በመሄድ የሕዝብ መመዝገቢያ መሄድ ይኖርብሃል፡፡  ከዚያም አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለማግኘት ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ መሄድ ይኖርብሃል፡፡ 

ለመጓዝ በምትሄዱበት ጊዜ

በሚጓዙበት ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዱን ከፓስፖርትዎ ጋር ማሳየት አለብዎት። በፓስፖርት እና የመኖሪያ ፍቃድ ካርድዎ፥ ”በሼንገን አካባቢ” (Schengenområdet) ለ90 ቀናት፥ በ180 ቀናት ውስጥ ባለው ጊዜ፥ መግባት እና በነፃነት መንቀሳቀስ ይችላሉ። ወደ ”በሼንገን” (Schengen) ያልሆነ ሀገር የሚጓዙ ከሆነ፥ ቪዛ ማግኘት ሊያስፈልግዎ ይችላል።

የመኖሪያ ፈቃድ ካርዱ፡ እንደ መታወቂያ ሰነድ ወይም የጉዞ ሰነድ (ፓስፖርት) መጠቀም አይቻልም።

ካርዱ ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳልዎት የሚያሳየው ካርድዎ ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ ሶስት ዓመት ነው። ይሁን እንጂ ፈቃድ የተሰጥዎት እንደ አንድ በአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት ውስጥ በነዋሪነት የሚቀመጥ ሰው ከሆነ፣ የመኖሪያ ፍቃድ ካርድዎ ጽንቶ የሚቆይበት ግዜ አምስት ዓመት ይሆናል። የአምስት ዓመት ጽናት ግዜዉ 1 ጃንዋሪ 2022 በፊት የወጡ የመኖሪያ ፈቃድ ካርዶችን ጭምር ይመለከታል።

አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ሲያወጡ ወይም ነባሩን ባራዘሙ ቁጥር አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ይሰጥዎታል። አንድ አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ሲያስፈልግዎት እንደገና ፎቶግራፍ ይነሳሉ እንዲሁም የጣት አሻራ ይሰጣሉ። ሁል ግዜ አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ ካርድ ለመውሰድ ወደ ሚግራሾንስቫርኬት ሲመጡ አሮጌውን ካርድ ይዘው ይምጡ።

ካርድህ ከጠፋ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድህ ቢጠፋብህ ወይም ቢሰረቅብህ በመጀመሪያ ለፖሊስ ማመልከት አለብህ፡፡ ከዚያም ለአዲስ ካርድ ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ቢሮ በመሄድ ፎቶግራፍ መነሳት እና አሻራ መስጠት ይኖርብሃል፡፡  ሪፖርት ባደረግክበት ወቅት ወይም ከዚያ በኋላ ከፖሊስ የተቀበልከውን የሪፖርት ቅጂ ይዘህ ሂድ፡፡

ካርዶን ያልተቀበሉ ከሆነ

የመኖሪያ ፈቃድ ካርድዎን ለመውሰድ ለረጅም ጊዜ እየጠበቁ ነው? ምክንያቱ ካርዱ ወደ ስደተኞች ኤጀንሲ ተመላሽ ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የስደተኞች ኤጀንሲ ስህተት የሆነ የእርሶ አድራሻ ይዞ ሊሆን ይችላል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄ ካለዎ የስደተኞች ኤጀንሲ ዘንድ በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: