መኖሪያ ቦታ
Boende – amhariska
የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብታችሁ መልስ እስኪመጣላችሁ በምትጠብቁበት ወቅት የመኖሪያ ቦታ ችግር ያለባችሁን ሰዎች፥ የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ሊረዳችሁ ይችላል። ራሳችሁ በግላችሁ ጥረት የመኖሪያ ቤት ማዘጋጀት ትችላላችሁ፥ ለምሳሌ ወዳጅ ዘመድ ጋር በመጥጋት። በዚህ መልክ የራሳችሁን መኖሪያ ቤት ካዘጋጃችሁ፥ ጽ/ ቤቱ ሲፈልጋችሁ ሊያገኛችሁ እንዲችል፥ ያላችሁበትን አድራሻ ለስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ማሳወቅ አለባችሁ።
የስደተኞች ””ጉዳይ ጽ/ ቤት”” ዘንድ መቀመጥ
የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት”፥ እናንተ ውሳኔ በምትጠብቁበት ግዜ ውስጥ፥ የምትቀመጡበት ግዜያዊ መኖሪያ ቤት ያቀርባል። ለመኖሪያው የሚሆን ገንዘብ ከሌላችሁ፥ የመኖሪያ ወጪውን የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ይከፍላል።
ቤት ውስጥ የመቆየት መብታችሁ ይነሳል
አገር ውስጥ መቀመጥ አትችሉም ወይም አገር ለቃችሁ እንድትወጡ የሚል ውሳኔ ከደረሳችሁ እና ውሳኔ በሥራ ላይ መዋል ከጀመረ፥ ወይም በራሳችሁ ፈቃድ አገር ለቅቃችሁ የምትወጡበት ቀን ካለፈ፤ የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” እንድትቀመጡበት የሰጣችሁ ቤት ውስጥ የመቆየት መብት አይኖራችሁም። ይህ በሞግዚታዊ ሃላፊነት የምታሳድገው ከ18 ዓመት በታች የሆነ፥ አብሮ የሚኖር ልጅ የሌለውን አዋቂ ሰው የሚመለከት ነው።
ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች በስዊድን የስደት ኤጄንሲ (Migration Agency) ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊቆዩ እና ስዊድንን ለቀው እስከሚወጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እስኪወጡ ድረስ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብታቸውን ሊያጠብቁ ይችላሉ። በእምቢታው ላይ ያለው ውሳኔ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ ለሥራ ፈቃድ የሚያመለክቱ ከሆነ፣ ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እንዲወጡ ይደረጋሉ እናም ከዚያ በኋላ የገንዘብ ድጋፍ ወይም መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት አይኖርዎትም። ከእርስዎ ጋር አብረው ለመኖሪያ ፈቃድ ለሚያመለክቱ የቤተሰብዎ አባላትም ተመሳሳይ ነው።
የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” ዘንድ ስለ መቀመጥ የበለጥ ለማንበብ።t
ራስህ ባዘጋጀኸው ቤት መቀመጥ
የስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” በሚያዘጋጀው የመኖሪያ ቦታ መቀመጥ የማትፈልጉ ሰዎች፥ የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግል መፈለግ ትችላላችሁ። ብዙ ሰዎች ላስገቡት ማመልከቻ መልስ እስኪያገኙ ድረስ፥ በዘመድ ወዳች ቤት ተጠግተው እየኖሩ መጠበቅ ይመርጣሉ። የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግላችሁ ማዘጋጀት የመረጣችሁ ሰዎች፥ የመኖሪያ ቤት ወጭያችሁን ራሳችሁ መቻል ይኖርባችኋል።
በኣንድ ኮሙን፡ ወደ ስደተኞች ”ጉዳይ ጽ/ ቤት” የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት ያለባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች ናቸው ተብለው ወደ ተመደቡ ሠፈሮች ቤት የቀየራችሁ ከሆነ፥ የዕለት አበል (dagersättning) እና ልዩ ድጎማ (särskilt bidrag) የሚባለውን ጥቅም የማግኘት መብታችሁን ታጣላችሁ።