ከለላ የሚፈልጉ ልጆች

Barn i asylprocessen – amhariska

የጥገኝነት ጥያቄው በሚካሄድበት ጊዜ የልጆች መብቶች ከአዋቂዎች መብቶች የተለዩ ናቸው። በዚህ ቦታ ላይ ከጥገኝነት ማመልከቻቸው እና ከተግባራዊ ሕይወታቸው ጋር በሚያያዝ መልኩ  ስለ ልጆች መብቶች፣ እና የእርዳታ ዕድሎች መረጃዎችን ሰብስበናል።

ስዊድን በልጅ መብቶች ላይ የተባበሩት መንግስታት/ UN ስምምነትን ፈርማለች። ይህ ስምምነት የሁሉንም ልጆች መብቶች ይገልጻል። እነዚህ መብቶች በስዊድን ለሚኖሩ ልጆች በሙሉ፣ የስዊድን ዜጎች ይሁኑ ወይም አይሁኑ፣ በጊዜያዊነት እዚህ ቢኖሩም፣ ወይም ጥገኝነት የሚፈልጉ ቢሆንም እነዚህ መብቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ። 

በስዊድን ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ሁሉ ልጅ ተደርጎ ይቆጠራል። ብዙውን ጊዜ የጥገኝነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ልጆች የሚመጡት ከአንዱ ወይም ከሁለቱም ወላጆቻቸው ጋር በመሆን ነው። ያለ ወላጅ ወይም አሳዳጊ እዚህ ስዊድን የሚደርሱ በርካታ ልጆች አሉ፤ እነዚህ አዋቂ ሰው አብሮአቸው የሌላቸው ልጆች የተለየ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ሰው አብሮአቸው የሌላቸው ልጆች ሊኖራቸው ስለሚገባው መብት ተጨማሪ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ጥገኝነት የሚፈልጉ ልጆች ድምጻቸውን የማሰማት መብት አላቸው

በስዊድን ሕግ መሰረት የስደተኞች ኤጄንሲ በተለየ ሁኔታ የልጅን ምርጥ ፍላጎት መቀበል አለበት። ሁሉም ልጆች ድምጻቸውን የማሰማት እና የመደመጥ መብት አላቸው።  ልጆች ጥገኝነት የፈለጉት ከወላጆች በተለዩ ምክንያቶች ሊሆን ስለሚችል፣ ጥገኝነት የፈለጉትበት ምክንያቶች በግል መታየት አለባቸው። ልጁ ጥገኝነት የፈለገባቸው ምክንያቶች በሚታዩበት ጊዜ፣ የስደተኞች ቦርድ ባለሥልጣን ምርመራውን በተቻለ መጠን የልጁን ዕድሜ፣ ጤና እና ብስለትን ባማከለ መልኩ ማደረግ አለበት።   ልጁ ምርመራው በሚደረግበት ጊዜ ከአዋቂ ሰው ጋር ሆኖ የመቅረብ መብት አለው። ወላጅ ወይም ሌላ ሕጋዊ አሳዳጊ፣ ሞግዚት፣ እና/ወይም የሕዝብ አማካሪ ሊሆን ይችላል።

ሁሉም ልጆች በትምህርት ቤት እና በቅድመ ትምህርት ቤት የመሳተፍ መብት አላቸው

ሁሉም ልጆች እና ወጣት አዋቂዎች እንደ ሌሎች በስዊድን እንደሚኖሩ ልጆች ትምህርት ቤት እና ቅድመ ትምህርት ቤት ለመሄድ እኩል መብት አላቸው።  በከተማው ውስጥ እንደሚኖሩ  እንደማንኛውም ልጆች እና ወጣት አዋቂዎች ትምህርት ቤት መሄድ እንዲችሉ ለማድረግ ልጁ የሚኖርበት ከተማ ኃላፊነት አለበት።  ይህ ቅድመ ትምህርት ቤት፣ መካከለኛ አንደኛ ደረጃ፣ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንም ይመለከታል። ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሄድ እንዲችሉ ጥገኝነት የሚፈልጉ ወጣት አዋቂዎች 18 ዓመት ሳይሞላቸው  ትምህርታቸውን መጀመር አለባቸው።

የስደተኞች ኤጄንሲ ያለ ወላጅ ስምምነት ጥገኝነት ስለሚጠይቁ ልጆች መረጃን ለከተማው  አስተዳደር መስጠት አይፈቀድለትም። ለስደተኞች ኤጄንሲ፣ ለልጅዎት ስም፣የልደት ሴርተፊኬት፣ ቋንቋ፣ የትውልድ አገር፣ እና የጉዳዩን ቁጥር ሕጋዊነት የሚሰጠው ጋር ስምምነትዎን መስጠት ይችላሉ። የከተማዋን አስተዳደር ማግኘት እና ልጆችዎ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ቅድመ ትምርህት ቤት እንዲሄድ እንደሚፈልጉ ማሳወቅ ይችላሉ።

ስለ ትምህርት ቤት ይበልጥ ያንብቡ

ሁሉም ልጆች የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው

ጥገኝነት የሚፈልጉ ልጆች ልክ እንደ ማንኛውም በስዊድን ውስጥ እንደሚኖሩ ልጆች የጤና እንክብካቤ እና የጥርስ እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው። የጥርስ ህክምና ከ18 ዓመት በታች ላሉት ያለ ክፍያ ይሰጣል። በበርካታ የቆጠራ ጉባኤዎች እና ክልሎች፣ ለልጆች የጤና እንክብካቤ በነጻ ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ በሚኖሩበት አከባቢ የሚገኘውን የቆጠራ ጉባኤ ወይም ክልል ያግኙ።

ስለ ጤና እክብካቤ በእርስዎ ካውንቲ ምክር ቤት ወይም ክልል በ www.1177.se ላይ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

ስለጥገኝነት ፈላጊዎች የጤና እና የህክምና እንክብካቤ የበለጠ ያንብቡ።

ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልሶ የመገናኘት መብት አላቸው

 ስለ ልጅ መብቶች በሚደነግገው የተባበሩት መንግስታት/ UN ስምምነት መሰረት፣ ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የመሆን መብት አላቸው።  የስዊድን ባለሥልጣትናት ወላጆች ብቻቸውን ከሚኖሩ ከጥቂቶቹ ጋር ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች አብሮአቸው ለማስቀመጥ ሙከራ የሚያደርገውም ለዚሁ ነው። የስደተኞች ኤጄንሲ የልጁን የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከቻ በሚመረምርበት ጊዜ ዘመዶችን ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት ይቀጥላል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ዓላማው ከወላጆቻቸው ጋር በትውልድ አገራቸው መልሶ እንዲገናኙ  ለማድረግ ነው። የልጁ ዘመዶች በሌሎች አገሮች ደኅንነቱ አስተማማኝ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኙ ከሆነ ልጆቹ መልሶ እዚያው እንዲያገኙዋቸው  ማድረግ ይችላል። በየትም ቦታ መልሶ የማገናኘቱ ሌሎች አማራጮች ከሌሉ፣ ልጁ በስዊድን የጥገኝነት የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጠው የልጁ ቤተሰብ በስዊድን ውስጥ እንዲኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጣቸዋል።

ልጁ የመኖሪያ ፈቃድ ካላገኘ እና መመለስ ካለበት ምን ሊሆን እንደሚችል የበለጠ ያንብቡ።

ስለ ልጁ መብቶች ተጨማሪ

ሁሉም የስዊድን ባለሥልጣናት ውሳኔዎችን በሚያስተላልፉበት ጊዜ የልጁን ፍላጎቶች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን፣ የልጆችን መብቶች ለመከላከል ልዩ ተልዕኮ የተሰጣቸው በርካታ ሌሎች ባለሥልጣናት አሉ።  ወላጆቹ እንክብካቤ ማድረግ ከተሳናቸው ወይም ወላጁቹ ልጁን የሚጎዱት ከሆነ፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ልጁ የሚኖርበት የከተማ አስተዳደር ለልጁ እንክብካቤ ለመስጠት ኃላፊነት አለበት። አንዳንድ ጊዜ ፖሊስ ልጁን ጥቃት ከሚደርስበት ስፍራ ወስዶ ደኅንነቱ ወደተጠበቀ የእንክብካቤ መስጫ ቦታለመውሰድ አገዛ ሊፈልግ ይችላል። ልጅን መምታት፣ ወይም ሴት ልጅን መግረዝ፣ ለምሳሌ አይፈቀድም። ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልቾች ጋብቻ እንዲፈፅሙ አይፈቀድም።

የበለጠ መረጃ

ስቃይ ለደረሰባቸው ልጆች ወይም በሌላ መንገድ ደካማ የሆነ አቋም ለሚያሳዩ ልጆች ሊሰጡ ስለሚችሉ ድጋፎች ተጨማሪ ያንብቡ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

ስለልጅ መብቶች ስምምነት ተጨማሪ ያንበቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

ስዊድን ስለደረሱ እና የጥገኝነት ማመልከቻ ስላቀረቡት ልጆች መረጃ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ስለ ጥገኝነት ጥያቄ እና  ለጥገኝነት ጥያቄ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በይበልጥ ለማወቅ፣ ወይም ለአዋቂዎች የልጆች የጥገኝነት ሂደቱን በማብራራት ለማገዝ እነዚህ ገጾች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

ስዊድን ከሚኖር ሰው ልጅ ወይም ፅንስ ላላቸው ጥገኝነት ፈላጊዎች መረጃ።

Last updated: