ይግባኝ ለማለት ከፈለጉ

Om du vill överklaga – amhariska

መቀበል የማይችሉት ”ከሚግራሾንስቨርከት” ውሳኔ ቢሰጥዎት፥ ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት መምረጥ ይችላሉ። እዚህ ላይ እንዴት ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ የበለጠ መረጃ ያገኛሉ።

”ከሚግራሾንስቨርከት” የተሰጥዎት ውሳኔ መቀበል ቢያቅትዎት፥ ይግባኝ ለማለት መብት ኣሎት። የይግባኝ ጥያቄ ማቅረብ ማለት፥ ”የሚግራሾንስቨርከት” ውሳኔ እንዲቀየርልዎ ፍላጎትዎን መግለጽ ማለት ነው። የይግባኝ ጥያቄዎ የሚመረምረው ፍርድ ቤት ሲሆን፥ ለይግባኝ ጥያቄ የሚያቀርቡት ጽሁፍዎ ግን፥ ወደ  ሚግራሾንስቨርከት” ነው የሚልኩት። ውሳኔው በተገለጸበት ግልባጭ ላይ፥ ይግባኝ ለማለት የተሰጥዎት ጊዜ ምን ያህል መሆኑን እዛ ሰፍሮ ያገኙታል። አብዛኛውን ጊዜ፡ የውሳኔውን ግልባጭ ከተቀበሉበት ቀን አንስቶ፥ ሶስት ሳምንት ያህል ጊዜ ይኖሯል። ጠበቃ ካልዎት፥ እሱ ወይ እሷ ይግባኝ ለማለት ይረድዎታል።

የመኖሪያ-ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፥ ጥያቄዎ ውድቅ ከተደረገ እና፥ ውሳኔው ሲሰጥዎም፡ እርሶ ገና ስዊድን አገር ውስጥ የሚገኙ ከሆነ፥ ይግባኝ ለማለት ምርጫዎ ቢሆንም፥ ሆኖም ወደ አገርዎ እንዲመለሱ ዕቅድዎ ማዘጋጀት አለቦት። ውሳኔው በተገለጸበት ሰነድ ላይ፥ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፥ እርሶ ስዊድን አገር ቆይታ የማድረግ መብት ያሎት እንደሆነ፥ እዛ ተጽፏል።

የመተዳደሪያዎን ወጭ መሸፈን ባለመቻልዎ ወይም ሕግ አክብረው መኖር ባለመቻልዎ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ጠያቄዎ ውድቅ ቢሆንብዎት ይግባኝ ማለት ይችላሉ።

”የሚግራሾንስቨርከት ፍርድ ቤት” የእርስዎን አቤቱታ ይመረምራል

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በትክክለኛ የግዜ ገደብ ውስጥ የደረሰውን ይግባኝ ሁልግዜ ለስደተኞች ጉዳይ ፍርድ/ ቤት ያሳልፋል።

ይግባኙ ወደ ፍርድ ቤት ከማሳለፉ በፊት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በራሱ ውሳኔውን ለመቀየር ላለመቀየር አቋም ይወስዳል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔው ለመቀየር ከወሰነ ይግባኝ የተጠየቀበትን ውሳኔ የሚተካ ሌላ አዲስ ውሳኔ ይጽፍና ከይግባኙ ጋር አያይዞ ወደ ፍርድ ቤቱ ይካል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የቀየረው ውሳኔ ትክክል መሆኑን የሚያጸድቀው የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ/ ቤት ነው።

የይግባኝ ጥያቄህ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከደረሰ ሰባት ቀን ባልሞላ ግዜ ውስጥ፥ ለስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት (migrationsdomstolen) ይቀርባል።

የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ይግባኙ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ይግባኙን የሚመለክት ጥያቄ እና የፍርድ ቤቱ አሰራር የሚመለከት ጥያቄ በሙሉ የሚያቀርቡት ለፍርድ ቤቱ ነው። የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤትን ብይን የመከታተሉ ሃላፊነት የእርሶ ነው። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አይከታተልሎትም።

አንድ ህዝባዊ የውሎ ቦታ (ሥራ ወይም ሥልጠና) ካልዎት፥ ወደ ውሎው ቦታ ለመጓጓዝ ይከፈልዎት የነበረውን ገንዘብ ይግባኙ ለፍርድ ቤት ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ይቋረጣል።

ሃሳብዎን ከቀየሩና ይግባኙን መሳብ የሚፈልጉ ከሆነ፥ ውሳኔውን መቀበልዎን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማሳወቅ ይችላሉ። ይህን ካደረጉ የይግባኙ ጉዳይ አይታይም፥ እንደገናም ይግባኝ ማለት አይችሉም።

የስደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤትን በተመለከተ የሚያስፈልገውን መረጃ ለማግኘት የስዊድን ፍርድ ቤቶች ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ትችላለህ። (በስዊድሽኛ ቋንቋ) External link, opens in new window.

አቤቱታ በዚህ ኣኳሃን ይጽፋሉ

ውሳኔው በተገለጸበት ግልባጭ ላይ፥ እንዴት ይግባኝ ለማለት እንደሚችሉ፥ እዛ ሰፍሮ ያገኙታል።  የሚግራሾንስቨርከት” ውሳኔ ይግባኝ ለማለት ከፈለጉ፥ እንዲለውጥ የሚፈልጉትን ውሳኔ እና፥ ለምን እንዲለወጥ እንደፈለጉ በመግለጽ፥ ”ለሚግራሾንስቨርከት” ደብዳቤ መጻፍ ይኖርዎታል። የእርስዎን ምክንያቶች የሚደግፉ ዶክመንቶችን (ዋናውን ቅጅ ቢሆን ይመረጣል) ወይም ሌሎች መረጃዎችን ካልዎትም ይልካሉ።

በእርስዎ የአቤቱታ ጽሁፍ ላይ፥ የእርስዎን የግል መረጃ እና የጉዳዩን ቁጥር መጻፍ አለብዎት። የጉዳዩ ቁጥር፡ በእርስዎ የጥገኝነት ፈላጊነት ካርድ (LMA) ላይም ያገኙታል። እንዲሁም፡ ”ሚግራሾንስቨርከት” ወይም ”ፍርድ ቤቱ” እርሶን ፈልጎ እንዲደርስዎት፥ የርሶ ስልክ ቁጥር እና አድራሻ ይጻፋሉ።

የእርስዎ አቤቱታ፡ በተሰጥዎ ጊዜ ውስጥ ወደ ”ሚግራሾንስቨርከት”መድረሱ፥ በጣም አስፈላጊ ነው። በዚህ ገጽ ባለው ሰንጠርጅ ላይ፥ ይግባኝ ለማለት ምን ያህል ጊዜ እንደ ተሰጥዎት ማየት ይችላሉ፤ ምክንያቱም፡ እንደየ ውሳኔው፡ የጊዜ ልዩነት ስለሚኖረው ነው። ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው፥ የውሳኔው መረጃ እጅዎ ላይ እንደ ደረሰ ነው።

አቤቱታውን ራስዎ ማቅረብ የማይችሉ ከሆነ፣ ሌላ ሰው እንዲያግዝዎት መጠየቅ ይችላሉ። በዚያ ሁኔታ ውስጥ፥ የውክልና-ሥልጣን ስለ ተሰጠው ሰው፥ “ለሚግራሾንስቨርከት” ማስረጃ ማስገባት ይኖርብዎታል።

የውክልና-ሥልጣን ምንድን ነው?

የውክልና-ሥልጣን፥ አንድ አመልካች፡ ሌላ ሰው በእሱ/ሷ ፈንታ ወይም እንደ እሱ/ሷ ሆኖ ጉዳዮችን እንዲፈጽምለት በጽሁፍ መብት የሰጠበት እና በፊርማው ያረጋገጠው ሰነድ ማለት ነው። አንድ የውክልና-ሥልጣን ለምሳሌ፥ አንድ ሰው ለሌላ ሰው ማመልከቻ እንዲያስገባለት፥ ለውሳኔ ምክንያት የሆኑትን ነጥቦች እንዲወስድ ወይም ውሳኔውን ይግባኝ እንዲልለት መብት የሚሰጥ ሊሆን ይችላል። የውክልና-ሥልጣን በውክልና ሰጪው የተጻፈ መሆን አለበት። እንዲሁም “ሚግራሾንስቨርከት” በጠየቀ ጊዜ፥ ዋናውን ቅጅ (ኦሪጂናል ሰነድ) ማቅረብ መቻል ያስፈልጋል።

የውክልና-ሥልጣን ለሌላ ሰው መስጠት እንዲችሉ፥ ”ለሚግራሾንስቨርከት” የሚቀጥሉት ነጥቦች ያካተተ አንድ ደብዳቤ ይጽፋሉ፡-

  • የውክልና-ሥልጣን መሆኑ
  • የውክልና-ሥልጣን ሰጪው ሙሉ ስም፥ የልደት-ቀን እና ኣድራሻ
  • ውክልና-ሥልጣን ተቀባዩ፥ ማድረግ የሚችለው የተሰጠው መብት
  • የውክልና-ሥልጣን ተቀባዩ ስም፥ የማንነት-ቁጥር (ፐርሾን-ኑመር) እና አድራሻ
  • የውክልና-ሥልጣን ሰጪው ፊርማ
  • የውክልና-ሥልጣን የተፈረመበት ቀን እና ቦታው

Power of Attorney, form number 107011 (ባእንግሊዝኛቋንቋ) Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

”በሚግራሾንስቨርከት ፍርድ ቤት” ውሳኔ ላይ አቤቱታ ማቅረብ ከፈለጉ

”በሚግራሾስንቨርከት ፍርድ ቤት” በተሰጠ ፍርድ ቅሬታ ቢኖርዎት፥ የፍርዱ ውሳኔ ግልባጭ በደረስዎት በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ፤ ”ለሚግራሾንስቨርከት የበላይ ፍርድ ቤት” ይግባኝ ማለት ይችላሉ። ”ሚግራሾንስቨርከት የበላይ ፍርድ ቤት”፥ የመጨረሻው የፍርድ ተቋም በመሆኑ፥ በዚህ ተቋም የሚሰጠው ውሳኔም፥ ”ሚግራሾንስቨርከት” እና ”ሚግራሾንስቨርከት ፍርድ ቤት” በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ለሚወስዱት አቋም ሁሉ፥ እንደ መመሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።

”የሚግራሾንስቨርከት የበላይ ፍርድ ቤት”፡ አንዳን ገና ሕጋዊ መመሪያ ያልተሰጣቸው የይግባኝ ጉዳዮች ወይም ”ሚግራሾንስቨርከት ፍርድ ቤት” በስህተት አኳሃን ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዳያች ብቻ ነው ለይቶ የሚመረምረው። በአብዛኛዎቹ የቀረቡለት የአቤቱታ ጉዳዮች፥ ”የሚግራሾንስቨርከት የበላይ ፍርድ ቤት” እንደገና እንዳይመረመሩ ነው የሚወስነው። እንደሱ ከሆነ፡ ጸንቶ የሚያገለግለው፡ ”የሚግራሾንስቨርከት ፍርድ ቤት” ውሳኔ ይሆናል።

ለሁሉም ውሳኔዎች ይግባኝ ለማለት አይቻልም

ይግባኝ ሊጠየቅባቸው የማይቻል አንዳንድ ውሳኔዎች ይኖራሉ። የውሳኔው ሰነድ ላይ ይግባኝ ሊጠይቁበት የሚቻልና የማይቻል መሆኑን የሚገልጽ መረጃ አለ።

ይግባኝ ሊጠይቁ ከማይችሉበት ጉዳይ መሃል አንዳዶቹ

  • አንድን ውሳኔ መቀበልዎንና በውሳኔው የረኩ መሆንዎን በፊርማዎ ካረጋገጡ በኋላ
  • የሰደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ጉዳይዎን አልመለከትም የሚል ውሳኔ ካሳለፈ
  • በግዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድ ሲሰጥዎት

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ይግባኝ የማይባል ጉዳይ ሆኖ እያለ እንኳ የይግባኝ ማመልከቻ በትክክለኛው ግዜ ውስጥ ከደረሰው፥ ይግባኙን ለሰደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ያስተላልፈዋል። ይሁን እንጂ የሰደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ይግባኙን አይመለከተውም።

ለተለያዩ የይግባኝ ጥያቄዎች - የተለያየ የጊዜ ገደብ

”ሚግራሾንስቨርከት”፡ ይግባኝ ለማለት የተስጦት ጊዜ ከመውደቁ በፊት፥ የእርሶ ኣቤቱታ ማግኘት ያስፈልገዋል። ”የፍርድ ቤቱ” ውሳኔ ይግባኝ ለማለት ከፈለጉ፥ ጽሁፍዎ ወደ ”ፍርድ ቤቱ” ይልካሉ። እና የሚያቀርቡት ጽሁፍ፥ ለአቤቱታዎ የተሰጦት ጊዜ ከመውደቁ በፊት፥ ”ፍርድ ቤቱ” ጋር መድረስ አለበት። ውሳኔው በተሰጠበት ግልባጭ ላይ፥ ይግባኝ ለማለት ምን ያህል ጊዜ እንደ ተሰጥዎት፥ እዛ ሰፍሮ ያገኙታል።

የጊዜው ገደብ ካለፈ በኋላ፥ ውሳኔው ሕጋዊ-ኃይል ተስጥቶላ ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ፥ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት ኣይፈቅድም።

ይግባኝ ለማቅረብ የሚፈቀደው የግዜ ገደብ

የሚከተለው ውሳኔ ተቀብሏል

ይግባኝ ማለት የሚችሉበት

ካገር የማባረር ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

ካገር የማባረር ውሳኔ፥ በፍጥነት የሚተገበር

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

የሰደተኞች ጉዳይ ፍርድ ቤት ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

የጥገኝነት ደረጃ መገለጫ ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

የጉዞ-ሰነድ (ፓስፖርት) ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

የውጭ ዜጎች ፓስፖርት ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

ተመልሶ ወደ ሸንገኝ አገሮች የመግባት እገዳ፥ በጊዜው ከስዊድ አገር ባለመውጣትዎ ምክንያት

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ የስደተኞንች ጉዳይ ጽ/ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ

ተመልሶ የመግባት እገዳ፥ በሌላ ምክንያት

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

ስለ ልዩ የገንዘብ ድጋፍ ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

አማራጭ ከለላ እንደ ሚያስፈልገው ሰው ታስበው የመኖሪያ ፈቃድ ውሳኔ (የስደተኛ ደረጃ መገለጫ ይገባኛል ብለው ካመኑበት)

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

ቀዋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እንዳይሰጥዎ ያተላለፈው ውሳኔ

በሶስት ሳምንት ውስጥ፥ ውሳኔ በእጅዎ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ

የቀን ድጎማ ስለ መቀነስ ወይ ስለ መሰረዝ የተሰጠ ውሳኔ

በአምስት ሳምንት ውስጥ፥ የስደተኞንች ጉዳይ ጽ/ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ

ስለ ክትትል ወይ ማቆያ-ቤት የተሰጠ ውሳኔ

የትኛው ግዜ


Last updated: