ቅጹን በዚህ መልክ መሙላት ይቻላል። Adressanmälan eller adressändring (Mot 93)

Så här fyller du i blan­ketten Adressanmälan eller adressändring (Mot93) – amhariska

ቅጹ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ መሙያ ቦታ መሞላት አለበት። አንዲሁም ቅጹ መጨረሻ ላይ ፊርማዎ መስፈር ይኖርበታል። አንድ መስመር ሳይሞላ ቢቀር የቀን አበልዎን ወይም የሚያገኙትን ልዩ ድጎማ በሚመለከት ጉዳይ ላይ የራሱ ተፅዕኖ ሊያደርግ ይችላል። እንዲያውም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የቀን አበልዎን ወይም ልዩ ድጎማ የማግኘት መብትዎን ሊሰርዝ ይችላል።

1. ግለ-ሰብዓዊ መረጃ

ወደ አዲሱ አድራሻ ሲቀይሩ፥ ከእርስዎ ጋር የሚጓዙ ሰዎች በሙሉ፣ ልጆችን ጨምሮ፣ ሥማቸውን፥ የተሌፎን ቁጥር እና የዶሴ ቁጥር ይሙሉ።

2. የተመዘገበው/አዲሱ አድራሻ

c/o:

ከሚለው የአደራ ምልከታ ሥር፥ የመኖሪያው ቤቱ በር ላይ ወይም ፖስታ ሳጥኑ ላይ የተጻፈውን መጠሪያ ሥም ያስፍሩ። ሥምዎ የመኖሪያው ቤት በር ላይ ወይም የፖስታ ሳጥኑ ላይ የተፃፈ ከሆነ ግን c/o. የሚለው የአደራ ምልከታ ማስፈር አያስፈልግም።

የጐዳና አድራሻ፡-

ቤትዎ የሚገኝበት ሰፈር ውስጥ ያለውን የመንገድ ሥም ያስፍሩ።

የመኖሪያ ቤት ቁጥር (Lägenhetsnummer)፡-

በጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ፥ ባለ አራት አሃዙ የጋራ መኖሪያ ቤቱን (lägenhetsnummer) ቁጥር ያስፍሩ። የጋራ መኖሪያ ቤቱን ቁጥር የህንፃው መግቢያ ላይ ወይም የመኖሪያ ቤቱ በር ላይ ወይም ፖስታ ሳጥኑ ላይ ወይም ኮንትራት የተፈራረሙበት ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ፖስታ ቁጥርና ክፍለ ከተማውን፡-

የፖስታ ቁጥርና የወረዳውን ወይም ክፍለ ከተማውን ስም ያስፍሩ

አድራሻው - እስከ የፀና ይሆናል፥(ዓመተ ምህረት፥ ወር፥ ዕለት)

አዲሱ አድራሻ ከየትኛው ቀን ጀምሮ እንደሚፀና ይግለፁ፥ (ዓመተ ምህረት፥ ወር፥ ዕለት)

3. ተጨማሪ ማብራሪያ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት እንዲያውቀው የሚፈልጉት ተጨማሪ ነገር ካለዎት፥ እዚህ ላይ ያስፍሩ።

4. ፊርማ

የአድራሻ መቀየሩ ጉዳይ ከአንድ አዋቂ ሰው በላይ የሚያካትት ከሆነ፥ ዕድሜያቸው ከ 18 ዓመት በላይ የሆኑቱ ሰዎች በሙሉ ፊርማቸውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል።

በቅጹ ላይ ፊርማዎን ሲያሰፍሩ የሚከተሉትን ጉዳዮች አረጋግጠዋል ማለት ነው፡-

  • የሰጡት መረጃ ትክክልና የተሟላ መሆኑን፥
  • አንዳች ለውጥ በሚኖርበት ግዜ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የማሳወቅ ግዴታ እንዳለብዎት መገንዘብዎን፥
  • ትክክል ያልሆነ መረጃ መስጠት፥ ወይም መረጃ ማስቀረት እንዲሁም ማጉደል ወይም አስቀድመው የሰጡት መረጃ በሚቀየርበት ግዜ፥ መቀየሩን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አለማሳወቅ የሚያስቀጣ መሆኑን ማወቅዎን ነው።

ቅጹን ሞልተው ከጨረሱ በኋላ መስተንግዶ ክፍላችን (mottagningsenhet) ዘንድ ያስገቡ ወይም ይላኩ።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የመስተንግዶ ክፍል (mottagningsenhet) አድራሻዎችን የግንኙነት መረጃ (kontaktuppgifter) ከሚለው ገጽ ላይ ያገኙታል፡-

የፖስታና አድራሻዎች (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

Last updated: