መኖሪያ ቦታ

Boende – amhariska

የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብታችሁ መልስ እስኪመጣላችሁ በምትጠብቁበት ወቅት የመኖሪያ ቦታ ችግር ያለባችሁን ሰዎች፥ የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ሊረዳችሁ ይችላል። ራሳችሁ በግላችሁ ጥረት የመኖሪያ ቤት ማዘጋጀት ትችላላችሁ፥ ለምሳሌ ወዳጅ ዘመድ ጋር በመጥጋት። በዚህ መልክ የራሳችሁን መኖሪያ ቤት ካዘጋጃችሁ፥ ጽ/ ቤቱ ሲፈልጋችሁ ሊያገኛችሁ እንዲችል፥ ያላችሁበትን አድራሻ ለስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ማሳወቅ አለባችሁ።

የስደተኞች ””ጉዳይ ጽ/ ቤት”” ዘንድ መቀመጥ

የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት”፥ እናንተ ውሳኔ በምትጠብቁበት ግዜ ውስጥ፥ የምትቀመጡበት ግዜያዊ መኖሪያ ቤት ያቀርባል። ለመኖሪያው የሚሆን ገንዘብ ከሌላችሁ፥ የመኖሪያ ወጪውን የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ይከፍላል።

አገር ውስጥ መቀመጥ አትችሉም ወይም አገር ለቃችሁ እንድትወጡ የሚል ውሳኔ ከደረሳችሁ እና ውሳኔ በሥራ ላይ መዋል ከጀመረ፥ ወይም በራሳችሁ ፈቃድ አገር ለቅቃችሁ የምትወጡበት ቀን ካለፈ፤ የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” እንድትቀመጡበት የሰጣችሁ ቤት ውስጥ የመቆየት መብት አይኖራችሁም። ይህ በሞግዚታዊ ሃላፊነት የምታሳድገው ከ18 ዓመት በታች የሆነ፥ አብሮ የሚኖር ልጅ የሌለውን አዋቂ ሰው የሚመለከት ነው።

ልጆች ያሏችሁ ቤተሰቦች፣ ስዊድን ውስጥ ለመኖር የጠየቃችሁት ጥያቄ ውድቅ ከሆነባችሁ ወይም አገር ለቅቃችሁ እንድትወጡ ከተወሰነባችሁ በኋላ፥ የመኖሪያ ሥፍራ የማግኘት መብታችሁ የተጠበቀ ነው። ይሁን እንጂ መኖሪያችሁን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ወደ አዘጋጀው “የተመላሽ ማቆያ ማዕከል” (återvändandecenter) መቀየር ይኖርባችኋል። ስዊድንን ለቅቀው እስኪወጡ ድረስ ወይም በሌላ ምክንያት ከስድተኛ ጉዳይ ጽ/ቤት መስተንግዶ ክፍል እስኪሰረዙ ድረስ የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብታቸው ይጠበቃል።

በእምቢታው ላይ ያለው ውሳኔ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ለሥራ ፈቃድ የሚያመለክቱ ከሆነ፣ ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እንዲወጡ ይደረጋሉ እናም ከዚያ በኋላ የገንዘብ ድጋፍ ወይም መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት አይኖርዎትም። ከእርስዎ ጋር አብረው ለመኖሪያ ፈቃድ ለሚያመለክቱ የቤተሰብዎ አባላትም ተመሳሳይ ነው።

የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ዘንድ ስለ መቀመጥ የበለጥ ለማንበብ።t

ራስህ ባዘጋጀኸው ቤት መቀመጥ

የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” በሚያዘጋጀው የመኖሪያ ቦታ መቀመጥ የማትፈልጉ ሰዎች፥ የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግል መፈለግ ትችላላችሁ። ብዙ ሰዎች ላስገቡት ማመልከቻ መልስ እስኪያገኙ ድረስ፥ በዘመድ ወዳች ቤት ተጠግተው እየኖሩ መጠበቅ ይመርጣሉ። የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግላችሁ ማዘጋጀት የመረጣችሁ ሰዎች፥ የመኖሪያ ቤት ወጭያችሁን ራሳችሁ መቻል ይኖርባችኋል።

በኣንድ ኮሙን፡ ወደ ስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት ያለባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች ናቸው ተብለው ወደ ተመደቡ ሠፈሮች ቤት የቀየራችሁ ከሆነ፥ የዕለት አበል (dagersättning) እና ልዩ ድጎማ (särskilt bidrag) የሚባለውን ጥቅም የማግኘት መብታችሁን ታጣላችሁ።

ራስህ ባዘጋጀኸው ቦታ ስለ መኖር የበለጠ ለማንበብ።

Last updated: