የራስህ መኖሪያ

Eget boende – amhariska

ይህ መረጃ ለእናንት፥ ስዊድን ውስጥ የጥገኝነት ማመልከቻ አስገብታችሁ ውሳኔ እስኪሰጣችሁ ደረስ የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግል ጥረት አዘጋጅታችሁ ለምትጠብቁ ሰዎች የተዘጋጀ ነው።

“የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” በሚያዘጋጀው የመኖሪያ ቦታ መቀመጥ የማትፈልጉ ሰዎች፥ የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግል መፈለግ ትችላላችሁ። ብዙ ሰዎች ላስገቡት ማመልከቻ መልስ እስኪያገኙ ድረስ፥ በዘመድ ወዳች ቤት ተጠግተው እየኖሩ ውሳኔ መጠበቅ ይመርጣሉ። የራሳችሁን መኖሪያ ቦታ በግላችሁ ማዘጋጀት የመረጣችሁ ሰዎች፥ የመኖሪያ ወጭያችሁን ራሳችሁ መቻል ይኖርባችኋል።

”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” ባዘጋጀው መኖሪያ ቦታ ሆነ በግላችሁ ባዘጋጃችሁት መኖሪያ ቦታ ብትኖሩም፥ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” ሊያገኛችሁ በሚፈለገበት ግዜ የምትገኙ መሆን አለባችሁ። ከምትኖሩበት ቤት ወደ ሌላ ሥፍራ በምትቀይሩበት ግዜ” የጽ/ ቤታችንን እንግዳ መቀበያ ክፍል ማሳወቅ አስታውሱ።

ስለ አዲሱ አድራሻዎን መልእክት የሚያስተላልፉበት ቅፅ፡- Adressanmälan eller adressändring (አድራሻ መቀየር)፡የቅፁ ቁጥር Mot93 ነው። (በስዊድሽኛ ቋንቋ) Pdf, 631.9 kB, opens in new window.

ቅጹን በዚህ መልክ መሙላት ይቻላል። Adressanmälan eller adressändring (Mot 93)

አንዳንድ የመኖሪያ ቤት አካባቢዎች የሚሰጣችሁን የድጎማ መጠን ሊነኩ ይችላሉ

የማህበረ- ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት ያለባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች አሉ። ወደ እነዚ ዓይነቶች አካባቢዎች ቤት ቀይራችሁ በሚትሄዱበት ግዜ፥ የዕለት አበል (dagersättning) እና ልዩ ድጎማ (särskilt bidrag) የሚባለውን ድጋፍ የማግኘት መብታችሁን ልታጡ ትችላላችሁ። በእውነት ከምትኖሩበት አድራሻ የተለየ ሌላ አድራሻ ከሰጣችሁም፥ እንዲሁ የዕለት አበል እና ልዩ ድጎማ ሚባለውን ጥቅምን የማግኘት መብታችሁን ታጣላችሁ፣ ለምሳሌ የፖስታ ሳጥን ቁጥር መስጠት።

መኖሪያችሁን ቀይራችሁ የምትሄዱበት አካባቢ፥ የድጎማን መጠን ሊያስቀር የሚችሉ ይሆኑ እንደሆነ፥ ከዚህ በታች ባለው ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ማጣራት ትችላላችሁ።

አድራሻውን እዚህ ይጻፉ፥

በቀይ በተመለከተ = ወደ እዚህ አዳራሻ ከቀየሩ ድጎማ የማግኘት መብትዎን ያጣሉ።

በአረንጓዴ በተመለከተ = ወደ እዚህ አዳራሻ ከቀየሩ ድጎማ የማግኘት መብትዎ አይነካም።

ያስተውሉ፥ ትክክለኛ መልስ ለማግኘት አድራሻውን በትክክል መሙላት አለብዎት። የፖስታ ሳጥን ቁጥር አይሆንም።

”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” በሚያዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራ ሁሌ ቦታ ይኖራችኋል።

በማንኛውም ምክንያት፥ ራሳችሁ በግል ጥረት ባገኛችሁት መኖሪያ ቦታ ውስጥ መቀመጥ የማትችሉበት ሁኔት ከተፈጠረ፥ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት” በሚያዘጋጀው መኖሪያ ሥፍራዎች ውስጥ ቦታ አታጡም። ይህን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፥ የተመዘገባችሁበት ጽ/ ቤት እንግዳ ማስተናገጃን (mottagningsenhet) አነጋግሩ።

ፈቃዳችሁን ስታገኙ

ራሳችሁ ባዘጋጃችጉት መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ፥ የመኖሪያ ፈቃዳችሁ (uppehållstillstånd) ሲመጣ፥ ወደፊት የምትኖሩበት የመኖሪያ ቤት የማዘጋጀት ጉዳይ ራሳችሁ የምትወጡት ጉዳይ ነው የሚሆነው። አብዛኛውን ግዜ ”የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት”፥ አንድ ሰው ፈቃዱን ካገኛችበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር ጊዜ ድጋፍ ያደርግለታል።

ግዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ በምታገኝበት ግዜ ስለሚሆነው ለማወቅ ተጨማሪ እዚህ አንብቡ።

ስዊድን ውስጥ እንዲኖሩ ካልተፈቀደልህ

በግልህ የመኖሪያ ሥፍራ ያዘጋጃችሁና ስዊድን ውስጥ ለመኖር የጠየቃችሁት ጥያቄ ውድቅ የሆነባችሁ ወይም አገር ለቅቃችሁ እንድትወጡ የተወሰነባችሁ ሰዎች፣ ውሳኔው ከሚጸናበት ዕለት ጀምሮ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ባዘጋጀው “የተመላሽ ማቆያ ማዕከል” (återvändandecenter) ውስጥ ማረፊያ ቦታ እንድታገኙ ጥሪ ይደረግላችኋል።

የጥገኝነት ጥያቄዎ ውድቅ ሲሆን በመካያው ምን እንደሚከተል ለማወቅ የበለጠ ያንብቡ! (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: