ለጥገኝነት ፈላጊዎች የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ

Ekonomiskt stöd för asylsökande – amhariska

ራስን መደገፍ መቻል አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሰራ ሰርተህ ገንዘብ እያገኘ ካሆነ ወይም ሌላ ምንም ዓይነት ምንጭ ከሌለህ ለስደተኞች ቦርድ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግልህ ማመልከት ትችላለህ፡፡ የገንዘብ ድጋፉ ብዙ ክፍሎች አሉት፡- የዕለት ወጪ ድጎማ፣ የቆይታ ወጪ እና ልዩ አበል፡፡

ጥገኝነት ስትፈልግ ለስደተኞች ቦርድ ምን ያህል ገንዘብ ወይም ሌላ ሀብት እንዳለህ መናገር ይኖርብሃል፡፡ የራስህ የሆነ ምንም ዓይነት ሀብት ከሌለህ የዕለት ወጪዎችህን ለመሸፈኛ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ይደረግልሃል፡፡

የገንዘብ ገቢህ ሁኔታ ቢቀየር - ለምሳሌ ስራ ብታገኝ ለስደተኞች ቦርድ መናገር ይኖርብሃል፡፡ የራስህን ገቢ ማግኘት ጀምረህ የዕለት ወጪህን መሸፈኛ ደግሞ የምትቀበል ከሆነ ድርጊቱ የወንጀል ድርጊት ይሆናል፡፡ ዕለታዊ አበልዎ በአድራሻ መቀየር ምክንያት ሊለወጥ ይችላል። ስለዚህ ሁሌ አድራሻ ሲቀይሩ አዲሱን አድራሻዎ ለስደተኛ ጽ/ቤት ያሳውቁ።

ውሳኔ በመጠበቅ ላይ ሳለህ ስራ ብታገኝ ማድረግ የሚገባህን ለማወቅ የበለጠ አንብብ፡፡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የቀን አበል

የቀን አበል መጠን እንደየ ሚኖሩበት ሁኔታ የተለያየ ነው፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በሚያዘጋጀው፥ የምግብ ወጪ በሚታሰብበትና የምግብ ወጪ በማይታሰብበት ቦታ ሲኖሩ መጠኑ ይለያያል ማለት ነው። የቀን አበልን መጠን የሚነካው ሌላው ሁኔታ ደግሞ፥ በግልዎ የመኖሪያ ቦታዎን ለማዘጋጀት የመረጡ ከሆነ ነው፥ ማለትም በወዳጅ ዘመድ ቤት ውስጥ ተጠግተው መኖር ከፈለጉ የአበሉን መጠን ይነካዋል።

መኖሪያ ከምግብ ጋር የሚሰጥበት የዕለት ወጪ ድጋፍ፡-

  • 24 ክሮ/ለብቻቸው ለሚኖሩ ጎልማሶች
  • 19 ክሮ/የቤት ወጪያቸውን ለሚጋሩ ጎልማሶች ለየግላቸው
  • 12 ክሮ/17 እና ከዚያ በታች ዕድሜ ላላቸው ህጻናት

ምግብ አብሮ ከመኖሪያ ጋር የማይሰጥበት የዕለት ወጪ

  • 71 ክሮ/ለብቻቸው ለሚኖሩ ጎልማሶች
  • 61 ክሮ/የቤት ወጪያቸውን ለሚጋሩ ጎልማሶች ለየግላቸው
  • 37 ክሮ/ከ 0–3 ዓመት ለሆኑ ህጻናት
  • 43 ክሮ/ከ 4–10 ዓመት ለሆኑ ህጻናት
  • 50 ክሮ/ከ 11–17 ዓመት ለሆኑ ህጻናት

ከሁለት ልጆች በላይ ያላቸው ቤተሰቦች ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ልጆች የየዕለቱን የወጪ ድጋፍ የሚያገኙ ሲሆን ለተቀሩት ልጆች ደግሞ የየዕለቱን የወጪ ሽፋን ግማሹን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

ከምግብ ውጪ የዕለት ወጪው ድጋፍ ለልብስ፣ ለጫማ፣ ለጤና ክብካቤ እና መድሃኒት፣ የጥርስ ክብካቤ፣ የመጸዳጃ ቤት ግብዓቶች፣ ሌላ ሸቀጣ ሸቀቶች እና ለመዝናኛ የሚሆኑ ወጪዎችን የሚሸፍን መቻል አለበት፡፡

የዕለት ወጪው የሚከተሉትን ከሆናችሁ ሊቀነስ ይችላል

  • ማንነተህን ለመግለጽ ፈቃደኛ የማትሆን ከሆነ
  • ራስን በመሰወር ለጥገኝነት የሚደረገውን ምርመራ የምታጓትት ከሆነ
  • ማመልከቻህ ተቀባይነት ካላገኘ ወይንም ወደ ሀገርህ እንድትመለስ ተወስኖ አንተን ለመመለስ በሚደረገው ስራ ላይ የማትተባበር ከሆነ

የመኖሪያ ሰፈርዎን፥ የማህበረ ኤኮኖሚ ተግዳሮት አለባቸው ወደ ሚባሉ አካባቢዎች የሚቀይሩ ከሆነ፥ የቀን አበል የማግኘት መብትዎን ሊነፈጉ ይችላሉ። የቀን አበል እና ልዩ ድጎማ የማግኘት መብትዎን ሊያሳጣዎት የሚችለው ሌላ ምክንያት ደግሞ የሚኖሩበትን ትክክለኛ አድራሻ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያላሳወቁ ከሆነ ነው። ለምሳሌ የፖስታ ሳጥን ቁጥር አድራሻ መስጠት።

በግልዎ በሚያዘጋጁት መኖሪያ ስለመቀመጥ እና ቤት የሚቀዩሩበት ሰፈር አድራሻ የቀን አበል የሚነካ መሆኑንና አለመሆኑን እዚህ ይፈትሹ

የቀን አበል መጠየቂያ ቅጽ (Mot23) (በስዊድሽኛ ቋንቋ) Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

የአበል ቅጹን በሚከተለው መልክ መሙላት ይችላሉ፣

የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስገኘው መብት ይነሳል

የመኖሪያ ፈቃድዎን በሚያገኙበት ወቅት የኢኮኖሚ ድጋፍ የሚያስገኝልዎትን መብት ያጣሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በሚያዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራ እያሉ አንድ ኮምዩን ሲቀበልዎት፤ እንደ ደንቡ ከሆነ ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ሲሰጥዎት የነበረውን ድጎማ አያገኙም። በግልዎ ባዘጋጁት መኖሪያ ቦታ የሚቀመጡ ከሆነ፥ የመኖሪያ ፈቃድዎን ካገኙ ከአንድ ወር በኋላ ድጎማ የማግኘት መብትዎ ይነሳል።

ከዚህ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ ሊነሳ የሚችለው፣ ማመልከቻዎ ውድቅ ሆኖ አገር ለቅቀው እንዲሄዱ ተወስኖ ወይም ከአገር እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላልፎ፥ ውሳኔው የሚጸናበት ግዜ ሲጀምር ወይም በራስዎ ፈቃድ ከአገር እንዲወጡ ታዝዘው የተሰጥዎት የግዜ ገደብ ሲያበቃ ነው። ይህ ደንብ የሚመለከተው ከ18 ዓመት በታች የሆነ፥ በአሳዳጊነት ወይም በሞግዚትነት አብሮ የሚኖር ልጅ የሌላቸውን አዋቂዎች ነው። የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብትዎ አገሪቱን ለቅቀው ሲወጡም ይነሳል።

ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች በስዊድን የስደት ኤጄንሲ (Migration Agency) ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊቆዩ እና ስዊድንን ለቀው እስከሚወጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እስኪወጡ ድረስ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብታቸውን ሊያጠብቁ ይችላሉ። በእምቢታው ላይ ያለው ውሳኔ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ለሥራ ፈቃድ የሚያመለክቱ ከሆነ፣ ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እንዲወጡ ይደረጋሉ እናም ከዚያ በኋላ የገንዘብ ድጋፍ ወይም መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት አይኖርዎትም። ከእርስዎ ጋር አብረው ለመኖሪያ ፈቃድ ለሚያመለክቱ የቤተሰብዎ አባላትም ተመሳሳይ ነው።

ልዩ አበል

በዕለት ወጪ ድጋፍ ሊሸፈን ያልቻለ ከፍተኛ ፍላጎት ካለህ ልዩ አበል እንዲሰጥህ ማመልከት ትችላለህ፡፡  ስለፈለከው ዕቃ ወይንም የአገልግሎት ዓይነት ያደረብህን ፍላጎት ማረጋገጥ የሚኖርብህ ሲሆን መክፈል አለመቻልህንም ማስረዳት አለብህ፡፡ ለምሳሌ መነጽር፣ ህጻን ማቀፊያ ወይን የሚሞቅ የክረምት ጫማ፡፡ የስደተኞች ቦርድ ለፍላጎትህ የግል ምዘና ያደርጋል፡፡

ፍላጎትህን ለማሟላት ከሚሆንህ ዕቃ ውስጥ ልታገኘው የምትችለው በዋጋው ርካሽ የሆነውን ብቻ ነው፡፡

ልዩ ድጎማ የማግኘት መብትዎ የሚነካበት አንዱ አጋጣሚ፥ በግልዎ ፈልገው የሚቀይሩበት መኖሪያ ቤት የማህበር ኢኮኖሚ ተግዳሮት እንዳለባቸው ያመለከቱ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኝ ከሆነ ነው።

ወደ ስደተኞች ቦርድ እንድትመጣ ስትፈለግ ለምሳሌ - ስለ ጥገኝነት ጥያቄህ ለማጣራት፣ ከተቀበለህ የአስተዳደር ሰራተኛ ጋር ለመገናኘት ወይንም በቡድን በሚካሄዱ ኩነቶች ላይ እንድትሳተፍ ሲፈለግ የጉዞ አበል የምታገኝ ይሆናል፡፡ ከምታገኘውን የአስተዳደር ሰራተኛ  ጋር ስለዚህ ጉዳይ ተነጋገር፡፡

ለጎልማሶች የሚሆን የማመልከቻ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር  Mot78 Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

ጎልማሶች ለልዩ አበል ቅጽ የሚሞሉት እንደዚህ ነው (በእንግሊዝኛ)

በዕድሜያቸው ገና የሆኑ ሰዎች የሚሆን የማመልከቻ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር Mot79 Pdf, 654.3 kB, opens in new window.

በዕድሜያቸው ገና የሆኑ ሰዎች ለልዩ አበል ቅጽ የሚሞሉት እንደዚህ ነው (በእንግሊዝኛ)

ከጎናቸው ማም ለሌለ ህጻናት እና ወጣቶች የሚሆን የማመልከቻ ቅጽ፣ የቅጽ ቁጥር Mot72 Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

የመኖሪያ ቤት ወጪ ድጋፍ

ስራ ካገኘህ ወይንም ስራ የሚሰጥህ ሰው ካገኘህ ለመኖሪያ ቤት ወጪ ማመልከት ትችላለህ፡፡ ይህ ማለት ያገኘኸው ስራ ከሶስት ወር የቅጥር ጊዜ የሚበልጥ ከሆነ እና የምትሄድበት ቦታ ላይ የስደተኞች ቦርድ ሊሰጥህ የሚችለው መኖሪያ ቤት ከሌለ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤት ወጪ ድጋፍ -

  • 850 ክሮ/ለቤተሰዎች በወር
  • 350 ክሮ/ለአንድ ሰው በወር

ስለ ገንዘብ ድጋፍ ያለ ውሳኔ

የስደተኞች ቦርድ ስለ ገንዘብ ድጋፍ ውሳኔ ሲሰጥ ስለ ውሳኔው እናሳውቅሃለን፡፡

  • በተቀበለህ የአስተዳደር ሰራተኛ በኩል
  • በተለምዶ ቀላል ማሳወቂያ በሚባለው በኩል

ቀላል ማስታወቂያ ማለት የስዊድን የፍልሰት ቦርድ የውሳኔ ማስታወቂያዎችን እርሶ በሰጡት አድራሻ መሰረት በፖስታ ሲልክሎት ማለት ነው፡፡ በሚቀጥለው ቀን ውሳኔ እንደተላለፈ የሚገልጥ ደብዳቤ በዛው አድራሻ ላይ ድጋሚ እንልካለን፡፡ ይህንን የምናደርገው ስህተቶችን ለመቀነስ ሲባል ነው፡፡ በዚህ መንገድ የፍልሰት ቦርዱ የውሳኔውን ማስታወቂያ ማስታወቂው ከተላከ ከሁለት ሳምንት በኃላ እንዳገኙት ያስባል (መረጃ ደርሶታል)፡፡ ከዚያ በኃለ ይግባኝ ለማለት ሶስት ሳምንት አለዎት፡፡

የሰጡንን አድራሻ ልንጠቀምበት ካልቻልን እና ስዊድን ውስጥ የተመዘገቡ ከሆነ የውሳኔውን ደብደቤ እና የቁጥጥር ደብዳቤውን መጀመሪያ ተመዝግበው ወደነበረበት አድራሻ እንልካለን፡፡

በተጨማሪም የፖስታ ሳጥኖን ሁል ጊዜ ማየቱን አይርሱ፡፡

የባንክ ካርድ

ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የቀን አበል እንዲያገኙ ከተፈቀደልዎት፥ ገንዘቡ ከሚቀመጥበት የባንክ ሂሳብ ጋር የተገናኘ አንድ የባንክ ካርድ ይሰጥዎታል።

ለራስዎ የ”ቀን-ድጎማ” (dagersättning) ለመጠቀም፥ የራስዎ የሆነ “የባንክ-ካርድ” (bankkort) እንዲኖሮት መብት ኣልዎት፥ በቤተሰባችሁ ውስጥ ብዙ ኣዋቂዎች የምትኖሩ ቢሆንም።

ስለ ጥገኝነት-ጠያቂዎች የባንክ-ካርድ እዚህ በይበልጥ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ይግባኝ መጠየቅ ከፈለግህ

ያንተን የወጪ ድጋፍ በተመለከተ የስደተኞች ቦርድ ስህተት ሰርቷል ብለህ ካሰብክ ውሳኔውን አስመልክቶ ይግባኝ መጠየቅ ትችላለህ፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉዳይ ሲገጥምህ የይግባኝ ጥያቄህን ውሳኔውን ከሰማህ (ካሳወቁህ) በኋላ ባሉ የሶስት ሳምንት ጊዜያት ውስጥ ወደ ስደተኞች ቦርድ ይዘህ መቅረብ ይኖርብሃል፡፡ የስደተኞች ቦርድ የይግባኝ ጥያቄህን ተመልክቶ ውሳኔውን ካልቀየረ የይግባኝ ጥያቄህ ጉዳይህን በድጋሚ ሊመለከት ወደሚችል የህግ የፍርድ ቤት አስተዳደር ያስተላልፈዋል፡፡ የህግ የፍርድ ቤት አስተዳደር የይግባኝ ጥያቄህን ውድቅ ካደረገው ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት (kammarrätten) ማመልከት ትችላለህ፡፡

የይግባኝ ጥያቄ የምታቀርብ ከሆነ ማድረግ ስላለብህ ነገሮች በደንብ አንብብ

ስለ ዕለት ወጪህ ድጋፍ ወይም ሌሎች አበሎችን በተመለከተ ጥያቄ ካለህ

ለጥገኝነት ፈላጊዎች የሚደረገውን የገንዘብ ድጋፍ በተመለከተ አጠቃላይ ጥያቄ ካለህ ወደ ስደተኞች ቦርድ መደወል ትችላለህ፡፡ ጥያቄህ ግን የራስህን የወጪ ድጋፍ በተመለከተ ከሆነ ወደ ተቋሙ መምጣት ይኖርብሃል፡፡ የስደተኞች ቦርድ ሰራተኞች ስለ ህጎቹ ሚስጥራዊነት ሲባል ይሄንን በስልክ ማውራት አይችሉም፡፡ ወደ ተቋሙ ስትሄድ የ LMA ካርድህን ይዘህ ሂድ፡፡

Last updated: