የቤተሰብ መልሶ መሰባሰብ

Familjeåterförening – amhariska

ቤተሰብዎን ወደዚህ ለማምጣት መብት ይኖርዎታል፥ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት፥ ወይም እንደ ፖለቲካ ጥገኛ ወይም ኣማራጭ ከለላ እንደ ሚያስፈልገው ሰው - በግዜ የተገደበ መኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት፥ ወይም ወደ ትውልድ አገርዎ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ በመከሰቱ ወይም አስጨናቂ ሁኔታ በመኖሩ ምክንያት፥ እንዲሁም ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥዎት የሚያስችል ጥሩ የተስፋ ምክንያት እንዳለ ሲገምገም ነው።

ቤተሰብዎን በራስዎ ኢኮኖሚያዊ ችሎታ የማስተዳደር ግዴታን ሟሟላት የሚገባዎት እንደ ሆነ ሁሉ፥ አንድ የተወሰነ ደረጃን የሚያሟላ የመኖርያ ቤትም እንዲኖርዎት ያስፈልጋል።

ማን የቤተሰብ መልሶ መገናኝት መብት ሊኖረው ይችላል?

እርሶ የሚከተሉትን ነጥቦች ያሟሉ ከሆነ፡ ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ ዕድል ይኖሯቸዋል፡-

  • ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጥዎት
  • እንደ አንድ ጥገኛ ወይም ኣማራጭ ከለላ እንደሚያስፈልገው ሰው በግዜ የተገደበ መኖሪያ ፈቃድ የተሰጥዎት እንደሆነ፥ እንዲሁም ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥዎት የሚያስችል ጥሩ የተስፋ ምክንያት እንዳለ ሲገምገም ነው።
  • በግዜ የተገደበ መኖሪያ ፈቃድ የተሰጥዎት - ወደ ትውልድ አገርዎ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ በመከሰቱ ወይም አስጨናቂ ሁኔታ በመኖሩ ምክንያት፥ እንዲሁም ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥዎት የሚያስችል ጥሩ የተስፋ ምክንያት ካለ ነው።

የቤተ ሰብ መልሶ መገኛኘት፥ በግዜ የተገደበ መኖሪያ ፈቃድ ለተሰጣቸው፥

ስዊድን ውስጥ ለመኖር በግዜ የተገደበ መኖሪያ ፈቃድ የተሰጣችሁ ሰዎች፥ ቤተ ሰቦቻችሁ ወደ እናንተ እንዲመጡና አብሯችሁ እንዲኖሩ የሚቻልበትን ዕድል ማግኘት ብዙ ነገሮች ላይ ይመሰረታል። ከሁሉ በፊት የመኖሪያ ፈቃድ እንዲኖርዎት ያስፈልጋል። ይህም ማለት፥ የመኖሪያ ፍቃድዎ ጸንቶ የሚቆይበት የግዜ ገደብ አልቆ ከሆነና፥ የመኖሪያ ፈቃዱዎ ግዜ እንዲራዘም ማመልከቻ ካስገቡ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤትበቅድሚያ ስዊድን ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድዎን በቀጣይነት የማራዘም መብት ያልዎት መሆኑን ያጣራል። በስዊድን ከለላ ያገኙ መሆንዎ ወይም ቀደም ብሎ የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጥዎት መሆንዎ ብቻ በቂ አይደለም።

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የጸና የመኖሪያ ፈቃድ ያልዎት መሆንዎን ካጣራ በኋላ፥ የቤተሰብዎን የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄን ያስተናግዳል። የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት እርስዎ የመኖሪያ ፈቃድዎን የማራዘም እድል ያለዎት መሆኑን መጀመሪያ ያያል። ረዘም ላለ ግዜ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥዎት የሚያስችል ጥሩ የተስፋ ምክንያት አለ ተብሎ ከተገምገመ በኋላ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የቤተሰቦችዎን ወደ ስዊድን አገር ለመምጣት ያስገቡትን ማመልከቻ መመርመር ይጀምራል፣ አርሶም የሚጠበቅብዎትን ሌሎች ግዴታዎች ማሟላትዎን ያጣጠናል።

የግዜ ገደብ በተጣለበት የመኖሪያ ፈቃድ መምጣት የሚችሉት የቅርብ ቤተ-ሰቦችዎ ብቻ ናቸው።

እንደ ቅርብ ቤተ ሰብ የሚቆጠሩት፥ ባል፥ ሚስት፥ በሕግ የተመዘገበ የኑሮ ጓደኛ ወይም አብሮ እና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ናቸው። ከ18 ዓመትበታችለሆኑ ልጆች እንደ ቅርብ ቤተ-ሰብ የሚቆጠሩት ወላጆች ናቸው። ሌሎች የቤተ-ሰብ አባላት መምጣት የሚችሉ፥አንድ ልዩ የሆነ ምክንያት በሚኖርበት ግዜ ብቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ልጅ እንዲመጣ ሊፈቀድለት ይችላል። እንደ አንድ ጥገኛ በግዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድ ያለህን ወይም አማራጭ ከለላ የሚያስፈልግህ የሆንከውን ወይም ወደ ትውልድ አገርህ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ የተፈጠረብህን ወይም የተለየ አስጨናቂ ሁኔታ ያለብህ ከሆነ ይህን ደንብ እርሶን ይመለከትዎታል።

በዋናው ደንብ መሰረት፡ አዲስ የትዳር እጩዎች (ያልተጋቡ ወይም አብረው የማይኖሩ ከሆነ) ስዊድን ውስጥ ተቀማጭ የሆነው ሰው በግዜ የተገደበ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ከሆነ፥ ቤተሰቡ የመኖሪያ ፈቃድ የማግኘት ዕድል አይኖራትም/ አይኖረውም። ይሁን እንጂ አብረው የማይኖሩ ሰዎችም ልዩ አስተያየት ተደርጎላቸው እንዲገናኙ የሚፈቀድበት ግዜ አለ። ስለዚህ እዚህ ስዊድን የምትኖረው ግለሰብ፥ የአንድ ጥገኛ ደረጃ ያለህ ወይም አማራጭ ከለላ የሚያስፈልገውን ሰው፡ ወይም ወደ ትውልድ አገርህ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ የተፈጠረብህ ወይም ወደ ትውልድ አገርህ መመለስ የሚከለክል ሁኔታ በመከሰቱ ወይም የተለየ አስጨናቂ ሁኔታ በመኖሩ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ያገኝህ መሆንንና ወደ ስዊድን ከምታመጣው (የምታመጣት) ሰው ጋር በሃገር ቤት እያላችሁ የጠበቀ ግንኙነት እንደ ነበራችሁ እና - በትውልድ አገራችሁ ውስጥ አብራችሁ ኑሮ መቀጠል የማትችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ይሆናል። በዚህ ደንብ መሰረት፥ ቀደም ብሎ አብረው መኖር ያልቻሉ ተማሳሳይ ጾታ ያላቸው ግለሰቦች ስዊድን ውስጥ አብረው መኖር ይችላሉ።

ቤተሰብዎ ለሁለት ዓመታት ጸንቶ የሚቆይ ፈቃድ ማግኘት የሚችሉ ቢሆንም፥ የእርሶ ፈቃድ ጸንቶ እስከሚቆይበት ዕለት ድረስ ነው ቤተ ሰቦችዎ የሚሰጣችው የፈቃድ ግዜ ርዝመት። ይህ ማለት፥ የእርሶ ፈቃድ ሊቃጠል አምስት ወራት ቀርቶት ከሆነ፥ ቤተሰብዎ አምስት ወራት ብቻ የሚቆይ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኛሉ ማለት ነው። የቤተ ሰብዎ አባላት ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ የሚችሉት የመኖሪያ ፈቃድ ይዘው ቢያንስ ሶስት ዓመታት ከኖሩ በኋላ ነው።

ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ካለዎት፥አዲስ የትዳር እጩ ቢሆን/ ብትሆንም ወደ ስዊድን ለመምጣት የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ ማስገባት ትችላለች/ ይችላል።

በትዳር ወይም ከኑሮ ጓደኛ ጋር አብሮ በመኖር ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ምን መሟላት እንዳለበት የበለጠ ለማውቅ እዚህ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ራስን የማስተዳደር ግዴታ

ከቤተሰብ ጋር የመገኛኘት መብትዎ ከተረጋገጠ ራስን የማስተዳደር ግዴታን መወጣት ሊመለከትዎት ይችላል። ይህ ማለት እርስዎና ቤተሰብዎ በሚገባ ለመኖር የሚያስፈልገውን ወጪ እርስዎ ራስዎ መሸፈን ይኖርብዎታል። በተጨማሪም ቤተሰብዎ ወደ ስዊድን ሲመጡ ከእርስዎ ጋር የሚኖሩበት፥ በመጠንና በጥራት ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ሊያዘጋጁ ይገባዎታል።

አንተ ራስን የመቻል ግዴታ፡ አንተን በጥገኛነት ደረጃ ቅቡልነት ካገኘህ አይመለከትህም - የቤተሰቦችህ አባላት አንተ የመኖሪያ ፈቃድ ወይም በጥገኛ ደረጃ ቅቡልነት ካገኘህበት ዕለት ጀምሮ፥ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ያስገቡ እንደሆነ ነው።

ስለ ራስን ማስተዳደር ግዴታና ማን እንደሚመለከት የበለጠ ላማወቅ እዚህ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ማመልከቻን በጊዜ ማስገባት አስፈላጊ ነው

ቤተሰቦችዎ፥ እርስዎ ፈቃድ ካገኙበት ጊዜ በሶስት ወራት ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ ካስገቡ የ'መታዳደሪያህን መቻል' ግዴታ ማሟላት አይመለከቶትም። ስለዚህ ማመልከቻውን በማለፊያ ጊዜ ውስጥ ጠቃሚ ነው።

ማመልከቻው በፍጥነት መድረሱን ዕርግጠኛ ለመሆን የበለጠው መንገድ እርስዎ ራሱዎ የቤተሰቦችዎን ማመልከቻ በኢንተርኔት ድረገፅ ቢያስገቡ ነው። በቤተሰቦችዎ ፈንታ እርስዎ ማመልከቻውን የሚያስገቡ ከሆነ የውክልና ሥልጣን እንዲኖሮት ያስፈልጋል። የስደተኞች ጽ/ቤት፥ ማመልከቻውን ከመዘገበው በኋላ ቤተሰቦችዎ የስዊድንን ኤምበሲ ወይም ቆንስላ ጽ/ቤት ለመጎብኘት ቀጠሮ እንዲይዙ ይጠየቃሉ።

የውክልና ሥልጣን ምንድን ነው? (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የቤተሰቦችዎን ማመልከቻ በኢንተርኔት ድረገፅ ለመላክ በዚህ ይሂዱ

በቤተሰቦችዎ ፈንታ ማመልከቻ ስለማስገባት ተጨማሪማብራሪያ ያንብቡ

ማመልከቻውን ተከታተል

ቤተሰብዎ ማመልከቻ ካስገቡ በኋላ የዶሴ ቁጥር ወይም የጉዳይ ቁጥር (ärendenummer) ይሰጣቸዋል። በዚህ ቁጥር አማካይነት፥ ማመልከቻው በስደተኞች ጽ/ቤት መመዝገቡንና ውሳኔም ተሰጥቶት እንድሆን በድረገፅ መከታተል ይቻላል።

ማመልከቻውን ተከታተል

የስደተኛ ቤተ ዘመድ ወደ ስዊድን ሲመጣ የሚሰጥ የመጓጓዣ ድጎማ

በጥገኝነት ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ የተሰጣችው ግለሰቦች ቤተ ዘመዶቻችው ወደ ስዊድን የሚጓዙ ከሆነ የመጓጓዣ ድጎማ እንዲሰጣችው ማመልከት ይችላሉ።

የመጓጓዣ ድጎማ ማግኘት የሚችሉት ቤተ እዝማዱ ከስዊድን ውጭ ቀደም ብሎ ከእርስዎ ጋር በሚከተለው መልክ አብራችሁ የኖራችሁ ከሆነ ነው፡-

  • እንደ ባልና ሚስት ወይም ባትጋቡም እንደ ባልና ሚስት ኖራችሁ ከነበረ
  • ልጆችዎ (ያላገቡና ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች ከሆነ)

ይህ ድጎማ እንዲሰጥዎት ማመልከት የሚችሉት በ1951 የጄነቫ ኮንቬንሽን መሰረት የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙና ”klassningskod” AF ወይም A3 የሚል የደረጃ ኮድ ካገኙ ነው። አገር የለሽ ፍልስጤማዊ ከሆኑና የመጓጓዣ ሰነድ ወይም እንደ ስደተኛ ዕውቅና ያገኙ ከሆኑም ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ።

ድጎማውን ለማግኘት ማመልከቻ ከማስገባትዎ በፊት፣ ቤተ ዘመዶችዎ የስዊድን መኖሪያ ፈቃድና የጸና ፓስፖርት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

የስዊድን ዜጋ ከሆኑ ወይም እርስዎ ወይም ቤተ ዘመዶችዎ የመጓጓዣውን ወጪ የመክፈል እቅም ያላቸው ከሆነ ድጎማ ማግኘት አይችሉም።

እንደ ደንቡ፣ ድጎማው ቤተ ዘመዶችዎ ከሚገኙበት አገር ወደ ስዊድን እንዲጓዙ በአንድ ሰው አንድ የአይሮፕላን ቲኬት ዋጋ የሚሸፍን ይሆናል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የበረራው ቲኬቱን ያዘጋጅልዎታል።

ማመልከቻ

የስደተኛ ቤተ ዘመድ ወደ ስውድን ሲጓዝ የሚሰጥ የመጓጓዣ ድጎማ ማመልከቻ ቅጽ (blankett) 4452 (በስዊድንኛ) Pdf, 1.1 MB, opens in new window.

ማመልከቻዎን በዚህ አድራሻ ይላኩ:

Migrationsverket
Box 3100
903 03 Umeå

ይግባኝ ማለት አይቻልም

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔን ይግባኝ ማለት እይችሉም።

ሕገ ድንብ (1984:936) ቤተ ዘመዶቻቸው ወደ ስዊድን ሲጓዙ ስደተኞች የሚያወጡትን የጉዞ ወጪን ስለ መደጎም (በስዊድንኛ) External link, opens in new window.

የተለመዱ ጥያቄዎች እና መልሶች የቤተሰብ አባላትዎን ወደ ስዊድን ለማምጣት ስለ የጉዞ አበል

ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ፣ ትኬቱ የሚያዘው እና የሚከፈለው፡ የስዊድን የስደተኞች ኤጀንሲ፥ በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ”International Organization for Migration” (IOM) በኩል ነው።

የበረራ ትኬቱ የሚሰራው ዘመዶቹ ካሉበት ሀገር ወደ ስዊድን እስኪመጡ ድረስ ነው (የሀገር ውስጥ በረራዎችም ተግባራዊ ይሆናሉ)። ባቡሮች እና አውቶቡሶች ላይ አይተገበርም።

የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ልጆች የኑሮ ደገፍ የመስጠትና እና ሌሎች ወጪዎቻችን የመርዳት ግዴታ ያለበት፥ በዋናነት “የማህበራዊ አገልግሎት ባለስልጣን” (Socialtjänsten) ነው። የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ወላጅ አልባ ለሆኑ ልጆች ዘመድ የጉዞ አበል የሚሰጠው፥ “ከማህበራዊ አገልግሎት ባለስልጣን” ውድቅ የተደረገ ውሳኔ ካለ እና፥ እዚህ በስዊድን ውስጥ ስላለው ልጅ የቀረበውን ማመልከቻ አይቶ ለመፍቀድ፥ ልዩ ምክንያቶች ሲኖሩ ብቻ ነው።

Last updated: