ትምህርት

Skola – amhariska

ጥገኘኝነት የሚጠይቁ ልጆች በሙሉ ትምህርት የመማር መብት አላቸው፡፡ ይሁን እንጂ አዋቂዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የመኖሪያ ፈቃድ እስኪያገኙ መጠበቅ ሊኖርባቸው ይችላል፡፡

ጥገኝነት የሚጠይቁ ልጆች እና ወጣቶች ሁሉ ቅድመ ትምህርት ቤት እና ትምህርት ቤት ገብተው የመማር መብት አላቸው፡፡  በግዛቱ ውስጥ እንዳሉት ልጆች ሁሉ እነዚህ ለልጆች እና ወጣቶች ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተከታተሉ መሆናቸውን መከታተል የግዛቱ አስተዳደር ሀላፊነት ነው፡፡  ይህ ለቅድመ ትምህርት፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚተገበር ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር መብት ለማግኘት ወጣት የጥገኝነት ጠያቂዎች ትምህርታቸውን ዕድሜያቸው 18 ከመሙላቱ በፊት መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡

ትንንሽ ልጆችም ቅድመ ትምህርት የመማር መብት አላቸው፡፡ 

አንድ ዓመት የሞላቸው ትንንሽ ልጆች ወላጆቻቸው ሥራ በሚሰሩበት ወይም በሚማሩበት ጊዜ ቅድመ ትምህርት ቤት የመግባት መብት ይኖራቸዋል፡፡  ከመኸር ጊዜ  ጀምሮ ማትም ልጆቹ ሶስት አመት ከሚሞላቸው ጊዜ ማለት ጀምሮ ምንም አይነት ክፍያ ሳይከፍሉ በየሳምንቱ ለ 15 ሰአታት ቅድመ ትምሀርት የመማር እድል አላቸው፡፡  ቅድመ ትምህርት ልጆች ወላጀቻቸው ወደ ሥራ ወይም ትምህርት ሲሄዱ የሚቆዩበት ሥፍራ ብቻ አይደለም፡፡  ልጆች ወላጆቻቸው ስራ ባይሰሩም ወይም ባይማሩም ነቅድመ ትምህት በመሳተፋቸው ጥቅም ሊያገኙ እና ሊድጉ ይችላሉ፡፡

የግዛቱ አስተዳደር ለትምህርት ቤቶች ሀላፊነት አለበት 

የግዛቱ አስተዳዳር በግዛቱ ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች እኩል ጥገኝነት ጠያቂ ልጆች እና ወጣቶች ቅድ ትምህርት እና ትምህርት ማግኘታቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት፡፡

የስደተኞች ኤጄንስ ያለወላጆች ፈቃድ የጥገኝነት ጠያቂ ልጆች መረጃዎችን ለግዛትቱ አስተዳደር አያስተላልፍም፡፡  ለስደተኞች አጀንሲ ፈቃድዎን መስጠት ይችላሉ እሱም ፈቃዱን ካገኘ በኋላ የልጆችዎን ስም፣ የተወለዱበትን ቀን፣ ቋንቋ፣ የትውልድ ሀገር እና የኬዝ ቁጥራቸውን ለግዛቱ አስተዳደር ይልካል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የግዛቱን አስተዳደር በግልዎ በማናገር  ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት እንዲገቡ እንደሚትፈልጉ መግለጽም ትችላላችሁ፡፡ 

በስውድን ውስጥ ስላሉ ትምህርት ቤቶች እና የትምህርት ሥርዓት ተጨማሪ አንብቡ

https://www.informationsverige.se/en/jag-ar-asylsokande/skola-under-asyltiden External link.

https://www.skolverket.se/regler-och-ansvar/ansvar-i-skolfragor/nyanlandas-ratt-till-utbildning (በስዊድሽኛ ቋንቋ) External link, opens in new window.

ወላጆቻቸው ጥገኝነት የጠየቁ ልጆች ስላላቸው መብቶች ስለልጆች በሚለው ገጽ ላይ ያንብቡ

እርስዎ ጥገኝነት ጠያቂ እንደ መሆንዎ የስዊድነኛ ቋንቋ ለማወቅ ይፈልጋሉ​

እስዊድን ኣገር የመኖር ፈቃድ ከተሰጠህና የግብረ ጽ/ቤት ከተመዘገብክ የስዊድሽኛ ቋንቋ ለውጭ ኣገር ሰዎች (ኤስ ኤፍ ኢ) ለመማር መብት አለህ። ግን ፈቃድህን ከማግኘትህ በፊት ለመማር ከፈለግክ ወደ ዕርዳታየሚሰጡ ወይንም ማሕበራውያን ትምሕርት ቤቶች ትምሕርተ ስለሚሰጡ ከነሱ ጋር ተገናኝ።

በኢንተርኔት ላይ በግልዎ ስዊድነኛ ቋንቋን ለመማር ብዙ ፕሮግራሞች አሉ እንደ www.informationsverige.se። ያሉ ድህረ ገጾች ላይ የተለያዩ ስዊድንኛ ቋንቋ ለማወቅ የሚረዱ አገናኝ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ። አብዛኞቹ ፕሮግራሞች የኢንተርኔት ግንኙነት ይጠይቃሉ። ሁሉም ግን ከክፍያ ነጻ ናቸው።

በሚቀጥለው ድህረ ገጹ ላይ የስዊድንኛ ቋንቋን ለመማር ሁሉንም አገናኞች ያገኛሉ (www.informationsverige.se – ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

Last updated: